>

አልተመለሰም የሚሉት የኦሮሞ ጥያቄዎች ...?!?  ሰዎቹ ግን ምንድን ነው የሚፈልጉት...?!? (ግርማ ካሳ)

አልተመለሰም የሚሉት የኦሮሞ ጥያቄዎች …?!?  ሰዎቹ ግን ምንድን ነው የሚፈልጉት…?!?

ግርማ ካሳ


*….. ለመሆኑ በእናንተ እይታ  “ማን ነው ኦሮሞ ?”  የኦሮሞ ጥያቄዎች ምንድ ናቸው ????

“ኦሮሞ ማለት ማን ነው ?”  የሚለው በራሱ አከራካሪና አወዛጋቢ ነው፡፡ “ኦሮሞ ነኝ” የሚል ነው ኦሮሞ ? ኦሮምኛ የሚናገር ነው ኦሮሞ ? ኦሮሞ ክልል የሚኖር ነው ኦሮሞ ? ወይንስ የኦሮሞ መሪ ነን የሚሉ የኦሮሞነት ሰርተፊኬት የሚሰጡት፣ ኦሮሞ ነው የሚባለው????  ይህ ራሱን የቻለ ሰፊ  ርእስ ስለሆነ በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ፡፡

ቀጥሎ የሚነሳ ጥያቄ ፣ “የኦሮሞ ጥያቄዎች ምንድን ናቸው ?”  የሚለው ነው፡፡በኔ እምነት የኦሮሞ ጥያቄዎች የምላቸው፣ ከሌላላው ማህበረሰብ ጥይቄዎች ጋር የተገናነኙ የኦሮሞ ሳይሁን በአጠቃልይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄዎች  የሆኑ ናቸው ባይ ነኝ፡፡እነርሱም፣ 1ኛ በሰላም የመኖር፣ 2ኛ የፍትህ፣ 3ኛ የእኩልነት፣ 4ኛ ራስን በራስ የማስተዳደርና የዲሞክራሲ ፣ 5ኛ የልማት እና ሃብትና የሪሶርስ እኩል የመጠቀም፣ 5ኛ  በራስ ቋንቋ የመጠቀም፣ ባህልና ቅርስ የማሳደኛ የማስፋፋት ጥያቄዎች ናቸው፡፡  እነዚህ 5  ጥያቄዎች የኦሮሞ ጥያቄዎች ብቻ ተደርገው መወሰድ የለባቸው፡፡ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥያቄዎች ናቸው፡፡

በዚህ ጉዳይ በቅርቡ የኦፌኮ መሪ ዶር መራራ ጉዲና የሰጡት አስተያየት አለ፡፡  ከሁለት አመት በፊትም መዓዛ መሐመድ ጃዋርን ቃለ መጠይቅ አድርጋ የነበረ ጊዜ እርሱም፣ በቅርቡ ዶር መራራ የተናገሩትን ነበር፣  ያኔም የተናገረው፡፡ እነዚህ ሁለት መሪዎች የተናገሩትን በመውሰድ የኦሮሞ ጥይቄዎች ያሏቸውን በአምስት ጨምቄ እንደሚከተለው አቅርቢያቸዋለሁ፡

1ኛ  በሰላም የመኖር

2ና ሃብትንና ሪሶርቸ የመጠቀም

3ኛ ራስን በራስ የማስተዳደር

4ኛ ባቋንቋ መጠቀም ባህልና ቅርስን የማሳደግ

5ኛ የፌንፊኔ

ጥያቄዎች ናቸው፡፡

በ1ኛ እና 2ኛ  ተራ ቁጥር ላይ ያሉት ጥያቄዎች የምጋራቸው ናቸው፡፡ የኦሮሞ ብቻ ጥያቄ አድርገው ማቅረባቸው  ባይጥመኝም፡፡  ግማሹ የኦሮሞ ክልል ጦርነት ውስጥ ነው ያለው፡፡ ህዝቡ ሰላምንና መረጋጋት ተርቧል፡፡ ከምንም ነገር በላይ ሰላም ነው የሚፈልገው፡፡ ለዚህ ከኦህዴድ/ብልጽግናዎች ባልተናነሰ ኦነጎችም ተጠያቂ ናቸው፡፡ እነ ዶር መራራ ኦህዴድ ላይ ብቻ ሳይሆን ኦነግም  ላይ ጠንከር ብለው ትችት ማቅረብ ሲገባቸው ኦህዴድ ላይ ብቻ ማተኮራቸው ስህተት ነው፡፡ ሚዛናዊነትም የጎደለው ነው፡፡

