>

" የኢትዮጵያን ህዝብ ፍቅር የተራበዉ ጎሰኛ መሪ የራሱን ድምጽ የህዝብ ድምጽ አድርጎ የራሱን የስነልቦና ርሃብ ያረካል...!!!" (ሸንቁጥ አየለ)

” የኢትዮጵያን ህዝብ ፍቅር የተራበዉ ጎሰኛ መሪ የራሱን ድምጽ የህዝብ ድምጽ አድርጎ የራሱን የስነልቦና ርሃብ ያረካል…!!!”

ሸንቁጥ አየለ

“አቢቹ ታላቅ ሰዉ ! አቢቹ ነዉ ምርጫችን “ :- አቢይ አህመድ እራሱን በራሱ የፌስ ቡክ ገጹ ሲያቆለጳጵስ እጅ ፈንጅ ሲያዝ….!!!

ማስታወሻ:-

*…. ይሄ አቢይ አህመድ ፔጅ ላይ የሚታዬዉ ፌስቡክ የሚሰጠዉ ልዩ የመታወቂያ ባጅ ፔጁ የራሳቸዉ የባለቤቶቹ መሆኑን አጣርቶ እና ባለቤቶቹም ግለሰባዊ ማስረጃዎችን ሲያቀርቡ ብቻ ነዉ::እናም ይሄ እዚህ የምታዩት ፔጅ የራሱ የአቢይ አህመድ ነዉ:: እንዲህ አይነት ስም ከዚህ ከልዩ መለያ ጋር የሚኖረዉ በፌስቡክ ዉስጥ አንድ እና አንድ ብቻ ነዉ:!!

የአቢይ አህመድ ነገር ይደንቃል ..

–የኢትዮጵያ ህዝብ ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ ወጥቶ “አቢይ ንገስብን : አቢቹ ታላቅ ሰዉ: ምርጫችን አቢይ ነዉ: አቢይ ኢትዮጵያዊነትን ሊመልስል ነዉ” ብሎ ዘመረለት : ዘፈነለት በታላቅ ሀገራዊ መሪነትም አከበረዉ::

አቢይ ግን መሆን የመረጠዉ የአንድ ጎሳ መሪ መሆንን ሆነ::ሚሊዮን ኢትዮጵያዉያን በነገዳቸዉ እና በሀይማኖታቸዉ ሲጨፈጨፉ ዛፍ እየተከለ እየተዘባነነል እየተቀማጠል የህዝብን ደም  ከትንኝ ሞት ያነሰ ዋጋ ሰጠው::

ከዚያ ይልቅ አቢይ የአንድ የጎሳ መሪ ብቻ ሆኖ “ኦሮሞ ኦሮሞን ከሚገለዉ ብለን ኦነግ ወንጀል ሲሰራ ሳንቀጣዉ ቀረን::ዝም ብለን አለፍነዉ::” ብሎ የሌሎች ኢትዮጵያዉያንን ህይወት የሚያረግፈዉን ኦነግ/ኦህደድን እንደ ባሌጌ እና  ቀበጥ ልጁ ሲንከባከበ በሌሎች ኢትዮጵያዉያን ነገዶች ሞት ላይ መቀናጣቱን ቀጠል::እንዴያዉም ወንጀለኛዉን ኦነግን እያስታጠቀ ሚሊዮኖች እንዲጨፈጨፉና እንዲፈናቀሉ አደረገ::

የኢትዮጵያ ህዝብም “እኛ የወደድንህ የሀገራችን የኢትዮጵያ መሪ ትሆናለህ ብለን እንጂ የጎሳ መሪማ ከሆንክ አክ እንትፍ” ብሎ አቢይ የተባለዉን ሰዉዬ ጠላዉ::

—–

እናም ህዝብ እንደተፋዉ የተገነዘበዉ አቢይ ፌስቡክ የልዩ መታወቂያ  ባጅ በሰጠው በራሱ አካዉንት “አቢቹ ታላቅ ሰዉ ! አቢቹ ነዉ ምርጫችን ነ” እያለ እራሱ እራሱን እያቆለጳጰሰ ይጽፋል::

እናም “አቢቹ ታላቅ ሰዉ ! አቢቹ ነዉ ምርጫችን ነዉ” እያለ እራሱ በራሱ አንደበት የሚያቆለጳጵሰዉ የኢትዮጵያ ህዝብ መሪያችን ሁን ቢለዉ የአንድ ጎሳ መሪ መሆንን የመረጠዉ ሰዉ ነዉ::

የኢትዮጵያን ህዝብ ፍቅር የተራበዉ ጎሰኛ መሪ የራሱን ድምጽ የህዝብ ድምጽ አድርጎ የራሱን የስነልቦና ርሃብ ያረካል::

ደናቁርቶቹ የራሱ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎችቹ: እንዲሁም ሙታንን እና እሥስቶቹ የብአዴን ሆዳም ካድሬዎቹም የአቢይ ቅሌትን በማሰራጨት share ያደርጉታል::

ግን ጥያቄዬ አቢይ የአይቲ እዉቀት አለዉ አልተባለም እንዴ? እንዴት እንዲህ ሲሰራ ህዝብ ያስተዉለኛል ብሎ አላሰበም?

Filed in: Amharic