>

ክቡር ገና ኢዜማን በይፋ ተሰናበቱ...!  (ዮናስ አበራ ዶ/ር)

ክቡር ገና ኢዜማን በይፋ ተሰናበቱ…!

ዮናስ አበራ ዶ/ር

”ኢዜማ የመንግስት ተለጣፊ ነው፣ ከአሁን በኋላ ከፓርቲው ወጥቻለሁ” 

ክቡር ገና

“ስልጣን መጋራት ብቸኛው አማራጭ ነው ብሎ ከሚያስብ አጎብዳጅ ፓርቲ ጋር አባል ሆኜ መቀጠል አልፈልግም” ክቡር ገና

ኢዜማ እንደ አንድ ተቃዋሚ ፓርቲ ለህዝብ የገባውን ቃል እና የተቋቋመበትን ዋነኛ አላማ እና ግብከማሳካት ይልቅ፣ ከገዢው ፓርቲ ጋር በመለጠፍ መስመሩን መሳቱ እጅግ የሚያሳስበኝ ጉዳይ ነው።

በመሆኑም ከዚህ በሗላ ስልጣን መጋራት ብቸኛው አማራጭ ነው ብሎ የሚያስብና ለመታረመም ለመቃናትም ዝግጁ ያልሆነ አጎብዳጅ ፓርቲ ጋር አባል ሆኜ መቀጠል አልፈልግም።

እምነት ጥዬ የገባሁበት ፓርቲ አላማውን ስቶ ወደ ገባበት የቁልቁለት ጉዞ አብሬ ለመግባትና የታሪክ ተወቃሽ ለመሆን ህሌናዬ አይፈቅድልኝም። በመሆኑም ከኢዜማ አባልነቴ በፈቃዴ ለቅቂያለሁ።

(ክቡር ገና – የኢዜማ ከፍተኛ አመራርና ለአዲስ አበባ ከንቲባነት የተወዳደረ ከመልቀቂያ ደብዳቤው ላይ የተወሰደ)

እነ ከተፌ እንዴት በግዜ ባነኑ ?

እኔኮ የሚገርመኝ የኢዜማን የአብይ ተለጣፊነት ለማወቅ አንድ እንደ ክቡር ገና ያለ ፖለቲከኛ እንዴት 4 ዓመት ይወስድበታል?

የኢዜማን ተለጣፊነት ሳያውቅና ሳይረዳ ቀርቶ እንዳይመስልህ አራት አመታት ሙሉ እዚያው ኢዜማ ውስጥ ሲንቦጫረቅ የከረመው፤ የብርሃኑ ነጋ አካሄድ ግልፅ አልሆንለት ብሎ፣ ከዛሬ ነገ ወደ ህዝብ እንመለሳለን፥ ብርሃኑም ይስተካከላል ብሎ እንዳይመስልህ!! በጭራሽ!!

ይሄኔ አረም ነቀላ ሚንስትርነትም ቢሆን አብይ ከጣለልኝ ብሎ ሲቀላውጥ የነበር ይመስለኛል!!

ቢያይ ቢያይ ወፍ የለም!! ፓርቲውም እንዳበቃለት በደንብ ገባው፤ ተሸበለለ!! አለቀ!!

ክቡር ገና ፖለቲካ በቃኝ የሚል ከመሰለህ “ያን ትውልድ” ፈፅሞ አታውቀውም ማለት ነው፤ ሰውዬው ሌላ ፓርቲ ውስጥ ይገባና አሁንም ይሞክራል፤ ብልፅግና ውስጥ ሳይቀር ነው የምልህ!!  Prostateቱ አብጦ ካቴተር በመሽኛው እስኪገባለት ድረስ ከፖርቲ ፓርቲ መገለባበጡ አይቀርም!! በእነዚህ ሰዎች ስንቴ ትሸወዳለህ? ብርሃኑን አየህ፣ አንዳርጋቸውን አየህ፣ በየነ ጴጥሮስን አየህ …. እንዴ? ስንት ዘመን ኢትዮጵያን ሲያጨማልቁ አየህ አይደል እንዴ? እግዚዮ!!

ይሄ ሁሉ መዓት ሃገሪቱ ላይ ሲወርድ ተለጉሞ የከረመ ተመላላሽ ፖለቲከኛ ዛሬ “ኢዜማን ለቅቂያለሁ” ብሎ እንደ አፋር ግመል ሙቀት ይፈጥራል!!

ወገኛ!!

ዛሬ ኢዜማን ተቸልኝ ብለህ “ከክቡር ገና ጎን እቆማለሁ” በል አንተ እንደለመድከው።

Me, I tell it like it is !!

Filed in: Amharic