>

የኦህዴዱ ብልጽግና አማራ ክልልን ከሁለት ለመክፈል እየሰራ ነው። (ኢትዮጵያ ን እናድን)

የኦህዴዱ ብልጽግና አማራ ክልልን ከሁለት ለመክፈል እየሰራ ነው።
ኢትዮጵያ ን እናድን


*…. የሸንጎ ሊቀመንበርና ምክትሉ (በdefacto) በዘረገፉት መረጃ መሠረት የኦህዴዱ ብልጽግና አማራ ክልልን ከሁለት ለመክፈል እየሰራ ነው።
ጠቅላይ ሚንስትሩ ሽማግሌ ወደ ሸንጎ በመላክ የአገው ሸንጎ የፓርቲ አባላትን አግኝቶ ስለ ክልሉና ስለ ፓርቲው ድርድርና ተልዕኮ የሚመስል ነገር ተነጋግሯል።
በድርድሩ የነ ሽመልሱ ብልጽግና በአለሙ ስሜ አማካኝነት ለሸንጎ የገባው ቃል፣
* ሸንጎ የአገው ብልጽግና ፓርቲ ተብሎ ዋግ ላስታን ያስተዳድራል።
( በዚህም አማራ ብልጽግና እነዚህን አከባቢዎች አይመለከተውም ማለት ነው። ይሄም በድርድሩ በሂደት አዊንም የሚያካትት ነው።)
* በቀጣይ የአገውን ክልልነት (ዋግላስታ፣ አዊና ቅማንት) ጥያቄያችሁን አብረን እንታገላለን፤
* የብልጽግናን ሃብት ሸንጎ በሚገባው ልክ ተጠቃሚ ይሆናል፤
* የአማራ ብልጽግናም ይሄንን ጉዳይ ከተወያዩበት በኋላ ክልሉን ከሁለት የሚከፍል ነገር ከሆነ ራሤን ከብልጽግና አገላለሁ ብሏል ይላል የሸንጎው ሊቀመንበርና ምክትሉ።
ይህ እንግዲህ የሆነው ሸንጎ ተጽዕኖ ፈጣሪ ፓርቲ ሆኖ አይደለም፤ ዋናው ክልሉን ማፍረስና የብጥብጥ መነኻሪያ አድርጎ ኦሮሚያ ላይ የሚካሄደውን cleansing ድምጽ አልባ ማድረግና “እናንተም ይሄው እየተፋጃችሁ ነው” የሚል አቻ ፍለጋ ነው።
ሸንጎ መሠረቴ ነው የሚለው ዋግ ሊቀመንበሩ ላንድ ቀንም እንደማያድር ያቀዋል። በጦርነቱ ጊዜ የዋግ ህዝብ ምን አይነት ስቃይ እንዳሣለፈ፣ ማን ማን እንደፈጸመውም ያቃል።
ሊቀመንበሩ ዋግ ላይ በተፈጸመ የታጣቂዎች ወንጀል በታሠረ ወዲያውኑ ነበር እንዲፈታ የተደረገው። ማን እንዳስፈታውም ይታወቃል።
እኔ በግሌ የትኛውም ፓርቲ ቢቋቋም መብቱ ነው፤ ችግሩ አላማው ህዝብና ህዝብን ማፋጀት ከሆነ ግን አደገኛ ነው፤ ራሱ ህዝቡም ሊታገለው ይገባል።
እነ አላምረው ያኔ መቀሌ ውሎ አዳራቸውን አድርገው ከርመው፣ በወረራው ወቅትም ከህወሀት ጀኔራሎች ጋር በስልክ ይገናኙ (ጄ. ጻድቃን ጋር) እንደነበር ላንድ ጓደኛው የላከው መልዕክት ላይ አንብቤአለሁ። ስለዚህ ዋግ ላይ ለተከሰተው ችግር ሁሉ በግሌ የሸንጎ ሰንሰለት በተለይም ሊቀመንበሩ አለበት ብየ አስባለሁ።
አሁን ደግሞ ሸንጎው ዉሎ አዳሩ ከአክራሪ የኦሮ*ሞ ጽ*ንፈኞች፣ ከኦነግና ከኦፌኮ ጋር ሆኗል። በየመግለጫዎቹ ሁሉ አላምረው እየተገኘ የአማራን ክልል በጅምላ ሲሳደብና ሲያንቋ*ሽሽ ይውላል። ክልሉም አቅም ስለሌለው ሲሰደብና ሲያሰድብ እየተከዘ ይጠጣል።
የክልሉ መንግስት (በነብሱ ካለ)ና የአማራ ኢሊትን የምመክረው
* ዋግ በተለየ መልኩ ከክልሉም ውስጥ ካለው አከባቢ የበለጠ የተጎዳ፣ የተጎሳቆለና በልማት ተለይቶ ወደኋላ የቀረ መሆኑን አምኖ መቀበል። ቀጥሎም ከሌላው አከባቢ ቢያንስ እኩል እንዲሆን ጠንክሮ መስራት አለበት። (ከኦሮሞ ብልጽግናና ሸንጎ ድርድር ውስጥ ከሁለት ዲጂት በላይ ቢሊዮን በጀት ይኖራችኋል የሚል እንዳለበት ልብ ይሏል)
* ክልሉ በነበረው መዋቅር ሆን ብሎም ይሁን ባለማወቅ ህዝቡን ውሃ አልባ፣ አስፓልት አልባ፣ የሰቆጣ ከተማን 1/10ኛ ህዝብ ለሌላቸው ከተሞች ዩንቨርስቲ ተክሎ ዋግን ዩንቨርስቲ አልባ፣ ክልሉ ካሉት 970 የዳስ ት/ቤቶች 786ቱ በዋግ ውስጥ የሚገኙበት ዞን አድርጎታል። ይሄንን ለመቀልበስና ለማልማት መነሣት አለበት።
*  የአገው ህዝብን ባህል፣ ቋንቋ፣ እሴት ማሳደግም የኔ ብሎ መንከባከብም ይጠበቅበታል። (ባህርዳር ዩንቨርስቲ ከአገውኛ ት/ት ይልቅ ኦሮምኛ ክላስ እንደሚሰጥ የዛሬ 3አመት አስታውቆ ነበር መጀመሩን አላቅም)
የዋግ ህዝብ ከክልሉ ህዝብ ጋር እኩል ልልማ ነው ያለው። ከዛ ውጭ አማራና አገው እያሉ ለማፋጀት የሚመጡትን ግን ከማንም በላይ ስለሚያቃቸው አበጥሮ ያጸዳቸዋል። ሲቀጥል አገው ራሱን እንደ ወላጅ አባት የሚያይ እንጂ አማራን ሌላ ህዝብ ነው ብሎ የሚያስብ አይደለም፣ እውነቱም እሱ ስለሆነ። ወንድም በወንድም ላይ ለማስነሣት የሚሯሯጡትንም እንደከዚህ ቀደሞ ይቀጣቸዋል
በወንዴ ብርሃኑ ካበው
Filed in: Amharic