>
5:13 pm - Tuesday April 19, 4321

በመንግስት የተጠቀሰው የሟቾች ቁጥር ትልቅ ተቃዉሞ አስነሳ ....!!! (D W)

በመንግስት የተጠቀሰው የሟቾች ቁጥር ትልቅ ተቃዉሞ አስነሳ ….!!!

D W


የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈዉ ሰኔ 11 ምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌና በአጎራባቹ በኒ ሻንጉል ቀበሌዎች በታጣቂዎች የተገደሉትን ሰዎች ቁጥር አስመልክቶ ትናንት ያወጣዉን ወግለጫ ከጥቃቱ ከተረፉ ነዋሪዎች ተቃዉሞ፣ ከመብት ተሟጋቾች ጥያቄ እየተሰነዘረበት ነዉ።ወላጅ፣ ዘመድ ወዳጆቻቸዉ የተገደሉባቸዉ፣ አንዳዶቹን ቀብረናል የሚሉ የአካባቢዉ ነዋሪዎች በየፊናቸዉ እንዳስታወቁት የሟቾቹ ቁጥር ከ2 ሺሕ ቢበልጥ እንጂ አያንስም።ሁለት ቦታዎች ብቻ ከሁለት መቶ በላይ አስከሬን መቅበራቸዉን የተናገሩ አንድ ነዋሪ እንደሚሉት ቤት ተዘግቶ እሳት የተለኮሰባቸዉ፣መስጊድ ዉስጥ በጅምላ የተረሸኑ፣ በየቤቱ በአሰቃቂ ሁኔታ የተቀሉት ሰዎች ቁጥር በሺዎች የሚቆጠር ነዉ።ሌለኛዉ አስተያየት ሰጪ ደግሞ እሳቸዉ በተሳተፉበት የቀብር ስርዓት ብቻ ከ400 በላይ አስከሬን ተቀብሯል።መቀመጫዉን ዩናይትድ ስቴትስ ያደረገዉ Genocide Prevention In Ethiopia (በኢትዮጵያ የዘር ማጥፋት ተከላካይ) የተሰኘዉ ድርጅት አንድ ባልደረባ ባለፈዉ ሳምንት እንዳስታወቁት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ1500 እንደሚበልጥ መረጃ ደርሷቸዋል።የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ቃል አቀባይ ቢልለኔ ስዩም ግን ትናንት ለዉጪ ጋዜጠኞች «ደረሰኝ» ባሉት መረጃ መሰረት የሟቾቹ ቁጥር 338 ነዉ።

ከጥቃቱ የተረፉ እንዳሉት የኢትዮጵያ መንግስት ኦነግ ሸኔ የሚለዉ የኦሮሞ ነፃነት ጦር (OLA) ቶሌ ቀበሌና በአካባቢዉ የሚኖሩ ሰላማዊ የአማራ ተወላጆችን ወንድ-ከሴት፣ ሕፃን-ካዋቂ ሳይለዩ በመደዳ ጨፋቸዋቸዋል።ዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ አንድ የOLA ባለስልጣን ስለጉዳዩ አስተያየት እንዲሰጡን በተደጋጋሚ ብንደዉልላቸዉም ስልካቸዉን አያነሱም።የተለያዩ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችና የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ግድያዉ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ እየጠየቁ ነዉ።ተቃዋሚ ፖለቲከኞች፣ተማሪዎች፣ ዉጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ጭፍጨፋዉን በተለያየ መንገድ እያወገዙ ነዉ።

Filed in: Amharic