“በዚህ ክፉ ዘመን ዝም ማለት ፤ ለህዝብ አለመጮህ የአማራን ህዝብ እንደ መክዳት ይቆጠራል!!!”
ሊቀ ሊቃውንት አባ ወልደ ትንሣኤ አባተ
*…. አማራ የዮድት ጉድትን የአርባመት የግራኝ አህመድን የአስራ አምስት አመት የጣልያንን የአምስት አመት ወረራ ተቋቁሞ ሲታገል የነበረ ኢትዮጵያ ከጥላት የጠበቀ ህዝብ ሁኖ እያለ ሀገር በቀል በምስለኔ የተወከለው ብአዴን ከግራኝም ከጉድትም ከጣልያንም የበለጠ ጭብጨፋ ወረራ ጌቶቹን ለማስደሰት በአማራ ህዝብ ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው በደል ፈፅሟል
ሂትለር በአይሁድ ህዝብ ላይ ጦርነት እንዳዎጀ ሁሉ አቢይ አህመድ አሊ በአማራ ህዝብ ላይ ግፍና በደል ጭፍጨፋ የበለጠ መከራ ህግ ማስከበር በሚል ውሃ የማይቋጥር ተልካሻ ምክንያት በመፈረክ በአማራ ህዝብ ላ አፈና እየፈፀመ ይገኛል። ዓለም በሰለጠነበት በዚህ በሃያ አንደኛው ክህፍለ ዘመን ላይ የሶስት ዓመት ህፃን በማፈን የ13 ዓመት ታዳጊ በጥይት በመግደል በሀገር እና በህዝብ ላይ ጦርነት ማወጅ ሂትለራዊነት ነው።
የአማራ ህዝብ ኢትዮጵያ ተወረረች ሲባል ሀብቱን ንብረቱን ሚስቱን ጥሎ ለእናት ሀገሩ ራሱን ሲገብር የኖረ ኢትዮጵያን ጥላት እንዳይደፍራት ያደረገ ሀገር ያስከበረ የሀገር ባለውለታ ኩሩ ህዝብ ነው ።
ላለፉት ሶስት አስርት አመታት በሀገር በቀል ጥላት እየተጨፈጨፈ ከኖረበት ሀገሩ ሀገርህ አደለም ውጣ እየተባለ ጥሩ ግሮ ያፈራውን ንብረቱን እየተነጠቀ በምድር ላይ የመኖር መብት ተነፍጎት ምድር ገሃነም ሁናበት የራሱን ሀገር እየረገመ በእየጎዳናው ወድቆ እጆቹን ወደ ፈጣሪ ዘርግቶ በምድር ላይ ያለችው የፍትህ ደጅ ስለተዘጋችበት ፍትህን ከፈጣሪው ጠይቆ ይግባኙን ከክርስቶስ ዘንድ እየጠበቀ ይገኛል።
አማራ የዮዲት ጉዲትን የአርባመት የግራኝ አህመድን የአስራ አምስት አመት የጣልያንን የአምስት አመት ወረራ ተቋቁሞ ሲታገል የነበረ ኢትዮጵያ ከጥላት የጠበቀ ህዝብ ሁኖ እያለ ሀገር በቀል በምስለኔ የተወከለው ብአዴን ከግራኝም ከጉድትም ከጣልያንም የበለጠ ጭብጨፋ ወረራ ጌቶቹን ለማስደሰት በአማራ ህዝብ ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው በደል ፈፅሟል።
ላለፉት ሶስት አስርት አመታት በሀገር በቀል ጥላት እየተጨፈጨፈ ከኖረበት ሀገሩ ሀገርህ አደለም ውጣ እየተባለ ጥሩ ግሮ ያፈራውን ንብረቱን እየተነጠቀ በምድር ላይ የመኖር መብት ተነፍጎት ምድር ገሃነም ሁናበት የራሱን ሀገር እየረገመ በእየጎዳናው ወድቆ እጆቹን ወደ ፈጣሪ ዘርግቶ በምድር ላይ ያለችው የፍትህ ደጅ ስለተዘጋችበት ፍትህን ከፈጣሪው ጠይቆ ይግባኙን ከክርስቶስ ዘንድ እየጠበቀ ይገኛል።
