>

በአማራ ህዝብ ሁሉ ላይ የተመዘዘች ሰይፍ ወይስ በግዝፈተ መንፈስ እስከ ጥቅል ክርስቲያን ኢትዮጵያ  ዘለግ ያለች...??? (ሸንቁጥ አየለ)

በአማራ ህዝብ ሁሉ ላይ የተመዘዘች ሰይፍ ወይስ በግዝፈተ መንፈስ እስከ ጥቅል ክርስቲያን ኢትዮጵያ  ዘለግ ያለች…???
—‐—–
ሸንቁጥ አየለ
——-
በምንም የፖለቲካ አይዲዮሎጂ ያልተሰባሰቡትን እና ያልታጠቁትን ወጣቶች ለመጨፍጨፍ የኦህዴድ ሰራዊት በአዉሮፕላን በታንክ እና በብዙ ሀይል ተጠናክሮ የዘር ማጥፋት ስራዉን ቀጥሏል፥፥
በጎጃም፥ በወሎ ፥ በሸዋ እና በጎንደር ያልታጠቁ ንጹሃን ወጣቶችን ማፈን ፥ መግደል እና በጅምላ መጨፍጨፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል፥፥ ይሄ በኦህዴድ እና ብአዴን የሚመራዉ ወንጀል  በኦፌኮ ስብስብ ምክር ለጋሽነት ብዙ ወጣቶችን የማጥፋት አላማ እንዳለዉ ግልጽ ሆኗል፥፥
 ይሄን ወንጀለኛ የአማራ ወጣቶችን የማጥፋት እንቅስቃሴ. ጃጃው ሞላ ፥ ጌትነት አልማው ፥ ብሩክ አበጋዝ እና የመሳሰሉት ከየአካባቢዉ የፈለቁ ከሃዲያን  ከኦህዴድ ሀይል ጋር ተባብረዉ  በፕሮፖጋንዳዉ ዘርፍ እየመሩት ነዉ፥፥ እነዚህም ሰዎች አንድ ሰሞን ፋኖ ነን ሲሉ የነበሩ ናቸዉ፥፥
ለማንኛዉም በባንዳ ስብጥር ከሆነ የአማራ ክልልን የሚመራዉ ይልቃል ከፍያለዉ ከጎጃም ነዉ መገኛዉ፥፥ ከይልቃል ከፍያለዉ ጋር የእማራ ወጣት ላይ የሞት ድግስ እያስተባበረ የሚገኘዉ በፌደራል ደረጃ ትልቅ ስልጣን ያለዉ አገኘሁ ተሻገር ከጎንደር ነዉ፥፥ልክ እንደነዚህ ሰዎች ሁሉ ከሸዋም ከወሎም በባንዳነት ተሰልፈዉ ያልታጠቀዉን የአማራ ወጣት እያስጨፈጨፉ ያሉ ብዙ ናቸዉ፥፥
ስለዚህ ባንዳዳዎች ከሁሉም እካባቢ መሆናቸዉን መዝግባችሁ ያዙ፥፥ ጠላት ከሚሰራዉ ማወናበጃ አንዱ  ሆን ብሎ አንዱ አካባቢ ከሱ ጋር እንደተሰለፈ በማድረግ ፕሮፖጋንዳ ይነዛል፥፥ የተወሰኑ ሰዎችን ስም እየጠራም የዚህ አካባቢ ሰዎች  በሙሉ ከኛ ጋር ናቸዉ ይላል፥፥
እዉነታው አንድ ነዉ፥፥ እየተቀጠቀጠ ያለዉ አማራዉ ተነጥሎ ነዉ፥፥ አማራን ነጥሎ ለመቀጥቀጥ ብዙ ሰበብ ይዘጋጃል፥፥ ብዙ ባንዳም  ከጠላት ወግኖ ይቆማል፥፥
አሁን በቀደም በጎንደር  ሙስሊም ክርስቲያኖች ሳይጣሉ ኦህዴድ/ብአዴን እራሳቸዉ ረብሻ ቀስቅሰዉ ብዙ ህይወት አጠፉ፥፥ በአስገራሚ ሁኔታ የአማራ ህዝብ በሚሊዮን ከወለጋና ቤኒሻንጉል ሲጨፈጨፍ በደስታ ዝምታ ሰመመን ዉስጥ የነበረዉ ኦፌኮ አለባህሪዉ የሙስሊም አማራዎች ተቆርቋሪ ሆነ፥፥ እናም በፍጥነት የኦህዴድ/ብአዴን ሚስጢራዊ ረብሻ የምክክሩ እካል የሆነዉ ኦፌኮ መግለጫ አውጣ፥፥ የችግሮቹ ሁሉ ምንጭ ፋኖ ነዉና ፋኖን አጥፉልኝ  የአማራ ክልል ወጣትን ጨፍጭፉልኝ ብሎ ተቃዋሚም መካሪም መስሎ ለወሮበላዉ መንግስት አቤት አለ፥፥
በዚያ መሰረትም ይሄዉ ያልታጠቀዉ እና ሰላማዊ  የአማራ ወጣት እየተቀጠቀጠ እየተጨፈጨፈ ነዉ፥፥
የዚህ ጭፍጨፋ ግብ አንዳንዶች በመላዉ አማራ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ ነዉ ይላሉ፥፥ይሄ አባባል ግን ግማሽ እዉነት ነዉ፥፥
ይሄ ጭፍጭፋ የተዋህዶ ኦርቶዶክስንም የመጨረሻ ቅስም መስበሪያ ስትራቴጂ ጭምር ተደርጎ ከአክራሪ  አልቃይዳ አይሲስ እና ተዛማጅ ሀይሎች ጋር ከመጋረጃ ጀርባ ብዙ ገንዘብ ተመድቦለት፥ ብዙ ተንኮል ተተብትቦለት የተነደፈ ክርቲያን ኢትዮጵያን ወዟንም ርሿዋንም ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ታጣ ዘንድ እየተሰራ ያለ መርዛማ ስትራቴጂ ነዉ፥፥
—————
የሚሆነዉ ግን ሌላ ነዉ፥፥
ዉጊያዉ ከመድሃኒዓለም ጋር ነዉና የድሉም ባለቤት እርሱ ነዉ፥፥ ኢትዮጵያም ትድናለች፥፥
እመን እንጂ አትፍራ !
—–
እግዚእብሄር ኢትዮጵያን ይባርካ
Filed in: Amharic