የአማራ ሕዝብ የተደቀነበትን ተጨባጭ የህልውና አደጋ እንደ ህዝብ መመከት የሚችልበትን አቅጣጫ ከማሳየታችን በስተቀር አንዳችም የወንጀል ድርጊት አልፈፀምንም። ብልፅግና እና አሽከሮቹ ዛሬ ላይ የሚያሳድዷቸው አባሎቻችን ወንጀል ምንድን ነው? ተብለው አስር ግዜ ቢጠየቁ የሚሰጡት ብቸኛ መልስ ፎቶ ተነስታችኋል። ከተማ ውስጥ መሳሪያ ይዛችሁ ታይታችኋል የሚል ነው።
የብልፅግና መንግስት እስካሁን ድረስ በአሽሙርም በቀጥታም በእኛ ላይ ውግዘት ሲያደርስ ከመቆየቱ በስተቀር ኃላፊነት እንደሚሰማው መዋቅር ከእኛ ጋር የፊት ለፊት ውይይት ለማድረግ ፍላጎት አሳይቶ አያውቅም።
ይሁን እንጅ ህግ ማስከበር በሚል ስም በተከፈተው የፋኖ ብተና ዘመቻ የአማራ ህዝባዊ ኃይል(ፋኖ) አመራር እና አባላትን፣ ሌሎች የፋኖ አደረጃጀቶችን እና የነቁ ወጣት እና ምሁራንን ያለ ህጋዊ መንገድ ያለ መያዣ እና መበርበሪያ ትዕዛዝ በሌሊትም ጭምር እያፈነ ይገኛል።
ይኸ ዘመቻ አማራን የማንበርከክ ዘመቻ እንደሆነ መሬት ላይ እየተከናወነ ካለው ሂደት በቀላሉ መረዳት ይቻላል። በርካታ ንፁሃንን እና ለሀገር ዋጋ የከፈሉ ፋኖወች በጥይት እየተገደሉ ነው። ሌሎችም እየተሳደዱ ነው።
ስለሆነም:-
1/ የአማራ ሕዝብ ወንዝ እና ድንበር ሳይገድብህ ይህንን “ድምፅ አልባ ወረራ” በመቃወም ከፍትህ እና ከልጆችህ ጎን በመቆም በማንኛውም ዓይነት የትግል መንገድ ወራሪውን እንድትከላከል፣
2/ መላው አባላቶቻችን አርበኛ ዘመነ ካሴን ጨምሮ በሁሉም የህዝባዊ ኃይሉ አመራር እና አባላት ላይ እየተደረገ ያለውን አፈና እና ወረራ በመስበር ታሪካችንን በደማቅ ቀለም እንድንፅፍ፣
3/ መላው የአማራ ፋኖ በተናጥል እና በጅምላ የተደቀነበትን የመጥፋት አደጋ እና የአማራን ህዝብ የመወረር ተጨባጭ ሃቅ በመገንዘብ ህዝቡን በከፍተኛ ቁርጠኝነት፣ ትጋት እና ፍጥነት ህዝቡን በማስተባበር አፋኙ እና ወራሪው ቡድን ከድርጊቱ እንዲታቀብ የሚያደርግ ማናቸውንም የትግል መንገዶች እንድንጠቀም፣
4/ የአማራ ልዩ ኃይል እና አድማ ብተና አባላት በወንድሞቻችሁ ላይ ምላጭ ላለመሳብ ያሳያችሁትን ስክነት እና ህዝባዊነት አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ እና የፀረ-ወረራ ተጋድሎውን እንድትቀላቀሉ፣
5/ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የማንንም መብት ሳንነካ፣ ንፁሃንን ሳንገድል፣ ሳንዘርፍ፣ ሳንደፍር፣ መንግስትን በሃይል የመገልበጥ ተግባር ውስጥ ሳንገባ የአማራን ህዝብ ህልውና እና የኢትዮጵያን አንድነት ለማፅናት የሚበጅ አደረጃጀት ለመፍጠር ስለጣርን ብቻ እንድንጠፋ የተዘመተብን መሆኑንን ተገንዝበህ ከጎናችን እንድትቆም ጥሪ እናስተላልፋለን።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ
ግንቦት 12 ቀን 2014 ዓ.ም
ባሕርዳር-ኢትዮጵያ