>

ከአራት ኪሎ የሚሰፈርላችሁ ቀለብ የተቋረጠባቸው የእነ መሳይ ካባ ግልበጣ....!!! (ዶ/ር ዮናስ አበራ)

ከአራት ኪሎ የሚሰፈርላችሁ ቀለብ የተቋረጠባቸው የእነ መሳይ ካባ ግልበጣ….!!!
ዶ/ር ዮናስ አበራ

 

(አነ መሳይ እንዲህ ይሉን ጀምረዋል !
እኛ ደግሞ  ዝቅ ብለን እንዲያ እንላለን…) 
 
*…. Why now? ዛሬ ለምን ይሄን  ፃፍክ ብዬ እጠይቃለሁ። ለምን አምና አልፃፍክም? ለምን ከምርጫው በኋላ አልፃፍክም? በበኩሌ ብዙ ምላምቶች አሉኝ።  መሳይ መኮንን እናስቀድመው
“እየሆነ ባለው ደስተኛ መሆን እጅግ ከባድ ነው። የሚሻልን በተስፋ ብቻ እየጠበቁ መኖር ፈተናው አይጣል ነው። የሚጨበጠው እየራቀ እንጂ እየቀረበን እንዳልሆነ በግሌ ይሰማኛል። በመልካም ቃላትና ሀሳብ ውስጤን የሞላው ተስፋ አንድ ቀን እውን ይሆናል የሚለውን አሁን ላይ እርግጠኛ የምሆንበት አቅም አጥቼአለሁ። ከአደጋ ብንወጣም ሌላ ውስብስብና አደገኛ አደጋ እንደከበበን የምንደብቀው ጉዳይ አይደለም። ብዙ ምክንያቶችን መደርደር ይቻላል። ለምን እዚህ ቅርቃር ውስጥ ገባን የሚለው እንደየፖለቲካ ሰልፋችን እይታችን ቢለያይም አንድ የማንክደው እውነታ ግን ኢትዮጵያ ጽኑ ችግር ውስጥ መኖሯን ነው። ማለባበሱ ጉዳቱ ሀገር ያጠፋል። መሸነጋገሉ በድምር ውጤት ኪሳራው የህዝብ ነው። ቢያንስ ከደመናው ወጥተን፣ ከተንሳፈፍንበት ተስፋ ወርደን ስለመጪው ጊዜ አብዝተን ልንወያይ፣ ከልብ ልንነጋገር ይገባል።
ለእኔ አሁን ውስጤ የቀረው አንድ ነፍስ ያለው ተስፋ የብሄራዊ ምክክሩ መድረክ ነው። ለዚህ መድረክ ስኬት በግልና በቡድን በሚደረገው እንቅስቃሴ የበኩሌን ሚና ለመጫወት ከወዲሁ ለራሴ ቃል አስገብቼአለሁ። ይህ መድረክ የፓርቲ ድግስ እንዳይሆን፣ እንደተጨናገፉት የሀገር ተስፋዎች መክኖ እንዳይቀር ከምኞት ባሻገር በጸሎት ፈጣሪን መለመን፣ በቅን ልቦና፣ ሀገርን ባስቀደመ መርህ መስራት ይገባናል። አሁን በመንግስትም ሆነ በሌላኛው ጎራ የሚታየው የቲፎዞው ጩኸትና በድርጅት ፍቅር አቅልን የመሳቱ አዝማሚያ ለሀገር የሚበጅ አይደለም። ትንንሽ ጉዳዮች፣ ደራሽ ክስተቶች፣ እለታዊ ክንውኖች ተጠምደናል። ወዴት እንደምንሄድ፣ የት እንደምንደርስ ማናችንም እርግጠኞች አይደለንም። በዚህም በዚያም መጋለብ ነው። የእውር ድንብር ጉዞ። መጨረሻው የማይታወቅ ሩጫ።
ቢያንስ የምክክር መድረኩ ከዚህ ጊዚያዊና ስሜት ከሚነዳው የየግል ሩጫችን ጋር ፍቺ ፈጽመን እንደ ሀገር ስለ ሀገር በጋራ የምንጨነቅበትን እድል ይሰጠን ይሆናል። ከትንንሽ አጀንዳዎች ወጥተን በትልልቆቹ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በድፍረት እንድንነጋገር መድረኩን ያመቻችልናል ብለን ሌላ ተስፋ እንድንሰንቅ ያደርገናል። በባዶ ተስፋ የሚንሳፈፈውም ሆነ በጨለምተኝነት ስሜት ውስጥ የሚዳክረውን ወደ አንድ መስመር ላይ መጥተው ስለወደፊታቸው እንዲነጋገሩ ያቀራርባቸውም ይሆናል። በእርግጥ ይሄም ተስፋ ነው። ተስፋን መሸሽ አይቻልም”
የእኔ Comment
 
