በጋምቤላ ከተማ በመንግሥትና በአማፅያን መካከል የተኩስ ልውውጥ ተደረገ !!
ባልደራስ
ከፊል የከተማዋ ክፍል በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ነው!!
በጋምቤላ መስተዳድር ጋምቤላ ከተማ ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ንጋት ላይ ጀምሮ የተኩስ ልውውጥ ለሰዓታት የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል። ተኩሱ በተለይም በርዕሰ መስተዳድሩ ፅህፈት ቤት አካባቢ ያተኮረ ነው።
የተኩስ ልውውጡ የተደረገው ኦነግ-ሸኔ እና የጋምቤላ ነፃነት ግንባር አማፅያን አንድ ግንባር በመፍጠር ከመንግሥት የሰራዊት አባላት ጋር ነው።
ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የተኩስ ልውውጡ እንደቀጠለ ሲሆን፤ ከባሮ ወንዝ ማዶ ያለው የከተማው ክፍል በአማፅያን ታጣቂዎች ቂጥጥር ስር መሆኑን ምንጮች አረጋግጠዋል።
በአሁኑ ሰዓት መንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች፣ የንግድ ተቋማትና ሌሎች አገልግሎት መስጫ ተቋማት ተዘግተዋል። ኗሪዎችም ከመኖሪያ ቤታቸው መውጣት አልቻሉም።