>

ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ ፣ ቢያስከፉሽ አይክፋሽ! (ቬርኒካ መላኩ)

ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ ፣ ቢያስከፉሽ አይክፋሽ!

ቬርኒካ መላኩ


*… በ4 አመት ውስጥ 4 ርዕሰ መስተዳድር ፥ 6 ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ እና 6 ልዩ ሃይል ሃላፊ በመቀያየር ሪከርዱን የሠበረው የአማራ ክልል 5ተኛው ር/መስተዳደር እየታጨለት መሆኑን ውስጥ አዋቂዎች ሹክ ብለውናል!

ለብአዴን ይህ ምን ማለት እንደሆነ እንኳ ቢገባው ጥሩ ነበር! ዳሩ ምን ማሰቢያ አለውና!

በነገራችን ላይ ኦሮሚያ ክልል እስከአሁን የርዕሰ መስተዳድር ለውጥ አላደረገም!

ያልተረጋጋና እርስበራሱ ሲተረማመስ የሚኖር በስቋላ ክልልና ህዝብ የማፅናት ስውር ፕሮጀክት!

ወዳጄ! አለማመን መብትህ ነው!

ነገርግን አስረግጨ የምነግርህ ብአዴንን ፣ አብንን ፣ ህዝባችንንና በዙሪያው ያሉ ፋኖዎች ፣ አንቂዎችን ወዘተረፈ ለሁለት ፣ ለሶስት ፣ ለአራት እያደረጉ የመከፋፈልና በራሳቸው ዛቢያ እየተሽከረከሩ ሲተረማመሱ እንዲሰነብቱ የማድረግ ትልቅ ፕሮጀክት ተፈፃሚ እየሆነ ነው!

ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ ፣ ቢያስከፉሽ አይክፋሽ!

ደሞ ለእንዳንቺ አይነት ፤ ግብር አመድ አፋሽ!

Filed in: Amharic