>

"ዛሬ ዘመነ ካሴን ካላስገደልን ባይ ሆድ አደሮች ነገ የኦህዴድ የጥይት ራት ናቸዉ...!!!" (አሳዬ ደርቤ / ሸንቁጥ አየለ)

“ዛሬ ዘመነ ካሴን ካላስገደልን ባይ ሆድ አደሮች ነገ የኦህዴድ የጥይት ራት ናቸዉ…!!!”

አሳዬ ደርቤ / ሸንቁጥ አየለ
 
*…. በታጋይ፣አርበኛ፣ፋኖ፣ ምሁር ዘመነ ካሴ ከበባ ውስጥ መሆን ላይ የምትሳለቁ ኢትዮጵያውያንን እያየን ነው። እወቁ ድጋፋችሁን አቁማችሁ ቁንጽል ጥያቄ ማቅረብ ስትጀምሩ የብልጽግና ሰይፍ ወደ እነንተ ይዞራል። ዘመነ ካሴ ከአለማያ ዩኒቨርስቲ  በወርቅ ሜዳልያ ፣ በዋንጫ የተመረቀ፣ዩንቨርስቲም ያስተማረ የህዝብ ጭቆና አንገፍግፎት ኤርትራ በረሀ የወረደ እውነተኛ የነጻነት ታጋይነቱ ከእነሱ የሸፍጥ ታጋይነት ጋር ቢጋጭባቸው ሊገድሉት ያሴሩበት የኢትዮጵያ ልጅ ነው ። ዛሬ እሱን ያልተከላከልክ ነገ ወየየሁ ለራስህ።
 
➔ጎጠኛ አክቲቪስቶች የሆነ ጎጥ ተወካይ ያደርጉታል፡፡ እሱ ግን በንግግሩም ሆነ በተግባሩ እንደ ኢትዮጵያ ሲያስብ ካልሆነ በቀር ከአማራነት ወርዶ ጎጥ ለጎጥ ሲሳብ የተገኘበት ቀን የለም፡፡
➔በሌላ መልኩ ደግሞ የአንድ አውራጃ ጠባቂ የሚያደርጉት ኃይሎች ‹‹እንደ ብርጋደር ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ሊዳፈኑ ወይም ደግሞ እንደ ብርጋደር ተፈራ ማሞ ሊታፈኑ የሚገባቸው አማራዎችን ዘርዝራችሁ አምጡ›› የሚል ትዕዛዝ ከበላይ አካል ሲሰጣቸው ‹‹አማራ›› ብለው በቀዳሚነት የሚጽፉት የእሱን ሥም ነው፡፡
➔ጥቅመኛ እና ተከፋይ ዙምቤዎች ካዝናውን በገንዘብ ሞልተው ይመቀኙታል፡፡ የዓላማው ግዝፈት ተረድተው የሚደግፉት ወገኖች ግን ‹‹የትኛውም ሐሳብ ያለ ገንዘብ ሊሳካ አይችልም›› በማለት ይከላከሉለታል፡፡ ‹‹ምን እንገዝህ?›› እያሉም ይጠይቁታል፡፡
➔የመንግሥት ካድሬዎች የሕብረተሰቡን ሰላም በማጥፋት ይከስሱታል፡፡ ድፍን የባሕር ዳር ወጣት ግን ስቴዲየም ገብቶ ሥሙን እያነሳ ይዘምርለታል፡፡
➔አንዳንድ የጎረቤት አክቲቪስቶች የሕዝባቸው ጠላት አድርገው ያብጠለጥሉታል፡፡ እሱ ግን ‹‹ክፋት ለማንም፣ በጎነት ለሁሉም›› በሚል አስተሳሰብ የሚመራ በመሆኑ ስለ አማራ እኩልነትና ነጻነት ከመናገር ባለፈ ሕዝብን ቀርቶ ፖለቲከኞችን  የሚያንቋሽሽ ቃል ተንፍሶ አያውቅም፡፡
➔በሌላ መልኩ ደግሞ እሱ እራሱን ከሌሎች የትግል ወንድሞቹ በላይ አድርጎ ያወራበት ቀን ባይኖርም የሚዘምቱበት ኃይሎች ግን ከወሬ የዘለለ ተግባር እንደሌለው በሚገልጽ ሐሜታቸው ዝቅ ዝቅ ሊያደርጉት ይሞክራሉ፡፡
ግን ደግሞ…
“ፋኖ መመታት አለበት” ሲባል ቀድሞ ወደ ጭንቅላታቸው የሚመጣው የእሱ መልክና የእሱ ሥም ነው፡፡  አማራን የማጥቃት ዘመቻቸውን መጀመር የሚሹትም ከእሱ ነው፡፡
“ዛሬ ዘመነ ካሴን ካላስገደልን ባይ ሆድ አደሮች ነገ የኦህዴድ የጥይት ራት ናቸዉ…!!!”
ዘመነ ካሴ ሊሸለም የሚገባዉ የህዝብ ጀግና ነዉ::
ስብከቱም ሆነ ድርጊቱ ስለ ህዝብ ነጻነት እና እኩልነት ነዉ::ከዚህ የዘለለ አንዳችም ስህተት የለበትም::
ሆኖም አንድ ሰሞን የአማራ ተጋድሎ መሪ ነን: አንድ ሰሞን የአማራ ብሄረተኛ ነን : አንድ ሰሞን  የህዉሃትን ሀይል ከኦህዴድ መከላከያ ሰራዊት ጋር ተሰልፈን ደምሳሽ ነን ሲሉ የነበሩ ሰዎች ተሰባስበዉ በዘመነ ካሴ ላይ የጋራ አቋም ይዘዋል::
ዘመነ ካሴ በህግ ማስከበር ሽፋን እንዲያዝላቸዉ ወይም እንዲገደልላቸዉ በጉጉት እየተጠባበቁ ያሉ ሀይሎች አሉ::
የሚገርመዉ እነዚህ ሰዎች በአማራ ህዝብ ስም ገንዘብ የሰበሰቡ:ህዝብን እናታግላለን የሚሉ እና ህዝብ እንመራለን የሚሉ ናቸዉ::አይገርምህም!
አስገራሚዉ ነገር ታዲያ ስለ አማራ ህዝብ እኩልነት የቆመዉን ዘመነ ካሴን እንዲገልላቸዉ ከኦህዴድ/ብልጽግና ጋር የጋራ አቋም የያዙት ሀይሎች ስለ አማራ ህዝብ ከኛ በላይ ተቆርቋሪ ከቶም በምድሪቱ ላይ የለም ባይ ስብስቦች መሆናቸዉ ነዉ::ከዚህ የከፋ ህዝባዊ ሰቀቀን ከቶም ያለ አይመስለኝም::
————
ሆኖም ዘመነ ካሴ ዛሬ ቢገደል እነዚህ ዛሬ ዘመነ ካልተገደለልን ሞተን እንገኛለን የሚሉት ሀይሎች በቀጣይ የኦህዴድ/ብልጽግና የጥይት ራት የሚበላቸዉ ናቸዉ::
Filed in: Amharic