>

በሀገረ~ እስራአኤል በኢትዮዽያ የሚፈፀመውን አፈና የሚቃወም ሰልፍ ተደረገ !!

ሁለት የባልደራስ አባላት ታፍነው አድራሻቸው ጠፋ!!

ባልደራስ

በሀገረ~ እስራአኤል በኢትዮዽያ የሚፈፀመውን አፈና የሚቃወም ሰልፍ ተደረገ !!


ሁለት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አባላት ካለፈው ግንቦት 17 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ፤ ማለትም እስከ ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ የት እንደታፈኑ ማወቅ አልተቻለም።

የታፈኑት ወጣቶች ዘገየ በቀለ እና ዳምጤ ተቃጫ ናቸው። ዘገየ ባለፈው የ2013ቱ ሀገራዊ ምርጫ ባልደራስን ወክለው ለአዲስ አበባ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ከተወዳደሩ ዕጩዎች መካከል አንዱ ሲሆን አዲስ አበባ፤ የካ አባዶ በሚገኘው የአጎቱ መኖሪያ ቤት አቅራቢያ ነው የታፈነው። አጎቱ አቶ ይትረፍ ድንበሩም አብረው እንደታፈኑ የደረሱበት አለመታወቁን ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ወጣት ዳምጤ ከ9 ቀናት በፊት ከቤት እንደወጣ አለመመለሱን ቤተሰቦቹ አረጋግጠዋል።

ቤተሰቦቻቸው አሁንም ድረስ በየፖሊስ ጣቢያው እየተመላለሱ ቢጠይቁም ሊያገኟቸው አልቻሉም።

ይህ በአንዲሀ‍ እንዳለ፣ በእስራኤል የሚኖሩ ኢትዮዸያዊያን በኢትዮዸያ የሚፈፀመውን አፈና ፣ ማሳደድድና የዘር ማፅዳት በመቃዎም ዛሬ አርብ፤ ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም. የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል።

ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፉ የተደረገው ቴልአቪቭ ከተማ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በር ላይ ላይ ነበር።

መፈክሮች ከአማርኛ በተጨማሪ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ጭምር ተነግረዋል።

በሀገረ እስራኤል የሚኖሩ ኢትዮዽያዊያን  ከዚህ ቀደም ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ ወደ እስራኤል በሄዱበት ጊዜ፣ ያረፉበት ሆቴል በር ላይ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ የስርዓቱን አፈና ማጋለጣቸው ይታወሳል።

ዘገባው—ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ

Filed in: Amharic