>

በኦሮሚያ ጉጂ ዞን "መጤ" ያሉትን ህዝን ቤት ንብረታቸውን አስጥለው እየሰበሰቧቸው ነው! ምን ታቅዶባቸው ነው...???

በኦሮሚያ ጉጂ ዞን “መጤ” ያሉትን ህዝን ቤት ንብረታቸውን አስጥለው እየሰበሰቧቸው ነው! ምን ታቅዶባቸው ነው…???

አሻራ ሚዲያ – ሰሜን አሜሪካ 

በኦሮሚያ ጉጂ ዞን በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ያሉ አማራዎችን በሙሉ “ኦነግ ሸኔን ልንመታ ስለሆነ …!” በሚል ሠበብ ቤት ንብረታቸውን ትተው ወደዞኑ ከተማ ቡሌሆራ በያገኙበት ቦታ እንዲሰባሰቡ እየተደረገ ነው፡፡

ከአማራ በተጨማሪ ጉራጌና ስልጤ ፣ ቡርጂ ፣ ኮይራ ኮንሶ ፥ ተብለው በብሄር ከተለዩ በኃላ “ለዘመቻው የሚውል ገንዘብ አዋጡ!” ተብሎ እንደብዛታቸው መጠን በርካታ ሚሊየን ብር ተጥሎባቸው  እንዲሰበስቡ እየተገደዱ ይገኛሉ፡፡ በግለሰብ ዝቅተኛ ከ3 ሺህ ብር ጀምሮ ፥ ከፍተኛው  እስከመቶ ሺህ ብር ድረስ ተገደው እንዲከፍሉ እየተደረገ መሆኑን   ፥ የመረጃ ምንጮቼ በዝርዝር አስረድተውኛል፡፡

በተቃራኒው ኦነግ ሸኔ ” እርምጃ ልንወስድ ነው ውጡ!” ተብለው ቤት ንብረታቸውን ጥለው የወጡትን ዜጎች ፥  መኖሪያ ቤትና ሀብታቸውን በነፃነት እያቃጠለና እያወደመ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸውና በብሄር ተከፋፍለው ወደከተማ ባዶ እጃቸውን እንዲሰበሰቡ የተደረጉት ዜጎች በአሁኑ ሠአት ከፍተኛ ጭንቀት ላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል!

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ባሳለፍነው ሳምንት ኦነግ ሸኔ ከቡሌ ሆራ በ7  ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ “ባዳ  መጋዳ” ከተባለ ጫካ አካባቢ እጅግ በርካታ ተሽከርካሪዎችን እያስቆመ ሲዘርፍና ሲያወድም  ፥ ዘረፋ ከሚካሄድበት ቦታ በ1 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ያሉ የመከላከያና የክልሉ ልዩሀይል ሰራዊቶች  አንዳች እርምጃ አለመውሰዳቸውን የመረጃ ምንጮቼ ገልፀዋል፡፡

ለመሆኑ በጉጂ ዞን ምን እየተካሄደ ነው?

ይሄንን ጉዳይ ክልሉስ ያውቀዋል ወይ ?

ገንዘብ ተገደው እንዲያዋጡ የሚደረገውስ ለምንድን ነው?

መልስ የሚሹ ጥያቄዎች ናቸው!

@ዘሪሁን ገሠሠ

Filed in: Amharic