>

ከአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የተሰጠ መግለጫ!!

ከአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የተሰጠ መግለጫ!!


*…. በልመና የተገኘ ነፃነት የለም!! በልመና ነፃ የወጣ ህዝብ አይኖርም !! ጠላትህን አስፈቅደህ የምትታገለው ትግል አይኖርም። በመቆዘም የተከበረ ማንነት የለም።

ሁሉም አማራ በሚኖርበት አካባቢ ሁሉ ሀገሩንና ወገኑን መጠበቅ አለበት። ጠላት ሊበጣጥሰው የማይችል መረብ መዘርጋት አለበት። የሰላም ሆነ የችግር ደወል ከተሰማ በየ አደረጃጀትህ ዕዝ ሰንሰላት ውስጥ መገኘት እንዳለብህ በንቃት ጠብቅ።

በልመና የተገኘ ነፃነት የለም!! በልመና ነፃ የወጣ ህዝብ አይኖርም !! ጠላትህን አስፈቅደህ የምትታገለው ትግል አይኖርም። በመቆዘም የተከበረ ማንነት የለም።

እስካሁን የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች አንዱ እንኳን አልተመለሰም። እነዚህ ጥያቄዎች ደም ፈሶባቸዋል!!  የጥያቄ ካርድ ከፍ አድርገን እንመዛለን። ለምን የተነሳንበት የህዝብ ጥያቄ ስለሆነ!!

የህዝብ መከታና የሀገር በለውለታ የሆነውን ፋኖ መነካካት ለኢትዮጵያ አይጠቅምም!! አሁን እያስተዋልነ ያለው የመንግስት አቋም ህዝብን ግራ የሚያጋባ ነው። ኢትዮጵያን የሚያሻግር ሳይሆን የትርምስ ቀጠና መሆን የምትችልበት አጋጣሚ ለመፍጠር አጉል ስብሰባዎች በዝተዋል!!

ጠላትህን ታውቃለህ!! አሁንም የተኛልህ አይምሰልህ !! ይልቁንስ በሎጂስቲክ ተጠናክሮ ጥላቻውን ከፍ አድርጎ ተሰልፏል። በተላይ አማራውን ለማዋረድ እየተመከረ ነው።

ጠላትህ ስራውን እየሰራ ባለበት ሁኔታ አንተ የማንንም ፈቃድ ጠባቂ ከሆንክ እየታገልክ አይደለም። የጠላትን ሙሉ መረጃና ማስረጃ እየተከታተልክ መዘጋጀት ካልቻልክ የሃይል ሚዛንህ ይወርዳል።

ለማንኛውም ሀሰተኛ ታርጋ እንደተዘጋጄልህ እወቅ። በመጀመሪያ ራስህን ነፃ ለማውጣት ታገል። አሁን እንተ ምን ላይ እንዳለህ አስበህ ግምገማሃን ገምግም። አዋጭነት የምትለውን የትግል መስመር አስምር!! መስመርህን ጠብቀህ በቁርጠኝነት ተጓዝ!!

ከዋትሳፑ መልእክት በተጨማሪ፡ አማራ ከእንግዲህ በማልቀስ የሚቀጥለው ትግል አይኖርም።ቀጥታ የአማራ ፋኖ ትግል ቤተ መንግስቱን ለመረከብ ብቻ ነው።ከዚህ የትግል አጀንዳ እና ግብ ማንም እንዲወርድ አይፈቀድም።ከእንግዲህ መፍትሔው ስልጣን ይዞ ሀገር መምራት ብቻ ነው።ለዚህ አላማ እና ግብ የማይታገል አማራ ለጠፍ ተሸካሚ ሆኖ የሚቀጥል ከሆነ የራሱ ጉዳይ ነው።ስለዚህ።የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ሰራዊት፡የትግል መዳረሻውን ወስኗል።የትኛውም አጋራችን እንዲያውቀው የምንፈልገው ያለምንም ይሉኝታ ፋኖ፡የአባቶቹን ቤተመንግስት መልሶ ስለመረከብ ይታገላል።የትኛውም ጉዞ የትኛውም እንቅስቃሴ ሁሉ ይህንን ማእከላይ የግብ ነጥብ ጠብቆ ለግቡ ስኬት የሚያግዝ እንዲሆን ይሰራል።

ይህ ግብ እጅግ ሚስጥራዊ እና ለጊዜው ለህዝብም ሆነ ለሚዲያ ይፋ የማይሆን በጥቂት ሰወች ጠባቂነት እና አመራርነት።የሚያዝ ነው።በየትኛውም አቅጣጫ የሚደረጉ የአማራ ህዝብ ማህበራዊ፡ኢኮኖሚያዊ፡እና ፖለቲካዊ ትግሎች መዳረሻ ነጥባቸው አንድ ወሳኝ ግብ ብቻ ነው።አማራ ስልጣኑን መረከብ አለበት።ካለበለዚያ ዘላለም ሙሾ አውራጅ ከመሆን አይድንም።

ይህ የላእላይ አስተባባሪወችም ሆነ የቁርጠኛ ታጋይ ፋኖ ሰራዊቱ ግልፅ አቋም ነው።( ይህንን እንደ አጋርነታቹህ እንድታውቁት ነው።) የአማራ ፋኖ ከእንግዲህ ለራሱ አላማ ለራሱ ራእይ እና ለራሱ ግብ እንዲሁም ሰፊው የአማራ ህዝብ የጣለበትን አደራ እና ሀላፊነት መዝኖ ይጓዛል እንጅ።የማንም የፖለቲካ ለጠፍ ተሸካሚ ሆኖ ማንም የመጣ የሄደው ሁሉ እንደ ጠፍ አህያ የሚጭነው አይደለም።

ፋኖ የአማራን ህዝብ ከረገጠው አውዳሚ ስርአት በፅኑ ተጋድሎ ነፃ በማውጣት ታሪካዊ አደራውን ብቻ ይወጣል።ከእንግዲህ ማንም በፋኖ ላይ አጀንዳ ሊጭንበት አይችልምም!!!!

አሻራ ሚዲያ

Filed in: Amharic