>

"መስቀል አደባባይን የተለያዩ አካላት የሚጠቀሙበትና የጋራ ነው ማለት ተደባደቡ ከማለት ያነሰ አይደለም...!!!"  (

“መስቀል አደባባይን የተለያዩ አካላት የሚጠቀሙበትና የጋራ ነው ማለት ተደባደቡ ከማለት ያነሰ አይደለም…!!!” 
ብፁዕ አቡነ አብርሃም ሊቀ ጳጳስ 
 
*…. መከራን መቀበል እንጂ መከራን በሰዎች ላይ መጣል የክርስቲያናዊ ጠባይ ባለመሆኑ ሁሉን እንችላለን የግፍ ጽዋይቱ እስክትሞላ…! 
 
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በዛሬው ዕለት በባሕርዳር ከተማ በተከበረው የሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ ተገኝተው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ በሰጡበት ወቅት ነው መስቀል አደባባይን የተለያዩ አካላት የሚጠቀሙበትና የጋራ ነው ማለት ተደባደቡ ከማለት ያነሰ አይደለም ሲሉ የገለፁት።
መስቀል አደባባይ ደመራው የሚደመርበት ሥፍራ ብቻ ነው ማለት ሞኝነት ነው ያሉት ብፁዕነታቸው አደባባዩ ካህናቱ ልብሰ ተክህኖ ለብሰው ስብሐተ እግዚአብሔር ያደረሱበት ሥፍራ ሁሉ ነው ያሉ ሲሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን “ሀገር ናት” የሚለው ንግግር ከቃል አልፎ በተግባር ሊያረጋግጥላት ይገባል ብለዋል ብፁዕ አቡነ አብርሃም።
የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን መብት ሊከበር ይገባል ያሉት ብፁዕነታቸው ኦርቶዶክሳውያን የሰላም ልጆች ናቸውና ከሁሉም ጋር በሰላም ይኖራሉ እንኖራለን ብለዋል። መከራን መቀበል እንጂ መከራን በሰዎች ላይ መጣል የክርስቲያናዊ ጠባይ ባለመሆኑ ሁሉን እንችላለን የግፍ ጽዋይቱ እስክትሞላ…!  በማለት ገልፀዋል።
Filed in: Amharic