>

ይድረሰ ለጠቅላዩ (ዘምሳሌ )

ይድረሰ ለጠቅላዩ

መግደል መሸነፍ ነው  ብለህ እያወራህ

ቤተስኪያን መስጊዱን ሲፈርስ ዝምብለህ

ህፃን ሽማግሌ ባልቴትን ጨምረህ

ገደል  ሲከቷቸው  በየቀኑ እያየህ

 

ስንቱ እየተራበ አንተ ስታወራ

በእርዳታ እየኖርክ መዝናኛ ስትሰራ

ፖርክ ልማት ብለህ  ባዶ ስትኩራራ

ህዝቡ ሲፈናቀል በየሁሉ ስፍራ

 

ፍላጎትህ ሞልቶ ህልምህም  ተሳክቶ

ጭንቀት ሆኖ እያለ  ወንጀል  ተበራክቶ

ሀገር  በየቀኑ ጩኸቷ በርክቶ

አንተን ያደነዘህ አዕምሮ አሳጥቶ

የቱ አዚም  ይሆን ውስጥህ  ያለው ገብቶ

የፈፀምከው ስህተት  የደረብከው ካባ

በድግስ   ተጠምደህ ህዝቡ እያነባ

በኑሮ ውድነት  ግራ እየተጋባ

ሀገር  ስትሸበር በታቀደ  ደባ

ዳቦ በሙዝ ብሉ እያልክ ስትገባ

የእምነት በር ጨብጠህ ለጊዜው ቢመስልህ

ስዩመ እግዚአብሔር  እስከመባል ደርሰህ

ላሻግራችሁ ስትል  ሙሴያችን ተብለህ

ታላቋን ኢትዮጵያ በጎሳ ለውጠህ

ያስፈጀኸው ወጣት ቃሎችህን አጥፈህ

የንፁሀኑ ነፍስ ተፈናቃይ  እምባ

የአሳምነው  ፅጌ የሰዐረ ደባ

የወለጋው ወንጀል ጨምሮ  አዲስ አባ

ደቡብ ምስራቅ ሰሜን በየሁሉ አምባ

የስልጣን ዘመንህ የተንኮል  ሽረባ

ውሸት ስታሰብክ ብልፅግና ብለህ

በመደመር  ስሌት ስንቶቹን አጣፍተህ

ሀገር ጠል ካድሬዎች ምክርቤት ሰብስበህ

ቤት እምነት ሲቃጠል  አፍህን ለጉመህ

የተሰጠህ አደራ  ቃል ኪዳን ስትገባ

በአድናቂዎችህ ዙሪያ ተብሎልህ ወሸባ

በስመኝ ቀድሰህ ሀገር ቤት ስትገባ

ሰው በዘር ሲገደል ስታፈስ የአዞ  እምባ

በመለስ ድርጅት በስለላው ተቋም

ወንጀልን ስትሰራ ንፁሀን ስታስለቅም

የታጠብክበት ደም ቢሆን የሚያሰጥም

የግፉአኑ ነፍስ  መች እንዲህ ልተክርም

 

ካባ  ለብሰህ ግደል ህዝብ አላልቅ ብሎሀል

የኛ ኢትዮጵያዊነት መቼስ  ይገባሀል

አይቀር የህዝብ እምባ በቁምህ ያንቅሀል

እመነኝ  አንተ ሰው  ያልተመለስክ እንደሁ  ቀን ተቆጥሮብሀል

ልክ እንደ ጋዳፊ ሜዳ ይጎትቱሀል!

 

Filed in: Amharic