የአገሪቷ ቀውስ ስር እየሰደደ ነው፤ የብልፅግና መንግስት አልቻለም….!?!
ግርማ ካሳ
*… ካለንበት ቀውስ መውጫ ቀዳዳ ካልተፈለገ አሁን ባለንበት ሁኔታ መቀጠል አንችልም፤ በመሆኑም ገዢው የብልፅግና ፓርቲን ያካተተ የሽግግር መንግስት ያስፈልጋል…!!!
የሽግግር መንግስቱ ምን መልክ ይኑረው ለሚለው የተለያዩ ሃሳቦች ሊኖሩ ችላሉ:: የሚከተለው አንድ አማራጭ ሊሆን ይችላል ብዬ ባለ አስራ ሶስት ነጥቦችን አስቀምጫለሁ::
1ኛ 43 አባላት ያሉት ጊዚያዊ ምክር ቤት ይመሰረታል:: በሚከተለው ቀመር የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካይች ይልካሉ:: ገዢው የብልፅግና ፖርቲ አንድ ሶስተኛውን መቀመጫ ይይዛል:: የፖለቲካ ፖርቲዎች ብቻ ያካተትኩት ነገሮች ሊቀላጠፊ ይችላሉ ከሚል ነው:: የሲቪክ ማህበራት የሃይማኖት ድርጅት ወዘተረፈ እየተባለ ፕሮሰስ ማብዛት ነገሮችን ማጏተት ነው የሚሆነው::
15 ከብልፅግና ፓርቲ
2 ከኦነግ
2 ከኦፌኮ
2 ከህወሃት
2 ከአብን
2 ከኢዜማ
2 ከህብር
2 ከመኢአድ
2 እናት
2 ነፃነት
2 ኢሶዴፖ
2 ባልደራስ
2 አረና
2 ኦብነግ
2 አዴሃን
2ኛ ዶር አብይ አህመድ ይለቃል:: ጡረታ ይወጣል::
3ኛ ከምክር ቤቱ አባላት ለአንድ አመት ጠቅላይ ሚኒስትር ይመረጣል:: በየአመቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ይቀየራል::
4ኛ ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትር አቅራቢነት ካቢኔ ይመሰርታል:: የካቢኔ አባላት ከምክር ቤት ውጭ በብቃትና በሞያ ይሰየማሉ:: ከአንድ አመት በላይ ሊያገለግሉ ይችላሉ::
5ኛ ጊዚያዊ መንግስቱ ከሶስት አመት በላይ አያገለግልም::በሶስት አመት ውስጥ ምርጫ ያደርጋል::
6ኛ ፖርላማውና የክልል ምክር ቤቶች ይፈርሳሉ:: በዞን ያሉ ምክር ቤቶችና አስተዳደሮች እንዲቀጥሉ ይደረጋል::
7ኛ የክልል ልዩ ሃይሎች በአገር መከላከያ ስር ሙሉ ለሙሉ እንዲጠቃለሉ ይደረጋል::
8ኛ የፌዴራል የመንግስት መግባቢያ ቋንቋ አማርኛ ሆኖ ይቀጥላል:: ሁሉም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የፌዴራል የስራ ቋንቋ ይሆናሉ:: ዜጎች በሚናገሩት ቋንቋ መንግስታዊ አገልግሎት የማግኘት መብታቸው ይጠበቃል::
9ኛ በሁሉም አገሪቷ አማርኛና እንግሊዘኛ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እንደ ትምህርት ይሰጣል::ሶስተኛ ቋንቋ ወላጆች የመረጡት ይሁን የወረዳ የዞን አስተዳደር የመረጡት በግዴታ ይሰጣል:: ሶስተኛ ቋንቋው የአገር ውስጥ ወይንም የውጭ አገር ቋንቋ ሊሆን ይችላል::
10ኛ ጊዜያዊ መንግስቱ በአገሪቱ መረጋጋት እንዲመጣ መፈናቅሎች ግድያዎች እንዲቆሙ ዜጎች በነፃነት በሁሉም የአገሪቷ ክፍል መንቀሳቀስ እንዲችሉ ማድረጉ ላይ ተቀድሚው ስራው ይሆናል::
11ኛ ፍርድ ቤት: መከላከያ: ፖሊስ: የመንግስት ሜዲያ: ምርጫ ቦርድ ገለልተኛ ሆነው እንዲዋቀሩ ያደርጋል::
12ኛ ፍትሃዊ በሆነ መልኩ የህዝብ ቆጠራ ያከናውናል::
13ኛ የህገ መንግስት ማሻሻያ ምክክሮች ያደርጋል:: አዲስ ህገ መንግስት እንዲረቅ ወይም ያለው እንዲሻሻል ያደርጋል::