>

ከ90 በላይ  ፖሊሶችና የልዩ ሃይል አባላት በጅምላ ተጨፍጭፈው  ጫሞ ሀይቅ ውስጥ ተጣሉ...!!! አዲስ አበባ ባልደራስ

ከ90 በላይ  ፖሊሶችና የልዩ ሃይል አባላት በጅምላ ተጨፍጭፈው  ጫሞ ሀይቅ ውስጥ ተጣሉ…!!!
አዲስ አበባ ባልደራስ

የደቡብ ፖሊስ አባላት እና የፌደራል ፖሊስ አባላት

የኢትዮጵያ ህዝብ ይወቅልን! 


በደቡብ ክልል ከ 90 በላይ የፌዴራል ፖሊስና የደቡብ ክልል ልዩ ሃይል አባላት በድራሼ ልዩ ልዩ ወረዳ ሆልቴ ላይ ሚያዝያ 18 ቀን 2014 ዓ.ም በወረዳው በተደራጀው የሽብር ቡድን(የኦነግ ሸኔ አባላት ጭምር) በጠራራ ፀሐይ  በገፍ ከተጨፈጭፈው አስክረናቸው በገጀራ ተቆራርጦ ብልታቸው ተቆርጦ እራቁታቸውን ወንዝ ውስጥ ተጨምረው ሌሎቹ ጫሞ ሐይቅ ውስጥ ተጥለዋል። የተገኙ አስክሬኖች መለየት ባለመቻሉም ትላንት ሚያዝያ 25 ቀን 2014 ዓ.ም አስክሬኖቹ በሸሌ ሞዞሪያ አካባቢ ቆላ ሼሌ በሚባል ቦታ በጅምላ ተቀብረዋል።
የደቡብ ክልል መንግስትም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ክልሉና ሀራቸውን ለዓመታት በክብር ያገለገሉ ከ90 በላይ የፌዴራል ፖሊስና የልዩ ሃይል አባላት አሰቃቂ ጭፍጨፋን አስመልክቶ የሀዘን መግለጫ እንኳን ሳያወጣ፤ የክልሉ ምክር ቤት በክልሉ ምንም እንዳልተፈጠረ ፕሮጀግቶችን እየጎበኘን ነው የሚል አሳፋሪ ክህደት እየፈፀመ ነው ::
 የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ሀላፊ የሞቾቹ አስክሬን እንኳን ለማንሳት ባልቻለበት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ አቶ አለማየው ባውዲ በደቡብ ቴሌቪዢን ቀርቦ የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር ተቆጣጥረንዋል መንገድ ተከፍቶል በማለት አይኑን በጨው አጥቦ ይዋሻል ለማን ነው ግን የሚዋሸው ::
ከሆልቴ በጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የምትገኘው የጋቶ ቀበሌ ሙሉ በሙሉ በእሳት ወድማለች። በሺዎቸ የሚቆጠሩ የኩስሜ እና የሌሎች የጎሳ አባላት ዛሬ ላይ ያለ ምግብ፣መጠለያ እና ውሃ ጎዳና ወድቀዋል።
መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በደቡብ ክልል የተፈፀመው አረመኒያዊና ዘግናኝ ጭፍጨፋ በመኮነን ድርጊቱን የአለም ህዝብ እንድያውቀው ማጋለጥ አለበት!
ፍትህ ለደብብ ወንድሞቻችን። ለወገኖቻችን።
Filed in: Amharic