>

ከእንግሊዝ መጥቶ ፋኖን የተቀላቀለው ሰሎሞን ቦጋለ  ታሰረ...!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

ከእንግሊዝ መጥቶ ፋኖን የተቀላቀለው ሰሎሞን ቦጋለ  ታሰረ…!!!

ቬሮኒካ መላኩ
ፋኖ ሰለሞን ቦጋለ ከሀገረ እንግሊዝ የአማራን የህልውና ትግል ለመቀላቀል የመጣ የቁርጥ ቀን ታጋይ ነው።
በአማራ ልዮ ኃይል ላይ ለምን ሸፍጥ ይሰራል? ጄኔራሎቹስ ለምን ተባረሩ? ፋኖ ለምን ይዋከባል? የሚሉ ጥያቄዎችን በህዝብ መድረክ በማንሳቱ ነው በጎንደር ከተማ ብልፅግና ለእስር የዳረገው።
ፋኖ ሰሎሞን ቦጋለ በጎንደር ከተማ፤ 2ኛ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ታስሯል። ፋኖው ካለፈው እሁድ ሚያዚያ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በእስር ላይ ቢሆንም፣ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ፍርድ ቤት አልቀረበም። ፖሊስ ሰሎሞንን ለማሰር በሰበብነት የጠቀሰው ‘የሰዓት እላፊ አዋጅን ጥሰሃል’ የሚል ነው። ይሁን እንጂ አዋጁን በመጣስ የተጠረጠረ ማንኛውም ሰው ከአንድ ቀን የእስር ቤት ቆንታ በኋላ በ5 መቶ ብር የገንዘብ ዋስትና እየተፈታ ቢሆንምቨ ሰሎሞን የዋስትና መብቱን ተነጥቋል።
ፋኖ ሰሎሞን ቦጋለ ባለፈው የጥምቀት በዓል የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጎንደር  በተገኙ ጊዜ ” አዳነች በበዓሉ አከባበር ላይ ንግግር ማድረግ የለባቸውም” በማለት እንዳስተባበረ በመጥቀስ የአካባቢው የመንግሥት ባለሥልጣናት ሲወነጅሉት መቆየታቸውን የመረጃ ምንጮች ተናግረዋል።
እንደ ምንጮች ገለፃ የሰሞኑ እስርም ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው።
ሰሎሞን ቦጋለ ኗሪነቱ በእንግሊዝ፤ ሎንዶን ቢሆንም፣ ከወያኔ ጋር ጦርነት በሚደረግበት ወደ ኢትዮጵያ  ገብቶ ከፋኖ ጋር በመዝመት በርካታ አስተዋፅኦ ከድርጓል። በተለይም ከፍተኛ የደጀንነት አገልግሎት ሰጥቷል።
ማዋከቡ እስሩ ከግንቦት 03/2014 ከባህርዳሩ የእውቅና ሽልማት በሗላ በስፋት ይጀምራል ተብሎ የታቀደው ፋኖን የማፍረስ እቅድ ከወዲሁ እየጀመሩት መሆኑ ታውቋል።
ፋኖን የማዋከቡ ስራ በምስራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ አካባቢ ትጥቅ በመቀማት አሐዱ ብለው ጀምረዋል።
Filed in: Amharic