የጎሰ ፖለቲከኞች በህዝብ ቆዳ ዉስጥ የመደበቅ ጥበብ.. ..!!!
ሸንቁጥ አየለ
*…. የጎሰኛ ፖለቲከኞች በህዝብ ቆዳ ዉስጥ የመደበቅ ጥበብ በጣም ተጠበዉበታል:: ኦህዴድ ሲተች ኦሮሞ ተተች: ህዉሃት ሲተች ትግሬ ተተቸ:ብአዴን ሲተች አማራ ተተቸ እያላችሁ ሁሌም በህዝብ ቆዳ ዉስጥ ለመወተፍ የምትራወጡ ዘረኞች ከህዝባዊ ፍርድ አታመልጡም::
ተመስገን ደሳለኝ ኢትዮጵያዉያንን በሙሉ ያከብራል::ማንንም ህዝብ ተሳድቦ አዋርዶ አያዉቅም::የሚተቸዉም የሚወቅሰዉም በህዝብ ላይ ግፍ የሚሰሩትን ህዉሃታዉያንን:ኦህዴዳዉያንን እና ብአዴናዉያንን ነዉ::
ሆኖም የኦህዴድ ካድሬዎች ተመስገን “በእስር ቤት ሳለ መደብደቡ ልክ ነዉ::ህዝብ ይሳደባል::የተመስገን አይነት ጋዜጠኛን የሚዳኘዉ ዱላ ብቻ ነዉ” የሚል ሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳ ይዘዉ መጥተዋል::
የጎሰኛ ፖለቲከኞች በህዝብ ቆዳ ዉስጥ የመደበቅ ጥበብ በጣም ተጠበዉበታል:: ኦህዴድ ሲተች ኦሮሞ ተተች: ህዉሃት ሲተች ትግሬ ተተቸ:ብአዴን ሲተች አማራ ተተቸ እያላችሁ ሁሌም በህዝብ ቆዳ ዉስጥ ለመወተፍ የምትራወጡ ዘረኞች ከህዝባዊ ፍርድ አታመልጡም::
ይሄን እዉነታ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠንቅቆ ያዉቃል::ኦህዴድ የኦሮሞን ህዝብ አይወክልም::ህዉሃትም የትግሬን ህዝብ አይወክልም::ብአዴን የተባለ እሥስትም የአማራን ህዝብ አይወክልም::
እነዚህ የጎሳ ፖለቲካ ፓርቲዎች የዬነገዳቸዉም ሆነ የአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ካንሰር በሽታ ናቸዉ እንጂ የትኛዉንም ህዝብ አይወክሉም::