>
5:21 pm - Monday July 20, 5693

የአብን የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ስብሰባ ረግጠው ወጡ! (አሻራ ሚድያ)

የአብን የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ስብሰባ ረግጠው ወጡ!

አሻራ ሚድያ


*…. በወለጋ_የተጨፈጨፉ_ከ2500 በላይ ደረሰ

ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአብን አባላት ስብሰባውን አቋርጠው ወጥተዋል። ረግጠው የወጡበች ምክንያት በዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ አማካኝነት ቀዳሚ አጀንዳ ወለጋ ጊምቢ ስለተጨፈጨፉት ወገኖቻችን ብሄራዊ የሃዘን ቀን እንዲታወጅ፣ ስብሰባውም በህሊና ጸሎት እንዲጀመርና ጠቅላይ ሚኒስትሩም በም/ቤቱ ቀርበው በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ ለአፈ-ጉባኤው ቀርቦ እንደነበር እና ነገር ግን አፈ-ጉባኤው ግን አጀንዳው እንዲያዝ አልመፍቀዳቸው ታውቋል።

በዘር-ተኮር በሆነው ጭፍጨፋ ከ400 በላይ ዜጎቻችንን ባጣንበት ወቅት ስብሰባውን እንደ አዘቦት ቀን መታደም ለህሊናችን ስለከበደን የሚከተሉት የአብን አባላት የም/ቤቱን ጉባኤ አቋርጠን ለመውጣት እንደተገደዱ ከዚህ በታች ያሉ የምክር ቤት አባላት መረጃውን አድርሰውኛል።

1. ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ (የባህር ዳር ተወካይ)

2. አቶ አበባው ደሳለው (የጅጋ /ምዕራብ ጎጃም ተወካይ)

3. አቶ ሙሉቀን አሰፋ (የሸበል በረንታ- ዕድ ውሃ ተወካይ)

4.አቶ ዘመነ ሃይሉ (የጭስ አባይ ተወካይ)

መረጃ ያደረሱኝ የምክር ቤት አባሉ አክለውም አቶ ክርስቲያን ታደለ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ስለሆኑና የሳቸው ኮሚቴ ሪፖርት ስለሚያቀርብ ስብሰባውን አቋርጠው መውጣት እንዳልቻሉም ገልጸውልኛል።

ሙሉጌታ አምበርብር

Filed in: Amharic