>

ከገዳይ በላይ፣ከጭፍጨፋው ሰቆቃ በበለጠ ለሞቱ የሚሰጠው ስም እና ትርጉም ያሰቅቀኛል...!!! (መስከረም አበራ)

ከገዳይ በላይ፣ከጭፍጨፋው ሰቆቃ በበለጠ ለሞቱ የሚሰጠው ስም እና ትርጉም ያሰቅቀኛል…!!!

መስከረም አበራ


*… አካሌ ከእስር ሲፈታ አእምሮዬ የሚያስበውን የምፅፍባቸው “Devices” (ስልኬ፣ Lap topዬ ) ከእስር አልተፈቱም። ካውንቶቼ ሁሉ ይበጃል ብዬ ባደረግኩት “Two step verification adjustment” ምክንያት ስልኬ እጄላይ ሳይኖር አካውንቶቼን መክፈት አልቻልኩም።

ስለሆነም ታስሬ በነበረበት ወቅት እኔንም፣ የጨቅላ አራስ ልጄንም፣የቤተሰቤንም ጩኸት ለጮሃችሁልኝ ውዶቼ ምስጋና ማቅረብ እንኳን አልቻልኩም። ዛሬ ግን የባሰው ስለመጣ በባለቤቴ አካውንት መጣሁ!!!!😪

ከቅርብ አመታት ወዲህ እየተባባሰ የመጣው የአማራ ህዝብ የሰቆቃ ኑሮና የውርደት ሞት አእምሮዬን ሰቅዞ ስለያዘኝ የገባሁበት የትግል መስመር በዛሬይቱ ኢትዮጵያ እጅግ አደገኛው መስመር እንደሆነ ጠንቅቄ እረዳለሁና እስሩ ብዙ  አላስገረመኝም፤ የዚህ ህዝብ አሰቃቂ ሞት እስኪያበቃ ድረስ ልሄድበት ለራሴ ከማልኩት ጉዞም የሚያስተጓጉለኝ አይሆንም – እንደውም ይበልጥ ያበረታኝ ይሆናል እንጅ!

ገና ከእስር ከመፈታቴ የጠበቀኝ በአሰቃቂነቱ ዓለምን ሁሉ ያነጋገረ የመከረኛው የአማራ ህዝብ ሞት ነው።

ይህ የአማራ ህዝብ እልቂት ዛሬ የተጀመረ ይመስል ዓለምን ሁሉ ገና ዛሬ ማነጋገሩ ልክ ባይሆንም አውቆ የተኛ በተነሳ ሰዓትም ቢሆን የህዝባችንን መከራ ተረድቼ አዘንኩ ማለቱ የዓማራን ህዝብ የህልውና ትግል ያግዛል እንጅ ክፋት የለውም።

ሆኖም የአማራ ህዝብ ለድፍን አራት አመት በር ተዘግቶበት ሲጨፈጨፍ  አውቆ የተኛው ዓለም ዛሬ ለደረሰው ጭፍጨፋ አስተዋፅኦ እንዳለው መረሳት የለበትም።

የአማራ ህዝብ በትግሉ ሰብዓዊ ክብሩን ሲያስከብር ዓለም በሞቱ ላይ ጆሮውን ደፍኖ የኖረውን ዓለም ሁሉ በሩዋንዳው የዘር ፍጅት እንዳደረጉት  ይቅርታ የሚጠይቁበት ዘመን ይመጣል።

እነዚህ ዘግይተው የነቁ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች፣ ኢምበሲዎች ፣ ታዋቂ ዲፕሎማቶች እንኳን ጭፍጨፋው በአማራ ህዝብ ላይ በማንነቱ ምክንያት የተደረገ ጭፍጨፋ እንደሆነ አስረግጠው ሲናገሩ በማከብረው ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የሚመራው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና ኢሰመጉ “የንፁሃን ዜጎች ሞት” ሲሉ ወንጀሉን  ያድበሰበሱበት ምን ለማግኘት እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም!

እንዲህ ያለው የ”Genocide”ን ወንጀል የማድበስበስ አደገኛ አካሄድ ዘር ማጥፋቱን የሚያግዝ ብሎም የሚያባብስ እንደሆነ ጠንቅቄ ስለማውቅ በእነዚህ ሁለት ተቋማት አካሄድ እጅግ ማዘኔን መግለፅ እወዳለሁ!!!! ኢዜማ፣ኦፌኮ ፣ኦህዴድ፣ኦነግ ስላወጡት መግለጫ ምንም ማለት አያስፈልገኝም!!!!!

ከገዳይ በላይ፣ከጭፍጨፋው ሰቆቃ በበለጠ ለሞቱ የሚሰጠው ስም እና ትርጉም እንደሚያሳዝነኝ ግን ሳልገልፅ አላልፍም።

ሃዘኔን የሚያበረታው  እንዲህ ያሉ አስመሳይ አካሄዶች  ወደፊትም ይህን መሰል ጭፍጨፋ እንዳይከሰት የሚያግዙ ስላልሆኑ ነው!!!!!! ሰው በስንቱ ያዝናል????

በእውነት ለመናገር አሁን ላይ የሚሰማኝን ስሜት ለመግለፅ ይቸግረኛል!!! ውስጤ ያለቅሳል፣ጥቅመቢስነት አጥንቴን ዘልቆ ይሰማኛል፣በሃገሬ ፖለቲካ ሁለመና ቂም ለመቋጠር ከሚዳዳው ልቤ ጋር ሙግት እገጥማለሁ፣ነፍሴ “ምን ይሻላልን?” በማሰላሰል ትቃትታለች……የአማራ ህዝብ በክንዱ፣በትግሉ ሰብዓዊ ክብሩን እንደሚያስመልስ ግን ቅንጣት ያህል አልጠራጠርም!!!!!!

ለዚህ ህዝብ የሚወጣ ቀን አለ !!!!!!!!!!!!

Filed in: Amharic