>

የሱዳን ጦር አንዳንድ ቁልፍ ቦታዎችን ከኢትዮጵያ ጦር አስለቅቆ መቆጣጠሩን ሮይተርስ ዘገበ!! (ባልደራስ)

የሱዳን ጦር አንዳንድ ቁልፍ ቦታዎችን ከኢትዮጵያ ጦር አስለቅቆ መቆጣጠሩን ሮይተርስ ዘገበ!!

 

ዘገባው—-ሮይተርስ


የሱዳን ጦር አንዳንድ ቁልፍ ቦታዎችን ከኢትዮጵያ ጦር አስለቅቆ መቆጣጠሩን ሮይተርስ ዘገበ። የሱዳን ጦር የተቆጣጠረው ጀበል ካላ አል-ላባን የተባለ ቦታ ነው ሲል የሱዳን መንግሥት ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል። “የዓይን እማኞች ነን” ያሉም ይህንኑ ለሮይተርስ ተናግረዋል።

የሱዳን ጦር በከባድ ጦር መሳሪያዎች እና በጦር አውሮፕላኖች የኢትዮጵያ ሠራዊት የያዛቸውን ቦታዎች ማጥቃቱ ታውቋል።

የሱዳን ዜና ምንጮች ደግሞ፣  የሱዳን ጦር “ባርካኻት”የተባለ ቦታ እና “ተስፋ አዳዊ” የተባሉ ኮረብታዎችን እንደተቆጣጠረ አመልክተዋል።

የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ሠራዊት ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት መፈጸሙን ምንጮች የተናገሩት፣ ሱዳን ሰባት የተማረኩ ወታደሮቿ በኢትዮጽያ ወታደሮች ተረሽነዋል የሚል ክስ ማቅረቧን እና የሱዳን ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጀኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርኻን በሱዳን ምሥራቃዊ ድንበር የሠፈረውን የሱዳን ጦር መጎብኘታቸውን ተከትሎ ነው።

ሱዳን በኢትዮጵያ ተረሸኑብኝ ላለቻቸው የተማረኩ ወታደሮቿ ጉዳይ ለተመድ ጸጥታው ምክር ቤት አቤቱታ ማቅረቧን ባለሥልጣናቷ ተናግረዋል።

ዘገባው—-ሮይተርስ

/

Filed in: Amharic