>

ተመስገን ደሳለኝ ህክመና ተከለከለ -  በድብደባው የጎን አጥንቱ ጉዳት ደርሶበታል...!!! (ታሪኩ ደሳለኝ)

ተመስገን ደሳለኝ ህክመና ተከለከለ –  በድብደባው የጎን አጥንቱ ጉዳት ደርሶበታል…!!!

ታሪኩ ደሳለኝ


ዛሬ ግንቦት 26/2014 ዓ.ም የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ደንበኛቸውን፣ እንዳነጋገሩት ትላንት ማታ የ3ተኛ ፖሊስ ጣቢያ ሀኪም እንዳየውና የአይኑ ስር እብጠት መሻሻል እንዳሰየ ነገርግን በትላንትናው ድብደባ ጎኑ (ribs) እንደተጎዳ ተናግረው፣ ለዚህም “ወጥቶ ህክምና ማግኘት አለበት” በማለት እንዲታከም ለራስ ደስታ ሆስፒታል ሪፈር  ፅፋውለት ነበር::

ዛሬ ግንቦት 26/2014 ዓ.ም ከቀኑ 5:40 ላይ ወደ ራስ ደስታ ሆስፒታል በአጃቢና በመኪና መሄድ ከጀመረ በኃላ በሬዲዮ መገናኛ በተሰጠ ትዕዛዝ ሆስፒታል ሳይደርስ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዲመለስ ተደርጓል::

በተጨማሪም ጠበቃ ሄኖክ እንደተናገሩት፣ በአሁኑ ሰዓት ጋዜጠኛ ተመስገን ፖሊሶቹ የተመታው ጎኑን (ribs) የህመም ስሜቱ እንዳልታገሰለት ነግረውኛል:: ጋዜጠኛ ተመስገን በዚህ የህመም ሁኔታ ውስጥ እያለ ነው ህክምና የተከለከለው።

[የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና ሚዲያዎች ጉዳዮን እንድታውቁልን፣ ማጣራት አድርጋችሁ ለሕዝብና ለሚመለከተው አካል እንድታደርሱልን]

ቤተሰቦቹ እና የፍትሕ መፅሔት ባልደረቦች

Filed in: Amharic