አይ መሳይ!!
Why now? ለምን ይሄን ዛሬ ፃፍክ ብዬ እጠይቃለሁ። ለምን አምና አልፃፍክም? ለምን ከምርጫው በኋላ አልፃፍክም? በበኩሌ ብዙ ምላምቶች አሉኝ።
1- አራት አመታት በአብይ ታውሮ የነበረው ዓይንህ “በቃኝ!” ብሎ ሊበራልህ ይሆናል፤ (very unlikely)
ወይም
2- ከአራት ኪሎ የሚሰፈርላችሁ ቀለብ ተቋርጦባችኋል፤
ወይም
3- የምታደንቀው ፀሐዩ መንግስትህ እንዳከተመለት ተረድተህ “በጊዜ” ወይ እኛ ዜጎች ላይ ወይም ቀጣይ መንግስት (ቀጣይ መንግስት ከመጣ ነው ለዚያውም) ላይ አርፋ ወጥተህ ልትፈናጠጥና የአጥቢያ አርበኛ ሆነህ “እኛም ያቅማችንን ያህል አገዛዙን ለመጣል በሚዲያ ስንታገል ነበር” ልትል አስበሃል፤
ወይም
4- አብይ አህመድ ለኢሳቶች አዲስ ሴራ ነድፎ ስጥቷችሁ “ግማሽ መንገድ ድረስ የህዝቡን እሮሮ ከአንገት በላይ በስርዓቱ የተበሳጨ በመምሰል ተጋሩና እንደገና አግበስብሳችሁ አምጡና እግሬ ስር ጣሉልኝ ብሏችሁ ያንን ለማስፈፀም መሞከርህ ነው፤
እንጂማ
 ስንት ፖለቲከኞች ለአራት አመታት ኡኡኡ ያሉበትን ጉዳይ አንተ ዛሬ እንደ አዲስ በጤና አላመጣኸውም!!
አየህ ህዝብ እምነት ሲያጣብህ?
 ሁሌ ውሸት ስታወራ ስለከረምክ ዛሬ ተነስተህ እውነት ከላይ ያለውን የፃፍከው የእውነት የኢትዮጵያ ጉዳይ አሳስቦህ እንኳን ቢሆን እስከወዲያኛው ህዝብ አያምንህም!! እየደማህ ቢያይህ ውሸቱን ነው ቀይ ቀለም ተቀብቶ ነው ትባላለህ!!
አንድ በእርግጠኛነት ማወቅ ያለብህ ነገር ግን አሁን ሁሉም ነገር ረፍዷል። ይሄ ጊዜ ይመጣ ዘንድ ነበር despite every grave injustice done by the government and its entourage ከህዝብ ጋር ሳይሆን ከአገዛዙ ጋር ሙጢኝ ያልከው!! እስክንድር የኦሮሞን ህዝብ ሽብርተኛ ሲል ፈረጀ ብለህ ያሳሰርከው!! ትግሬን በሙሉ ለቃቅመን መጋዘን ውስጥ እናጉር ያልከው!!
እደግመዋለሁ
 አንድ በእርግጠኛነት ማወቅ ያለብህ ነገር ግን አሁን ሁሉም ነገር ረፍዷል!! ወደፊት ታሪክ ሲፃፍ “ለውድመቱ የራሳቸውን ሚና ከተጫወቱት መካከል” በሚለው chapter ስር አንተና የኢሳት ጓደኞችህ ከላይ ካሉት 5 ረድፎች ውስጥ ትፃፋላችሁ። እንኳን ደስ ያለህ!!
Filed in: Amharic