>
5:21 pm - Monday July 20, 9096

"እውቅና እና ሽልማት ለመስጠት የተሄደበትን የሴራ አካሄድ ተገንዝበናል  ...!!!" (የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር)

“እውቅና እና ሽልማት ለመስጠት የተሄደበትን የሴራ አካሄድ ተገንዝበናል  …!!!”
የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር
            አሻራ ሚዲያ 

ከአማራ ፋኖ አንድነት  በጎንደር  የተሰጠ መግለጫ ።
በህግ ማስከበርና በህልውና ዘመቻ የተከፈለ መስዋዕትነት ለኢትዮጵያ ሉዐላዊነት እና አንድነት በሚል መሪ ቃል ዛሬ ማለትም በቀን 03/9/2014 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ የተካሄደው የውቅና ፕሮግራም የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተካሂዷል ። የዚህ በፕሮግራም  ሀሳቡ ጤነኛ ሊሆን ይችላል ነገር ግን እውቅና እና ሽልማት ለመስጠት የተሄደበት ሂደት ትክክል እንዳልሆነ ተገንዝበናል። ሽልማት የተበረከተላቸው አንዳንድ የፋኑ አባላት፣የልዩ ሃይልና የምልሻ አባላትም ሆነ ሌሎች ግለሰቦች ትክክለኛ ሊሆን ይችላል። የአንዳንዶቹ ደግሞ ፈፅሞ አይደለም ሽልማት ፋኖ የሚለው መጠሪያ ስም የማይገባቸው አካላትም እንዳሉ አይተናል። በጦርነት ወቅት መስዋዕትነት ለሆኑ ማናቸውም አካል የክብር ስም መስጠቱ ተገቢ ነው። ቤተሰቦቻቸውንም ዘላቂ በሆነ መንገድ መደገፍ እንዳለባቸው እናምናለን ።
ከዚህ ፕሮግራም ተግባራትና መልዕክት ተነስተን የሚከተሉን ነጥቦች ማድረስ እንዳለብን አምነናል።
1. መሪ ቃሉ ችግር የለበትም። የሽልማት አሰጣጥ ላይ ትልቅ ችግር እንዳለ አይተናል። ለምሳሌ ያክል ውስጣዊ የመንግስት ቃል አቀባይ ሆነው ከመንግስት ዕዝ ውጭ መታገል የማይችሉ አካላትን በፋኖ ስም መሸላም ተገቢ አይሆንም። ሽልማቱ እንኳን ያስፈልጋል ተብሎ ከታመነ ስንት በጀግንነት ጀብድ የፈፀሙ የፋኖ አባላትን ያካተተ አልነበረም።
ከዚህ በተጨማሪ ከዚህ ግባ የሚባል የትግል መስመር የሌላቸው ፣የመንግስት ውስጣዊ ተከፋይ በሆኑ ግለሰቦች እከሌ አባበለው ነው ጀግና በማለት በሀሰት ቃል አቀባይነት እጩ ተደርጎ የተሸለመ አካል እንዳለ ተረድተናል።
ጀግናን የሚያውቀው ጀግና እንደሆነ እናምናለን።
2. ዋጋ ለከፈለ አካል እዉቅና መሰጠቱ ተገቢ ነው። ሊበረታታ የሚገባ ጉዳይም ነው።
የተዘጋጀው ፕሮግራም እውነት አንድነትን የሚፈጥር ነው ወይ ከተባለ እንደ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ፕሮግራሙ ብዙ ዕፀፅ ያሉበት ከመሆኑ አንፃር ልዩነት እንደተሰበከ እንረዳለን። ስለሆነም በጎንደር፣በሽዋ፣በወሎና በጎጃም የምትገኙ የፋኖ አባላት በሙሉ የሰራችሁት ጀብድ ጠላት ያውቀዋል!! የቆምክለት ህዝብም እውነተኛ ታሪኩን ይመሰክራል!! ከዚህ በመረዳት ከምንጊዜውም በላይ የአንድነት ማማችን ከፍ ማለት እንዳለበት በአፅንኦት እናሳስባለን !!
3. ለልዩ ሃይልና ሚሊሻ አባላት በሙሉ መሸላም ሲገባቸው ያልተነሱና የታለፉ አካላት ሊኖሩ ይችላሉ። ነገር ግን ዋናው ቁም ነገር ከጠላት ጋር መፋለምህን ያዝ። ይህ የአንድ ቀን ፕሮግራም ነው። በዚህ የተነሳ በመካከላችሁ አንዳችም ልዩነት እንዳይፈጠር መልዕክታችን ነው።
4. የፋኖ አባላትን እያሳደዱ፣ወደ ስር እየወረወሩና ፋኖ መፍረስ አለበት እያሉ በጎን የሚሰጥ ሽልማት ጤነኛ አይሁንም። ለፋኖ የወርቅ ሆነ ሌላ ሽልማት ከምሰጠት ይልቅ ማሳደድን እንደ ማቆም ትልቅ ነገር አይኖርም !! ህዝብ ሊፈርድ ይገባል። የህዝብ ብይን እንቀበላለን ። እውነታው ምንድን ነው?
5. የትግራይ ወራሪ ሃይል ለዳግም ወረራ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው። የጠላት ሃይል በጠለምት፣በኮረም አላማጣና በወልቃይት ጠገዴ እያጃበበ መሆኑን በመረዳት ሁሉም ነፃነት ፈላጊ አካል ትኩረቱን ወደ ግንባር ማድረግ አለበት።
           አርበኝነት አርማችን ነው!!
           የፋኖ ሽልማቱ ነፃነቱ!!
Filed in: Amharic