ልማትን በተመለከተ፣  75% የኦሮሚያ ክልል ባጀት አዲስ አበባና አዲስ አበባ ዙሪያ ብቻ ስለሆነ የሚጠፋው፣ በኦህዴዶችም ስለሚዘረፍ ፣ አብዛኛው የኦሮሞ ክልል አካባቢዎች እነ ነቀምቴ፣ አርሲ፣ ባሌ ወዘተ ከልማት እንቅስቃሴዎች እጅግ በጣም ወደ ኋላ የቀሩ ናቸው፡፡ ምን አልባት አንዳንድ አካባቢዎች በክላስተር የእርሻ ስራ ከመስራት ውጭ ፋብሪካዎች ወዘተ የሉም፡፡  ነቀምቴ፣ መቱ፣ ጎባ፣ አሰላ የቀድሞ ክፍለ ሃገራት ዋና ከተሞች ነበሩ፡፡ ትልቅ ደረጃ መድረስ የነበረባቸው፡፡ ለብዙ የኦሮሞ ወጣት የስራ እድል የሚፈጥሩ፡፡ ግን እነዚህ ከተሞች አሁን ተራ መንደሮች ሆነው የለም እንዴ ???? በርግጥ ኦሮሞ የልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ከተፈለገ ኦሮሚያ የሚለው ጸረ ልማት፣ ለአስተዳደር የማያመች ክልል አነስ ወዳሉ መስተዳድሮች መሸንሸን አለበት፡፡

የራስን እድል በራስ የመወሰን መብትን በተመለከተ ፣ ኦሮሞ በኦሮሞ ነው መገዛት ያለበት ከሆነ ጥያቄያቸው፣ ላለፉት 31 አመታት የኦሮሞ ክልልን፣ የኦሮሞ ዞኖች፤ ወረዳዎች፣ ከተሞችን ኦሮሞ ብቻ አልነበረም እንዴ ሲያስተዳድር የነበረው ? አይ ያኔ ሕወሃት ከበስተጀርባ ነበረች ከተባለ ደግሞ፣ እሺ አሁንስ ?  ላለፉት 4 አመታት የፌዴራል መንግስትን ጨምሮ የያዙትና የተቆጣጠሩት ኦሮሞዎች ብቻ አይደሉምን ? በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ኦሮሞ ክልል ውስጥ አለ፡፡ አንድ ኦሮሞ ያልሆነ የኦሮሞ ክልል ፣ የዞኖች፣ የወረዳዎች፣ የከተሞች ሃላፊ ነው የሚሰራ፣ የጨፌ አባል የሆነ አለ ????? ክልሉ ሙሉ ለሙሉ የኦሮሞ፣ በኦሮሞ ለኦሮሞ ብቻ የሆነ የለየለት አፓርታይዳዊ ክልል አይደለምን ?

አዎን በኦሮሞ ክልል ኦሮሞ ያልሆኑ በብዛት በሚኖሩባቸው አካባቢዎች ሳይቀር፣ ኦሮሞ ብቻ ነው የሚሾመው፡፡ በኦሮሞ ክልል ኦሮሞ ያልሆኑ ወገኖች በብዛት የሚኖሩባቸው አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች ራሳቸውን በራስ የማስተዳደር መብታቸው የተጨፈለቀ ነው፡፡ የአሰላ ፣ የናዝሬት፣ የደብረ ዘይት… ከተማዎች ሕዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብት አለውን ? ራሱ በመረጣቸው ከንቲባዎች ነው የሚመራውን ? ለምን በነዚህ ከተሞች፣ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ቢኖር፣  ህዝብ ቢመርጥ፣ ኦሮሞ ያልሆነ ሊመረጥ ይችል ነበር፡፡ ግን እየሆነ ያለው እንደዚያ አይደለም፡፡   ኦሮሞነት እንደ መለኪያ ተቆጥሮ፣ የነዚህ ከተሞች ከንቲባዎች በኦሮሞነታቸው ነው የሚሾሙት፡፡

ከከተሞች አልፈን ስንሄድ በወረዳ ደረጃም ኦሮሞ ያልሆኑ ማጆሪቲ የሆኑባቸው ወረዳዎች አሉ፣ የደራ፣ ፈንታሌ፣ ግራግ ጃርሶ፣ አቤ ደንጎሮ፣ ቦሰት፣ አዳማ…. የወረዳ ጽ/ቤቶች ኦሮሞዎች ብቻ ናቸው፡፡ እንደውም አገለግሎትም አብዛኛው ነዋሪ አማርኛ ተናጋሪም ሆኖ፣  በአስተርጓሚ በኦሮምኛ ነው፡፡

