>

አቶ ስንታየሁ ቸኮል በኦሮምኛ ተናጋሪ ሰላዮች መታፈኑ ተረጋገጠ !

አቶ ስንታየሁ ቸኮል በኦሮምኛ ተናጋሪ ሰላዮች መታፈኑ ተረጋገጠ !


የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) የአደረጃጀት ጉዳዮች ሓላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ከአዲስ አበባ ለዚሁ ተግባር ከቤተ መንግሥት ስምሪት ተቀብለው በመጡ ኦሮምኛ ተናጋሪ የመንግሥት የስለላ ሠራተኞች ባሕር ዳር ከተማ ውስጥ መታፈኑ ተረጋግጧል። አቶ ስንታየሁ በአሁኑ ጊዜ በባሕር ዳር ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት፤ አቢሲንያ ባንክ አጠገብ በሚገኘው 1ኛ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ ይገኛል። በዚህ የታሰረው በአደራ እንደሆነ እና ወደ አዲስ አበባ እንደሚወስዲት አፋኞቹ የነገሩት መሆኑንም ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ.ም. በእስር ቤቱ ተገኝተው ለጠየቁት የውቢቷ  ባሕር ዳር ከተማ ኗሪዎች ተናግሯል።
እስር ቤቱ አስቀድሞ አክቲቪስት ቲና በላይ የታሰረችበት ሲሆን ከአቶ ስንታየሁ ቸኮል።ጋርም በርቀት ተገናኝተዋል።
ስንታየሁ ባልደራስ ወደ ሀገር አቀፍ ፓርቲነት የሚያደርገውን ጉዞ ተከትሎ፤ የድጋፍ ፊርማ የማሰባሰብ ንቅናቄውን ለመምራት አስቀድሞ ባሕር ዳር መግባቱ ይታወቃል።
Filed in: Amharic