>

ሀገራችን የምስራቅ አፍሪካን ፖለቲካ የምታሽከረክር፤ የቀይ ባህር ፖለቲካ ፈላጭ ቆራጭ ነበረች...!!!  ሱሌይማን አብደላ

ሀገራችን የምስራቅ አፍሪካን ፖለቲካ የምታሽከረክር፤ የቀይ ባህር ፖለቲካ ፈላጭ ቆራጭ ነበረች…!!! 
ሱሌይማን አብደላ

*…ከዘመነ 1960 እስከ 2014 አረቦችና ኢትዮጵያ !
 
አስፈሪ ነጭ ለበሽ ባለ ውሃ ሰመያዊ ቦኔት አጥላቂ ወታደሮቿ ከምፅዋ እስከ አደን፣ ከባቡል መንደብ እስከ ሶኮትራ ወደብ ድረስ እየተገማሸሩ ሲሽከረከሩ ዞር ብሎ የሚናገራቸው የማንም አገር የባህር ሀይል የለም ነበር። ንጉሳቸውን አፍሪካውያን እንደ አለት የሚያዪት፣ ራስ ተፈሪዎች እንደ ፈጣሪ የሚወዱት ነበር። ይህ ታሪክ በአንድ ወቅት የአዲስ አበባ ታሪክ ነበር።
.
የዛች አገር ንጉስ ወደ ጅዳ ቤተ መንግስት ሲመጣ ዝናብ የወረደ ያህል ነበር የሚታየው። ጃንሆይ ጅዳ የሚመጡት አስር ጊዜ ተለምነው ነው። አዎ ወደ ጅዳ እመጣለሁ የሚል መልስ ከተሰማበት ቀን ጀምሮ የጅዳ ጎዳናዎች የቀይ ባህር ጀልባዎች የኢትዮጵያን መንግስት ለመቀበል ሽር ጉድ ይላሉ። ጃንሆን ቀጥታ ከአዲስ አበባ አስመራ አርፈው ወደ ጅዳ በባህር መሄድ ይወዳሉ።
ጥቀሩን ቀይ ባህርን ሰንጥቀው ሰልካካ ወገበ ለምዛጋ አስፈሪ ቅድንብ ባላቸው አጃቢዎች በኢትዮጵያ ባህር ሀይል ታጅበው  የጅዳን ባህር ቆርጠው ጅዳ ሲገቡ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አለማ ከባህር በሩ እስከ ጅዳ በቴ መንግስት ድረስ እንደጉድ ይውለበለባል። ይህ በአንድ ከወቅ የነበረ የኢትዮጵያ ገናና ዲፕሎማሲያዊ ሀያልነት የሰራው ታሪክ ነው። ንጉሷ ተለምኖ ወደዚች አገር የሚመጣበት ታሪክ ግን 1960ዎቹ አካባቢ ታሪክ ሆኖ ላይመለስ ሰመጠ።
.
ይህ ታሪክ በአገሬው ሰው ስማቸው በጥሩም በመጥፎ የሚነሳው የንጉስ ሀይለስላሴ የስልጣን ዘመን ነው።
.
ያዘመን ሰመጠና 1960ወቹ አካባቢ ሌላ ሰው ብቅ አለ። መንግስቱ ሀይለማርያም
አረቦች ሰውየው እንደ እመጫት ነበር ነው። ከነካሀው አይለቅህም። ካከበርከው አያስነካሀም የሚል ስም ይሰጡታል። ኮረኔል መንግስቱ ሀይለማርያም። በአረቦች ዘንድ እጅግ የተከረበና እጅ የሚፈራ ሰው ነው። ሱዳን አሁን የተቆጣጠረችው መሬት ላይ አንድ ኢትዮጵያ ገበሬ ካለቀሰ ይቅርታ ብላ ለመንግስቱ ደብዳቤ ትፅፍ ነበር። ይህ ታሪክ ካርቱም ያለው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ውስጥ ተፅፍ የተቀመጠ ነው። እንኳን ሊወሩን ፣እንኳን ሊያፈናቅሉን ይቅርና።
እመጫት ነበር የሚል ስም ያለ መንግስቱ ትንሽ ስልጣን ላይ እንደቆየ አረቦች በነዳጅ ሀብታቸው ኪሳቸው ማኩረፍ ጀመረ። ኪሳቸው እያኮረፈ ሲያስቸግራቸው ወደ ልማት እና ወደተዳላደለ ኑሮ መቀየር ፈለጉ። አዎ ቢሊዮን ዶላር በቀን የሚያመርቱ አገሮች እንዴት ኪሳቸው አይቦጠጥ። የሆነው ሆኖ እነሱ እያፈረጠሙ ሲመጡ እኛ ወደ እርስበርስ ጦርነት ገባን። በሦስት አቅጫ ተከበብን።
