>
5:13 pm - Saturday April 19, 6092

ቅዱስ ፓትርያርኩ የወለጋና ጋምቤላውን ጭፍጨፋ አወገዙ...!!! (አባይ ነህ ካሴ)

ቅዱስ ፓትርያርኩ የወለጋና ጋምቤላውን ጭፍጨፋ አወገዙ…!!!

አባይ ነህ ካሴ


ግፉን ባወገዙበት መግለጫ የሚከተሉትን ነጥቦች አንሥተዋል።

ስሜትን በሚወርር፣ ልብን በሚያሳዝን፣ ጉልበትን በሚሰብር ኀዘን ውስጥ ላሉት ወገኖቻችን፤ ትናንት ባለ ብዙ ቤተሰብ ዛሬ ሌጣ ለኾኑት፣ የክብር ሞትና መቃብር ለተነፈጉት፣ ሰው ሆነው በሰው ለተገፉት፣ ኢትዮጵያዊ ሁነው በኢትዮጵያውያን ለተሠዉት፣ አገር : ሳላቸው እንደ ባዕድ ለተቆጠሩት ለደከሙበት ምድር : በወርቅ ፈንታ ሰይፍ ለተከፈሉት ልጆቻችን እግዚአብሔር ያጽናችሁ በማለት፣ የሞቱትንም ደመ አቤልን ያከበረ አምላክ ደማቸውን እንዲመራመር በመለመን መልእክታችንን እንጀምራለን!

ብዙ መልካም ቃላት በሚነገሩበት፣ የጥበብ ድምፆች በሚያስተጋቡበት፣ መሠረት ፈርሶ ለጉልላት ጌጥ በምንጨነቅበት በዚህ ዘመን፣ “እንዴት ካለው ጊዜ ደረስን ማለት መመጻደቅ ባይሆን ኖሮ የሚባልበት ወቅት ሁኖ አግኝተነዋል።

ትናንት ገንዘብን የሚቀሙ “እንዴት የሰውን ልፋት ይወስዳሉም ተብለው በተወገዙበት ምድር ሕይወትን የሚቀሙ፡ የሰው ዘር ቅነሳ የሚያደርጉ ግፈኞች ሲንጎማለሉ ማየት ያሳዝናል።

ንጹሐን ወገኖቻችን እግዚአብሔር በሰጣቸው ማንነት ብቻ ሲሞቱ ስናይ የዝቅታችንና የመውደቃችን ልክ ማጣት ጎልቶ ይታያል።

ገዳዮችም ቀጥተኛ የእግዚአብሔር ተቃዋሚዎች ናቸው።

በወለጋና በጋምቤላ የአገራችን ክፍል የደረሰውን አሰቃቂ የወገኖቻችን ግድያ ስሰማ እንደ ወትሮው ልቤ በታላቅ ኀዘን ተመትቷል።

አገራችን ኢትዮጵያ የሚያስከብሯትን መሪዎች አሁንም እየተጣራች ነውና መንግሥትና ሕዝብ ግፍን በተግባር ማውገዝ ያስፈልጋቸዋል።

ጊዜው እየረፈደ፣ ሞትም ዜና እየሆነ፣ ዜጋም ክብሩን እያጣ ስጋትም ገዥ እየሆነ የምንቀጥልበት ጊዜ እንዲያበቃም ታላቅ ጥሪያችንን በሕያው እግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን!

Filed in: Amharic