>

የጃዋርና የተመስገን ኢትዮጵያ....!!!! (ዮሴፍ ታደለ)

የጃዋርና የተመስገን ኢትዮጵያ….!!!!

ዮሴፍ ታደለ


የኦባንቱ ጋዜጠኛ፦ በእስር ቤት የነበረህ ቆይታ ምን ይመስል ነበር? 

ሃጂ ጃዋር መሀመድ፦ በእውነቱ ልዩ ነበር። ፖሊሶቹም፣ የፖሊሶቹም አለቆች ተንከባክበው ነው የያዙን። በቋንቋም እንግባባ ስለነበረ በሚገባ ነበር ይረዱን የነበረው። ምግብ አንበላም ብለን የረሃብ አድማ ባደረግን ጊዜ እንኳ ፖሊሶቹ በጣም ተጨንቀው እያለቀሱ ምግብ እንድንበላ ሲማጸኑንና ሲለምኑን ነበር። ላፕቶፕ፣ የእጅ ስልክ ሁላ ሰጥተውን እኔ ራሱ ለባለቤቴ አሜሪካ ድረስ በየቀኑ እንድደውል ያደርጉን ነበር። ዋይፋይ ነበረን። ወዳጅ ዘመድ ጠያቂም ውስጥ ድረስ ገብቶ እንዲጠይቁን ያደርጉ ነበር። ከእስር ስንፈታ ራሱ ስቅስቅ ብለው ያለቀሱ ፖሊሶች አሉ።

“…ዛሬ ግንቦት 25/2014 ዓ.ም የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ ወንድሙን ለመጠየቅ በተለምዶ 3ተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተብሎ ወደሚታወቀው ዝነኛ እስርቤት ይሄዳል። እዚያም እንደደረሰ ወንድሙን ያስጠራና ለማነጋገር ይሞክራል። በዚህ እስር ቤት በታሳሪና በጠያቂ መካከል በሁለት ሾቦ የተጋረደ ከ10 ሜትር የሚበልጥ ርቀት ስላለ በታሳሪና በጣያቂ መካከል ንግግር ለማድረግ እጅግ አዳጋች ነው። አጠቃላይ ነገሩ መጯጯህ ነው ይላል ታሪኩ። መጥፎው ነገር ደግሞ ተመስገን ከዚህ በፊት በእስር ቤት እያለ ባጋጠመው በጆሮ ህምም ምክኒያት በዚህ ግር ግር ውስጥ ጆሮው ለመስማት ያዳግተዋል።

“… በዚህ ምክንያት ጋዜጠኛ ተመስገን ለፖሊሶቹ “ትንሽ ቀረብ ብሎ ቢያወራኝ ” በማለት በትህትና መጠየቅ፣ ፖሊሱም በእጁ የማመናጨቅ ምልክት ማሳየት፣ ተመስገንም ድጋሜ ለማስረዳት ሲሞክር አንዱ ፖሊስ ከነበረበት ከጠያቂ ቦታ ሌላው ፖሊስ ከእስረኛቹ መቆሚያ ደረጃ ላይ በመውረድ ለሁለት ተመስገንን አብረውት ከቆሙት እስረኞች መካከል ጎትተው በማውጣት በቦክስ፣ በጫማ ጥፊ፣ በካልቾ ለሁለት ይደበድቡታል። ይህ ሲሆን የሌሎች እስረኛ ጠያቂ ቤተሰቦችና እስረኞችም አይተዋል። ድብደባውን እየፈፀሙ ወደ እስረኛ ክፍል ሳይሆን ወደ ሌላ ቦታ ይዘውት ይሄዳሉ።

“…ከቆይታ በኋላ በቢሮ ውስጥ ተመስገንን ስናገኘው የግራ ዓይኑ ስር አብጦ የለበሰው ቲ-ሸርት ተቀዶ አግኝተነዋል። አሁን ከእስር ቤቱ  አስወጥተውኝ በሩ ላይ እገኛለሁ ሲል በፌስቡክ ገጹ ላይ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና ሚዲያዎች ጉዳዮን እንድታውቁልን በማለት አስፍሯል።

https://youtu.be/g2KAOXrNRKg

Filed in: Amharic