ለምዕራባውያን የማይመች ለእስራኤል እውቅና የማይሰጠው ኮረኔል ግዙፉን የአፍሪካ ፖለቲካ መወሰኛ ማዕከል  ተቆጣጠረው። በአራት አቅጣጫ መውጋት ተጀመርን። በሻዕቢያ፣ በትህነግ በሱዳን ሸማቂ፣ በሱማሌ ወራሪ መደብደብ ተጀመርን። በሞሳድና በሲአይኤ ጥርስ ተነከሰብን። የኛ ነገር ዝናብ እንደጠገበ የወፍ ላባ መጠቅለል መቦጨቅ ማነስ ሆነ። በዚህን ግዜ አረቦች የጉልበት ሰራተኛ እንፈልጋለን የሚል መልዕክት ይዘው ወደዛች በአንድ ወቅት ዝነኛ ወደሚሏት አገር ለመሄድ ደፈሩ።
አዲስ አበባ አዲስ ነገር ሰማች። ይሄንን ደብዳቤ ያዩት የወቅቱ መሪ ኮረኔል መንግስቱ ሀይለማርያም እንዴት ብትንቁን ነው የቤትና የጉልበት ሰራተኛን ከኢትዮጵያ ለመውሰድ የጠየቃችሁን አሉ። መልሰውምይልቅ እኛ ለቤተ መንግስት አስተናጋጅ የሚሆን ቀያይ የአረብ ሰራተኞችን እንፈልጋለን የሚል መልስ ሰጣቸው። እውነትም እመጫት ነበር የሚሉት መንግስቱ አሁንም ችግር ላይ ሆኖ ገናና ስነ ልቦነው እንዳልፈረሰ አመኑ።
ያም ታሪክ በ1980ዎቹ መጀመሪያ ላይ ሰመጠ። ኤርትራም ተሸኘች። ኢትዮጵያም ኢህአዴግ በሚሉት ስብስብ እጅግ ወደቀች። አሁን ነገሮች ተቀያየሩ። ኢህአዴግ በገዛ በ3 አመቱ ያቺ በአንድ ወቅት የቀይባህር ፈላጭ ቆራጭ፣ አፍሪካ ወሳኝ የፖለቲካ ተጫዋች፣ የሆነች አገር ከሁሉም ነገሯ ወርዳ ሴት ልጆቿን ወደ አረብ አገር በሰራተኝነት መላክ ጀመረች። ስለኢትዮጵያ ምንም አንብበው የማቁት የአረብ አዲሱ ትውልድ ኢትዮጵያን በጠንካራ የቤት ሰራተኛ አቅራቢነት ተዋወቋት።
አሁን ላይ ኢትዮጵያ በአረቦች ዘንድ በሁለት ነገር ትታወቃለች። ገና ጉልበታቸው ያልተበላ ቀጫጭን ቆንጆ እድሜያቸው ከ15 እስከ 30″,አመት የሆኑ ሴት የቤት ሰራተኞችን በማቅረብ እና በጣፋጭ ቡናዋ ስሟ በቀን ሞቶ ጊዜ ይዘመራል። ምርጥ ኢትዮጵያዊነት የቤት ሰራተኛ አለች። ምርጥ ኢትዮጵያዊ የአትክልት ሰራተኛ የከብቶች እረኛ አሉኝ የሚል መለዮዋችን ታወቅን።
የነበረን አስገራሚ ታሪክ ተቀይሮ በዚህ መልኩ ተፅፏል። 
.
ውዱን ቡና የምንልክ ሰዎች። ጣፋጭ ስጋን የምናቀርብ አገሮች። ፈጣሪ ለመኖር ሀብት አድሎ በውሃና በዝናብ አመፃድቆ የፈጠራት አገር ልጆች በአረብ አገር እንዲህ ተደፍው እንዲሰሩ ተፈርዶባቸዋል።
ይህቺ በምስሉ ላይ የምታዩት እንስት የዛች አገር ብቃይ ልጅ ናት። ታዲያ ይሄንን ነገር ማን ይፃፈው። ለዚህ ያበቃንን የመንደር ፖለቲካ እንዴት አርመን ተከብረን የምንኖርበትን አገር እንመስርት የሚል ሙህራን የለም። ፕሮፌሰር፣ ዶከተር፣  የፖለቲካ ጠቢብ፣ የማህበረሰብ አንቂ፣ የኢኮኖሚ ባለሙያ፣ የምንላቸው ሰዎች ስለዚህ ነገር አይናሩም። የምድጃ ፖለቲካ ላይ ተጥደው ስለ ክልልና ስለ ብሔር ስለ እምነት ሲሰብክ ይውላሉ።
አነሰም ከፋም ወደ ኋላ ያለውን ዘመን ይራገማሉ። የነሱ ታሪክ ግን ከኋለኛው ዘመን ምን የተሻለ ነገር ሰሩ ተብሎ ቢጠየቅ ከክልሌ ውጣልኝ፣ አትስገድብኝ፣  በቋንቋህ አትናገረኝ፣ አትፀልይብኝ፣ የሚል ትውልድ መፍጠራቸው ነው። እህትና ወንድሞቹን በዘመናዊ ፓርነት አስረክቦ በነሱ የውጭ መንዛሬ የሚኩራራ ስረት መፍጠራቸው ነው።
Filed in: Amharic