>

አንድ አጭር ጥያቄ ለፍትህ ምኒስትሩ ለዶከተር ጌድዮን ጢሞትዮስ (አበጋዝ ወንድሙ)

አንድ አጭር ጥያቄ ለፍትህ ምኒስትሩ ለዶከተር ጌድዮን ጢሞትዮስ

አበጋዝ ወንድሙ


የፍትህ ምኒስትሩ ዶክተር ጌድዮን ጢሞቲዎስ የመንግስት ባለስልጣን ከመሆኑ ጥቂት ቀደም ብሎ  በትዊተር ገጹ ላይ የሚከተለውን አስፍሮ  ነበር።

በፖለቲካ ውሳኔ፣ለፖለቲካ አላማ ክስ ይመሰረታል። በፖለቲካ ውሳኔ፣ለፖለቲካ አላማ ክስ ይቋረጣል። ስልጣንን ለመጠበቅ ሰዎች ይታሰራሉ፣ ስልጣንን ለማቆየት ደግሞ ይፈታሉ። ሕግ ሙሉ በሙሉ በፖለቲካ ሞግዚትነት ስር በሚያድርበት ሀገር፣ ሕግ ለሃቅና ለፍትህ ባዳ ሆኖ በፍርድ አደባባይ ሸፍጥ ይገናል። ለማንኛውም፣ ፓርላማ ልናያቸው ሲገባ ዘብጥያ የከረሙት ሊፈቱ መሆኑ ደስ ይላል። ሆኖምየፍትህስርዓቱ ፈርሶ ካልተሰራ ይሄው በፖለቲከኞች ፈቃድ የማሰርና የመፍታት ዑደት ይቀጥላል

ዶክተር ጌድዮን ጢሞቲዎስ ዛሬ ላይ ቆሞ፣ ላለፉት ሶስት አመታት፣ እሱ ከጠቅላይ ዓቃቤ እስከ አሁን ካለበት የፍትህ ምኒስቴር፣ መአዛ አሸናፊ ደግሞ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዘዳንት ሆና በመምራት ላይ ያሉት ተቋማት የሚያስተዳድሩት ስርዓት፣ ‘ፈርሶ የተሰራ’ የፍትህ ስርዓት ነው ብሎ ያምናል? ወይንስ ፈረንሳዮች እንደሚሉት “plus ça change, plus c’est la même chose  በግርድፉነገሮች የተለወጡ በመሰሉ ቁጥር እንዳሉ ይቆያሉ”  ነው?

 

 

 

Filed in: Amharic