>

የባልደራስ አመራሩ ስንታየሁ ቸኮል መልዕክት ከባሕር ዳሩ እስር ቤት፦ (ጌጥዬ ያለው)

የባልደራስ አመራሩ ስንታየሁ ቸኮል መልዕክት ከባሕር ዳሩ እስር ቤት፦

ጌጥዬ ያለው


የታፈንነው ከአዲስ አበባ በመጡ የኦሮሞ ፖሊሶች ነው። ለእግዚአብሔር እንኳን አፋቸው ቋንቋን ለመናገር የሚፀየፉ አፋኞች ናቸው። እነዚህ የመንግሥት ኃይሎች በGPS በመጠቀም ያረፍኩበት ክፍል ድረስ መጥተው ነው ያፈኑኝ። አሁን በታገትኩበት የባሕር ዳር 1ኛ ፖሊስ ጣቢያ ያሉ ፖሊሶች ለምን ምክንያት እንደታገትኩ አያውቁም። ከላይ በመጣ ትዕዛዝ “ጠብቁ” ተብለዋል። ምናልባት ነገ ወይም ከነገ ወዲያ ወደ አዲስ አበባ ወይም ወደ ሌላ ቦታ ሊወስዱኝ ይችላሉ።

በዋናነት እዚህ ያመጣኝ የአዲስ አበባው ስውር መንግሥት ነው። ይህንን ሕዝቡ ሊያውቅ ይገባል። በተለይ የአማራ ሕዝብ ይህንን በመገንዘብ በነቂስ ወጥቶ ህልውናውን ማስቀጠል አለበት። ምክንያቱም ይህ ሁሉ አፈና የእርሱን ህልውና ያለ ሃይ ባይ ለማጥፋት ነው።

ከፈጣሪ ቀጥሎ ሃይላችሁ፤ ትክሻችሁና ጉልበታችሁ መሆኑን አውቃችሁ በነቂስ እንድትወጡ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።

ስልኬን ሰብረውታል። ትግሉ ይቀጥላል!

ግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ.ም.

ባሕር ዳር 1ኛ ፖሊስ ጣቢያ

Filed in: Amharic