>

በፓርላማው ውስጥ…!!  (ዘመድኩን በቀለ)

በፓርላማው ውስጥ…!!

(ዘመድኩን በቀለ)

• ትግሬ ጭራሽ ለጊዜው የህዝብ ወኪል የለውም። እሱን ቀን እስኪወጣለት ዝም ብሎ ማየት ነው። ጮጋ…!!

• #አፋር በስሙ ፓርላማ የገቡ ወኪል እንደራሴዎች ነበሩት። ነገር ግን የተወከሉት በብልጽግና በኩል ስለሆነ ለአፋር ለሞቱ፣ ለራብ፣ ለጥሙና ለስደቱ ድምፅ የሚሆነው እንደራሴ የለውም።

“…ሶማሌም፣ ደቡብም፣ ጋምቤላም፣ ሐረሬ እና ጉምዝም ሁላቸውም ወኪል እንደራሴ ነበራቸው። ነገር ግን ህዝቡ የተወከለው በብልጽግና ስለሆነ ትንፍሽ የሚልላቸው የለም።

“…ኦሮሞም ዋናውን ጨምሮ ነፍ ወኪል እንደራሴዎች ነበሩት። ነገር ግን በተሸጠው ኦነግና በበለፀገው ኦህዴድ ስለተወከሉ ሞት ስደታቸውን በፓርላማ ለህዝብ የሚያሰማላቸው አንድም ኦሮሞ አላገኙም። ቢያንስ ምዕራብ ሸዋ፣ ወለጋ፣ እና ደቡብ ኦሮሚያ ያለውን ስቃይ አቤት የሚል ድምፅ ይፈለግ ነበር። ግን ወኪል ከየት የምጣ…?

“…ኢዜማን እርሱት። የመረጠውም የለም ስለዚህ እሱ አይፈረድበትም። ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ነበረ እሱም ጭራሽ በፓርላማው አልተገኘም። ወይ እኔ አላየሁትም።

“…የቀረው ዐማራ ነበር። እሱም ቢሆን በመቶዎች በሚቆጠሩ የለመዱ በድንና አሁን ደግሞ በለፀገው ብአዴን ተወክለው የነበረ ቢሆንም፣ እንደ መረገም ሆኖ ብአዴን ለህዝቡ ድምጽ የመሆን ፀጋም ስሜትም ስለሌለው አይጠበቅም። በስተመጨረሻ ግን ሳይደግስ የማይጣላው ጌታ ባልተለመደ መልኩ በዚያ በፓርላማ ውስጥ ድምጽ የሚሆኑት ሁለት ትንታግ ልጆች በተአምር ተከሰቱለት። መንጋ ሙሉ ብአዴን በታጨቀበት በዚያ ፓርላማ ሁለቱ የዐማራ የቁርጥ ቀን ልጆች የሺ ሰው ግምቶቹ የተከበሩ ዶር ደሳለኝ ጫኔ እና የተከበሩ አቶ ክርስቲያን ታደለ ድምፅ ሆኑት፣ ከጥርነፋ ወጥተው ነፃ ሆነው በድኖቹ በተጎለቱበት የዐብኖቹ ፈርጦች ለህዝባቸው ድምፅ ሆኑት።

“…ሰውየው ግን ፊቱ ነው የጠቆረ…!!

Filed in: Amharic