>

ስንታየሁ ቸኮል በእስር ቤት ውስጥ የሚደርስበትን የመብት ጥሰት በመቃወም የርሃብ አድማ ጀመረ...!!! (ጌጥዬ ያለው)

ስንታየሁ ቸኮል በእስር ቤት ውስጥ የሚደርስበትን የመብት ጥሰት በመቃወም የርሃብ አድማ ጀመረ…!!!

*… እስካሁን  ፍርድ ቤት ቀርቦ አያውቅም! “እኔ ነኝ አሳሪህ” የሚል አካልም አልተገኘም…!!!

ጌጥዬ ያለው

 

“… የባልደራስ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊና ስራ አስፈጻሚ ስንታየሁ ቸኮል ለህይወቱ በሚያሰጋ ሁኔታ ላይ እንዳለ ከውስጥ መረጃ ደርሶናል፤ ፍርድ አደላዳዩ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ከጎነ ልንቆም ልንጮህለት ይገባል!!!

*…የሰብዓዊ መብት ድርጅቶችም እንዲጎበኙት ጥሪ አቅርቧል!

በባሕር ዳር አንደኛ ፖሊስ ጣቢያ ታግቶ የሚገኘው የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) የአደረጃጀት ጉዳዮች ኃላፊው ስንታየሁ ቸኮል፣ በእስር ቤት ውስጥ እየደረሰበት ያለውን የመብት ጥሰት በመቃወም ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ.ም. የርሃብ አድማ ጀምሯል። ዛሬ ረፋድ ጀምሮ የሄደለትን ምግብ መልሶ ልኳል።

እጅግ አሰቃቂ በሆነ ክፍል ውስጥ መታሰሩን የገለፀው አቶ ስንታየሁ፣ የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት በአካል ተገኝተው የእስር ቤቱን ሁኔታ እንዲጎበኙም ጥሪ አቅርቧል።

ካለፈው ግንቦት 19 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ታግቶ የሚገኘው አመራሩ፣ እስከ ሞት የሚደርስ ጉዳት ሊደርስበት እንደሚችል እና በእስር ቤቱ ውስጥ እየተዛተበት መሆኑንም ተናግሯል።

ከታሰረ 11 ቀናት ቢቆጠሩም ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ፍርድ ቤት አልቀረበም። የጣቢያው ፖሊስ አባላት የስንታየሁን ፍርድ ቤት አለመቅረብ ለአማራ ፖሊስ ኮሚሽን  ቢያሳውቁም፣ “እናንተ አያገባችሁም” የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው የመረጃ ምንጮች አረጋግጠዋል።

ስንታየሁ ቸኮል፣ ባልደራስ ሀገራዊ ፓርቲ ለመሆን የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ተከትሎ በባሕር ዳር ከተማ ሕዝባዊ የድጋፍ ፊርማዎችን   እያስፈረመ በከተማዋ ሲንቀሳቀሰሰ መቆየቱ፣  ከአረፈበት ሆቴል መኝታ ክፍል ውስጥ መታፈኑ ይታወሳል።

ስንታየሁ “እኔ ነኝ አሳሪህ” የሚል አካል እንኳ አላገኘም…!

ስንትሽ በብልጽግና ሰላዮች ታግቶ ባሕር ዳር 1ኛ ፖሊስ ጣቢያ ከገባ 11 ቀናትን አስቆጠረ። ጣቢያው ከተማው ውስጥ ካሉት ሁሉ በመጥፎነቱ የሚታወቅ ነው። እስከ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቦ አያውቅም። “እኔ ነኝ አሳሪህ” የሚል አልተገኘም። አጋቾቹ ግን ያው ወራሪዎቹ ናቸው።

በእስር ቤቱ ውስጥ በርካታ የመብት ጥሰቶች እየደረሱበት ነው። የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት (በተለይም መንግሥታዊው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን) ስማችሁን የሚመጥን እንኳን ባይሆን ስማችሁን የሚመስል ሥራ ሥሩ። ይህን ማድረግ ካልቻላችሁ የቁም እስረኞች መሆናችሁን እኛ ደጋግመን ከምንናገር አንድ አፍታ እንኳን እናንተ ራሳችሁ ተናገሩ። የሕግ ባለሙያዎች ማሕበራትም የተቋምነት ሰርተፊኬታችሁ አለመቀደዱን አሳዩን!

Filed in: Amharic