>

አሮጌው የአምባገነኖች ስልቻ በአዲስ የአምባገነኖች የማይጠረቃ ስልቻ ተተክቷል...!!! (ምኒልክ ሳልሳዊ)

አሮጌው የአምባገነኖች ስልቻ በአዲስ የአምባገነኖች የማይጠረቃ ስልቻ ተተክቷል…!!!

ምኒልክ ሳልሳዊ


ተረኞቹ አምባ ገነኖች እንደ አባታቸው አፈናውን፣ ግድያውን፣ ማሳደዱን፣ ቤተሰብን ማሰቃየትን፣ እስሩን፣ ወዘተ ቀጥለውታል።

የበርካቶች ተስፋ የጨለመበት፣ ከሐገር አልፎ አሕጉርንና አለምን ያስደመሙ የኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት የተበተነባት፣ ምሁራን የተገፉበት፣ ለሐገርና ለወገን የሚጠቅሙ የተገደሉባት የተሰደዱባትና ዘረኞችና አናሳ የአፓርታይድ ስርዓት አራማጆች ስልጣን በጠበንጃ የጨበጡባት እለት ናት። ሕወ. ሓት/ኢሕአዴግ/ብልፅግና ስማቸውን እየቀያየሩ በሕዝብ አናት ላይ የሚዘፍኑባት አገር የተፈጠረችው በዛሬው እለት ነው። ይህ የሕወ።ሓትን ሌጋሲ ብልጽግናም አስቀጥሎታል

ዛሬ ላይ ቆመን የምናያቸው የሌጋሲው አስቀጣዮች ሐገርን ለማተራመስ አመጽ የሚሰብኩ፣ ፖለቲካውን በዘር የሚለኩ፣ ቢሮክራሲውን በጎጥና በብሔር የሞሉ፣ ቅድሚያ ለዜጎች ሳይሆን ለዘር የሚሰጡ፣ አደርባዮች፣ የአፓርታይድ አራማጆች፣ የሚናገሩትና የሚያደርጉት የተለያየ የሆኑ ባለስልጣኖች። አስመሳዮችና በወሬ የሚደልሉ ታሪክ አጥፊዎች፣ የፖለቲካ ደላሎችና የአዞ እንባ አፍሳሾች፣ ያዘኑ መስለው ሕዝብን የካዱ ውርጃዎች የግንቦት ሃያ ፍሬዎች ትሩፋቶች ናቸው።

–በግንቦት 20 ኢትዮጵያ አገራችን በጨለማ ጉም ተሸፈነች:: አገርና ህዝብ ጥቁር የሃዘን ልብስ ለበሱ:: ሲጠሏት እና ታሪኳን እና ህዝቧን ሲያዋርዱን ሲያንቋሽሹ በነበሩት ወያኔ ህወሃት ለእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ተዳረገች:: ዘረኛው እና ጎጠኛው ወ,ያ ኔ ህወ,ሃት በመለስዜናዊ የሚመራው የማ,ፍያ ፋሺ,ስት ግልገል እና ግብረ አበሮቹ ጸረ ሀገር እና ጸረ ህዝብ የሆኑትን ለዘመናት የተከበረው የምኒሊክ ቤተ መንግስት ተቆጣጥረው የግልገል ፋሺ,ስቶች መንደላቀቂያ ሆነ::

ህወ. ሃት ከደደቢት ይዞት የመጣውን ህገ ደንቡን የኢትዮጵያ ህገ መንግስት አደረገው:: ኢትዮጵያን በዘር ፣ በቋንቋ እና በሃይማኖት ከፋፍሎ የህዝቡን አንድነት እና ኢትዮጵያዊነት አጠፋዋለሁ ብሎ ያመጣውን የዘረ,ኝነት ህጉን በኢትዮጵያ ዘረጋ:: አሮጌ የአምባገነኖች ስልቻ በአዲስ የአምባገነኖች ስልቻ የተተካበት። ወታደራዊው ደርግ ሲሞት ወን,በዴው ደርግ የተወለደባት ቀን ግንቦት ሐያ። ትልቅ የፖለቲካ የኢኮኖሚና የማሕበራዊ ኪሳራ በሀገር ላይ ያደረሱ ጸረ ኢትዮጵያ ኃይሎች ስልጣኑን የተቆናጠጡበት እለት ግንቦት 20።

Filed in: Amharic