በዘመነ ወያኔ ተላላኪ ሁኖ በሀገር መከላክያ ሰራዊት የታገዘ ጥቃት በብአዴን አስተባባሪነት ለሰላሳ አመት ያክል አማራ ሀገር አልባ ሁኖ የተናቀ ትቢያ ሁኖ ለሀገር የከፈለው ውለታ እንደመርገም ጨርቅ ተቆጥሩ እየተሳደደ ሲገደል ኑሯል የአማራ ህዝብ ለፍትህ ሲል በመንግስት ወታደር የታገዘ ጭፍጨፋ ከጎርጎራ እስከ ወገራ ከባህርዳር እስከ ወልድያ ራያ መርሳና በተለያዩ በጎንደርና በጎጃም በወሎ በሸዋ ከፋኝ ብለው ዱር ገብተው ሲዋጋ ኑሯል። ለዚህም በረሃ የቀሩት እነጎቤ መልኬ የነፃነት ታጋይ ስለ ፍትህ የሞቱ አርበኞች ህያው ምስክር ናቸው። የነጎቤን ትግል ወስዶ ራሱን የለውጥ አካል አድርጎ በወንድሞቻችን ደም ላይ ተረማምድ ዛሬም ከስልጣን ላይ ፊጢጥ ያለው ሲጠሩት አቤት ሲልኩት ወደየት የሚለው ብአዴን የምኒልክን ሂሳብ እናዎራርዳለን ብለው በተነሱ የሀገርና ይህዝብ ጠላት በሆኑ ሀገር ጠል ባለስልጣናት ትዛዝ ብአዴን ህዝባችን እየጨፈጨፈ እያረደ ይገኛል ። ይህ ገዳይ እና አፋኝ ቡድን በቃህ ካልተባለ የአማራ ህዝብ
ሰቆቃ እስከ አሁን ከነበረው የከፋ ይሆናል። የአማራ ህዝብ እየሞተ መኖሩን አቁሞ ሁሉም ለትግል መዘጋጀት ይኖርበታል ። ብአዴን ከወያኔ ጋር አብሮ ኤርትራ እንድትገነጠል ያደረገ ኢትዮጵያ ባህር አልባ እንድትሆን የፈረመ ከመጣው ሁሉ ጋር የሚያጨበጭብ ሀገር አፍራሽ የማይጠቅም በደም የተነከረ የአማራን ልጆች ቢበላ የማይይጠግብ ስብስብ ነው። ትናት ከራያ እስከ ጉና ከሰቆጣ እስከ ሞላሌ ከማይፀብሪ እስከ ዳባትና ደባርቅ ድረስ አማራን ያስወረረ እናቶቻችንን እህቶቻችን ያስደፈረ ጠላት ሀገር ሲወር ሀብት ሲከፋፈል የነበረ ድርጅት ነው። ዛሬ ህግ አስከባሪ ሁኖ ለህዝብ ድምፅ የነበሩ ጋዜጠኞችን እና ለሀገር ለህዝብ በጨበጣ ሲዋጋ የነበረውን ፋኖን እያፈነ እና እያሳደደ ይገኛል። ይህን እንደስስታዊ ባህሪ ያለው በየደቂቃው የሚቀያየር እንደ መቃብር ድንጋይ ህዝባችን የተጫነ ዘራፊ ድርጅትና የወሮበሎች ስብስብ ስለሆነ አምርረን ልንታገለው ይገባል። 1986ቱን የኢህአዴግ መርህ በመከተል በህግ እናስከብራለን ሽፋን አማራን ነፍጥ በማስፈታት የአማራን አንገት ማስደፋት ስለሆነ ከፋኖ ጎን ልንቆም ይገባል ።
ይህ ካልሆነ አማራ የአብይ አህመዱ ብልፅግና ተላላኪ እና ባርያ ሁኖ ተንቆ እንደትቢያ እየተረገጠ ይኖራል። ከብአዴን ኮፈን የምንወጣበት መንገድ በትግላችን ማምጣት አለብን ። ከባርነት ነፃነት ይሻለናል። ኢትዮጵያ ስንሮር በፍቅር የምንኖርባት ሀገር እንጅ በቁማችን ፍትህን ነፍጋን ስንሞት መቃብር ከልክላን የምንኖርባት ምድር የግዞት ሀገራችን አይደለችም ። አሁን ያለችው ኢትዮጵያ ለአማራ ህዝብ ገሃነም ሁና የአማራ ተወላጆችን በመከራ በሲኦል ባህር ውስጥ ልታሰጥመው እየጣረች ትገኛለች። አማራ ንቃ አማራ ንቃ አማራ ንቃ ፍትህ ለወገኖቻችን ፍትህ በለለበት ዓለም ውስጥ አንዱ መሪ ሌላው ተመሪ ሁነን አንቀጥልም።
ህይዎቴን እስከ መስጠት ድረስ ከፋኖ ጎን እሰለፋለሁ ። ፋኖነት የኢትዮጵያ የነፃነት አርማና ምልክት ነው።