>

ለውጥ መጣ ተብሎ - የኢትዮጵያ ጉዳይ የማያሳስበው ነውረኛ አገዛዝ ላይ ወድቀናል...!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

ለውጥ መጣ ተብሎ – የኢትዮጵያ ጉዳይ የማያሳስበው ነውረኛ አገዛዝ ላይ ወድቀናል…!!!

አቻምየለህ ታምሩ

 


*…. የሻዕብያን ያኽል እንኳን የኢትዮጵያ ጉዳይ የማያሳስበው ነውረኛ አገዛዝ በኢትዮጵያ መንበር በመንግሥትነት የሚሰየምበት ጊዜ ሊመጣ ይችላል የሚል ግምት እስካሁን ድረስ ኖሮ የሚያውቅ አይመስለኝም።

ሆኖም ግን ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ ላይ ያንዣበበው አደጋ በመንግሥትነት ከተሰየመው የኦሮሙማ የአፓርታይድ አገዛዝ በላይ የኤርትራን መንግሥት አሳስቦት መግለጫ አውጥቷል።

በውድቀት አፋፍ ላይ እያጣጣረች የምትገኘዋን ኢትዮጵያን በከንቱ ውዳሴ ወደ ተስፋ ምድርነት ለመቀየር ሩብ ጉዳይ የቀራት፣ በወረራ አደጋ ላይ ያልወደቀችና የሰላም አየር የምትተነፍስ አድርጎ የሚያቀርባት በመንግሥትነት የተሰየመው የኦሮሙማ የአፓርታይድ አገዛዝ በኢትዮጵያ ላይ ስላንዣበበው የፋሽስት ወያኔ አደጋ አንዳች ቃል ትንፍሽ ሳይል አደጋው ያሳሰበው የኤርትራ መንግሥት ስለ ኢትዮጵያ መግለጫ አውጥቷል።

በሌላ አነጋገር በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ላይ ስላንዣበበው የፋሽስት ወያኔ አደጋ ባለጉዳይ ሊሆን ከሚገባው በመንግሥትነት ከተሰየመው የዐቢይ አሕመድ የኦሮሙማ የአፓርታይድ አገዛዝ በላይ የኤርትራ መንግሥት ተቆርቋሪ ሆኗል።

በአለም ታሪክ እንደዚህ አይነት የወርሮ በላይ አገዛዝ በመንግሥትነት ተሰይሞ የኖረበትን ጊዜ አላስታውስም። ለውጥ መጣ ተብሎ እዚህ ደርሰናል። የጉድ አገር!

https://shabait.com/2022/05/17/%e1%88%93%e1%89%b0%e1%89%b3-2/

Filed in: Amharic