ኦህዴድና ሕወሃት “ግንባር” ፈጥረው ነው የሚንቀሳቀሱት …!!!
ግርማ ካሳ
*… ኢንጅነር ይልቃል * ፋኖን ማጥፋት የተፈለገው የአማራን ጥቅም የሚጋፋ ድርድር ማድረግ ስለታሰበ ነው” ይላል ። እኔ ግን ትንሽ እርሱ ያለውን ለማሻሻል:: ድርድር መጀመር ሳይሆን ጨርሰውታል:: እነ አብይ እህመድ ስምምነት አድርገዋል:: የተስማሙበትን ተግባራዊ ለማድረግ በቅንጅትና በእቅድ ጊዜውን እየጠበቁ እየሰሩ ነው እላለሁ.!!
አንድ ሜዲያ ላይ አንድ ጥያቄ ቀረበለኝ፡፡ “አሁንም ሕወሃት ነው ዋና ጠላታችን ፣ ቅድሚያ ህወሃት ላይ ነው ማድረግ ነው ያለብን፤ ከኦህዴዶች ጋር ያለው ችግር ለነገ ማሳደር ያስፈለጋል ይላሉ አንዳንዶች፣ አንተ ምን ትላለህ ? ” ተብዬ፡፡
“ኦህዴዶች ከሕወሃት ጋር ተደራድረው ስምምነት አድርገዋል፡፡ ያኔ ሕወሃት ከኦነግ ጋር ነበር ቅንጅት ፈጥሮ እንደ አንድ ግንባር ሲዋጋ የነበረው፡፡ አሁን ህወሃትና ኦህዴድ ስምነት አድርገዋል። ቅንጅት ፈጥረዋል የሚል እምነት ነው ያለኝ፡፡ ስለዚህ የአብይ አህመድ ጦር የሕወሃት አንድ እዝ ጦር አድርጌ ነው የማያቸው፡፡ ስለሆነ ኦህዴድም ሕወሃትም አንድ ናቸው” የሚል መልስ ነው የሰጠሁት፡፡
አንድ ባይሆኑ ኖሮ የአብይ አህመድ የኦህዴድ/ብልጽግዎች ሕወሃት ኃይሏን እያጠናከረች ባለበት ጊዜ ህወሃትን ሲፋለሙ የነበሩ ፋኖዎች ላይ ጦርነት አይከፍትም ነበር፡፡
# የህወሃት አመራሮችን እነ ስብሃት ነጋን ሲፈቱ፣ ህወሃትን ሲታገሉ የነበሩ እነ ጀነራል ተፈራ ማሞን አያስሩም ነበር፡፡
እዚህ ጋር አንድ ነገር ላስምርበት፡፡ ሁለቱም አንድ የሚያደርጋቸው ነገር አለ፡፡ አማራውን እንደ ጠላትና እንደ ስጋት ነው የሚያዩት፡፡ አማራው ከተመታ ወያኔዎች እነ ወልቃይትንና በርካታ የወሎ መሬቶች ይይዙና ታላቂቷን ትግራይ ለመመስረት እድል ይኖረናል የሚል ሃሳብ አላቸው፡፡ ኦህዴዶች ደግሞ አዲስ አበባን እየሰለጠቁ፣ አማራውን ከተዳከመ፣ የኦሮሙማ አጀንዳቸውን ያለ ምንም ተቀናቃኝ እናስቀጥላለን ይላሉ፡፡