በኔ እይታ የኦሮሞዎች ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ሙሉ ለሙሉ ተከብሯል ባይ ነኝ፡፡ ያልተከበረውና የተጨፈለቀው በኦሮሞ ክልል ያሉ የሌሎች ማህበረሰባት ራስን በራስ የማስተዳደር፣ የፖለቲካ ውክልና የማግኘት መብት ነው፡፡ እነ ዶር መራራ ያንን መናገር አይፈልጉም፡፡

በቋንቋ መጠቀም ፣ ባህልና ቅርስን ማሳደግ ወዘተ የተባለው፣ መቼም አገር የሚያየው ነገር ነው፡፡ ኦሮሞ ክልል እንዳለ የስራ ቋንቋ ኦሮምኛ ብቻ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ሳይቀር በኦሮምኛ  የፈለገ ኦሮሞ ካለ፣  መማር ይችላል፡፡ ኢሬቻ ደብረ ዘይት በሉ አዲስ አበባ ለቀናት መንገድ ዘግተው ያከብራሉ፡፡ በአዲስ አበባ ሰፊ መሬት ወስደው የኦሮሞ ባህል ማእከል አላቸው፡፡ ቆይ ምንድን ነው ሰዎቹ የሚፈልጉት ???????

ኦሮምኛ የፌዴራል ቋንቋ ካልሆነ የሚሉት፡ ነገር ነው ?  እስከሚገባኝ  ድረስ ያንን የሚቃወም ብዙ ሰው ይኖራል ብዬ አላስብም፡፡ አማርኛ ዋና የፌዴራል መንግስት መግባብያ ቋንቋ ሆኖ፣ ሁሉም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የፌዴራል ቋንቋ ማድረግ ይችላል፡፡ ማለት አንድን ቋንቋ የሚናገሩ ዜጎች በብዛት የሚኖሩባቸው አካባቢዎች የፌዴራል መንግስት አገልግሎት በዚያ ቋንቋ እንዲያገኙ ማድረግ፡፡ ለምሳሌ በም እራብ ወለጋ 97% ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ባሉበት አካባቢ የፌዴራል መንግስቱ በኦሮምኛ አገለግሎት መስጠት አለበት፡፡ በሶማሌ ክልል በሶማሌኛ፡፡በትግራይ በትግሪኛ፡፡

አምስተኛው ጥያቄ የፊንፊኔ ጥያቄ ያሉት ነው፡፡ ይህ የእብደት ጥያቄ  ነው፡፡ በግልጽ መታወቅ ያለበት፣ የፊንፊኔ ጥይቄ አለን ሲሉ፣ የአዲስ አበባ ሕዝብ የራስ እድል በራስ የመወሰን፣ ራሱን በራሱ የማስተዳደር ሊኖረው አይገባውም፣ ለአዲስ አበባ ሕዝብ እኛን ነን የምንወስንለት ማለታቸው ነው፡፡ ይህ ጥያቄ፡ ተቀባይነት የለውም፡፡ ባሌና አርሲ ያሉ ኦሮሞ ነን የሚሉ ለአዲስ አበቤ ሊወስኑልት አይችሉም፡፡

ለጊዜው በጉልበት አራት ኪሎን ስለተቆጣጠሩ እንጂ፣  ያለ ምንም ጥርጥር የአዲስ አበባ ሕዝብ ኦሮሚያ የሚባለውን ከንቱ ክልልን አይፈልግም፡፡ የኦሮሞ ክልል ጽ/ቤት ከአዲስ

አበባ እንዲወጣም ይደረጋል፡፡ በአፓርታይድ ስር መሆን የማይታሰብ ነው፡፡

ከመቶ አመት በፊት አዲስ አበባ የኦሮሞ ነበር የሚል ነገር አላቸው፡፡ ይሄንን ጨዋታ እዚያው ያቁሙት፡፡ አዎን ከመቶ አመት በፊት ከ10 ሺህ የማይበልጡ የኦሮሞ ቆቱዎች (ገበሬዎች) ይኖሩ ነበር፡፡ ከ350 አመት በፊት ደግሞ ኦሮሞ የሚባል አዲስ አበባ አይደለም ሸዋ አልነበረም፡፡ ስለዚህ ከመቶ አመት በፊት ሲባል፣ ከ350 በፊት የሚል ጥያቄ ስለሚመታ  እዚያ ላይ ሙግት መፍጠር አያዋጣም፡፡ አዲስ አበባ የነዋሪዎቿ ናት፡፡ ማንም ሰው ኦሮሞ ይሁን ሌላ አዲስ አበባ መጥቶ መኖር፣ አዲስ አበቤ መሆን ይችላል፡፡ አበቃ፡፡

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=10227406425857098&id=1555646492

Filed in: Amharic