>

ይድረስ  ለባለ ''ሾርት ሜሞሪ'' ክቡርነትዎ  (ዘምሳሌ)

ይድረስ  ”ለባለ ሾርት ሜሞሪ”ክቡርነትዎ 

 

አዎን

እንደእባብ  በልብህ በደፈጣ ከርመህ

ቀን ጎድሎብን ወጣህ  ከዘረኞች ጎልተህ

አሳ ጎርጓሪዎች   ሰው አጥተው  አገኙህ

እናም እርጉሙ ወዳጄ

ተደመሩ ብለህ  ፊቱኑ ስታውጅ

መልካም ወጣት ብለህ ቄሮን ስታደራጅ

አምሀራ በዘሩ  ባገሩ ሲፈረጅ

በተራ አመራርህ በየትም ሰው ሲፈጅ

በኦነግም መንፈስ ሀገርን ስትመራ

ቤተመንግሥት ሆነህ ህዝቡ ደም ሲዘራ

በኑሮ ውድነት በሕዝቦች መከራ

በታክስ ከፋዮች ብር  ስትረግጥ ዳንኪራ

ኢትዮጵያ እያልከን ሀገር አደንዝዘህ

ምክር ቤት ድራማ አባላት አፍዝዘህ

ዘረኛ ምላስክን  በስተሗላ አግዘህ

ንፁሀን ስታስፈጅ ሸኔን ተመርኩዘህ

ታስታውስ እንደሆን

ባልበሰለ አዕምሮ በጅምላ ስትሰድበን

በወያኔ ምሬት ሰው መስለህ አንግሰን

አመትም ሳይሞላህ ለምድህ ወልቆ አየን  ይኸው አንተ መጥተህ ቁልቁል ተሰቀልን

በጅምላም ተቀበርን በዶዘር ተረገጥን

እርጉሙ ወዳጄ ታዲያ

በአሽቃባጮች ድጋፍ በስልጣን ከለላ

ለኦነግ ስም ሰጥተህ  በሸኔ ታፔላ

ለስልጣንህ ብለህ ገንዘብ ስታስበላ

የንፁሀን ዜጎችን አንገት ስታስቀላ

በመደመር ስሌት   ፈረስ ብልፅግና

ከጅማ ተነስተህ በጨቅላ ልቦና

በዘር ተመርዘህ በህዋት ቁመና

በታዛዥነትህ  ስትሰልል  ገና

ላስታውስህ ብዬ ነው

አይምሮህ  ማስታወስ ድንገት  ከተሳነው

 

ያኔ ማለቴ ነው ገና  ለምድ ለብሰህ

ስንቶችን አስፈጀህ ተላላኪ  ሆነህ

እንደቡችላቸው ይዘው ሲጎትቱህ

የስንቱን ነፍስ አለ  በዘረኛው እጅህ

ያልተረሳህ እንደሁ ሜሞሪ ሾርት ሆነህ

አዎን ፍላጎቱትህ ሞልቶ ህልምህም  ተሳክቶ

ሁሉን ልትጨፈልቅ   ደም ጥማትህ ረክቶ

ለጊዜው ቢመስልህ  አጨብጫቢህ በዝቶ

በዘር ማጥፋት ወንጀል ማትጠየቅ ከቶ

ሕፃናት አዋቂ  ሁሉን አስለቀሰህ

ባህል ማንነትን አፍርሰህ እያንኳሰህ

በኦነግ ሸኔ ታርጋ  ትውልድ አስገድለህ

ኢትዮጵያዊነትን በዘር  እየለካህ

ምን ያለ መሪ ነህ ሀገር  የምትጠላ

የኢትዮጵያን መሬት  ስትሸጠው  ለሌላ

ውለህ የምታድር  ከጠላት ሽንገላ

መርገም የተጣባህ  ሰው  የምታስበላ

አምሀራን ከትግሬ  ከጦርነት ዘፍቀህ

ኦሮሞን መርዘህ አማሀራ  አስገድለህ

ከሱዳን ዶልተህ ከግብፅ ትእዛዝ ወስደህ

ለሻቢያ መሪ ቀለበትም አስረህ

አራቱን አመታት  ሀገር አመሳቅለህ

ተቃዋሚን  ሁላ ወዶ  ሊሆን ምርኮ

ፈዛዛ ምሁራን  ውስጥህ ተሰግስጎ

ሮጠህ መሬት ስትሰጥ ለባእዳን ድርጎ

ወስደህ ስታስረክብ  በድብቅ ተልዕኮ

አዎን ጥፋቱ ወዲህ ነው ለሰላም ስንቋምጥ

ፈቅደን ቤተመንግሥት  ወደን ስትቀመጥ

መርዘኛው ስሌትህ  ሀገር  ሲበጠብጥ

አንተው አሳየኸን ዘርህን ስታስበልጥ

የሚገርመው ደግሞ

ምሁራን ተብየው  ላንተ ያሸረገደው

ሆዳም ከርሱን ይዞ ክብሩን የሸቀጠው

አብላጫው  አንድሁኖ  ካንተ የተጣባው

ሀገር አሰዳቢው  ፍርድ የሚጠብቀው

 

አለ ገና ብዙ

መች  አውግቼህ በቃኝ  የፖስተሯ ፀሎት

ያንተ አስመሳይነት  ሀገር ለመበጥበጥ

በእግዜር ቃል ስትሸቅጥ መቻኮል ለክደት

ድቢ  ስታስመታ  በጥንቆላ  ህይወት

መች ተባረክና  ቅይጥ እምነት ይዘህ

አንዱ ለሌላኛው ተቃርኖ ሳይገባህ

ከሼኩ ስትበላ ከፖስተርህ መክረህ

ከቄሱም ስትዶልት  በሆድ ጩቤ ይዘህ

ሙስሊም ገዳ ጴንጤ አክተር በሁሉም ቤት

ቦኮ ሀራም ወድቆ አልሸባብ  አልፎበት

አንተ አዲስ አመጣህ  በመደመር ስሌት

መንግስት የተባለ  የአራጆች ሰራዊት

እያየን ታዘብን

ቀን ይመጣል ብለን

ግና

ጊዜያት ተቆጠሩ ሟችም  በሀገር በዛ

የህዝብ ቅነሳው ግድያው እንደዛ

ባልጠበከው መጠን አምሀራ እየበዛ

መሄጃ ሲያሳጣህ ከዚህም እሰከዛ

ደጋፊህ ዘረኛ  ባንተ የታቀፈ

ዘወትር  በኢትዮጵያ ህዝብ እየገፈፈ

ሀገር ጠል እውራን ሰው እየቀጠፈ

ህፃናት አዋቂ  እየረፈረፈ

ቤተመንግሥት ሆነህ ዜጎች ስትናደፍ

ለስልጣንህ ብለህ  ንፁሀን ስታረግፍ

በደም ተጨማልቆ እጅህ የሞላው ግፍ

ለጊዜው  ቢመስልህ  ሳትጠየቅ ምታልፍ

ያ ጊዜ ይመጣል  አንተኑ ሊይዝህ

የሰራኸው ተንኮል   ማምለጪያ እንኳ የለህ

ዛሬን ብታናፋ  ስልጣን አለኝ ብለህ

እመነኝ ዘረኛዉ  ነገ ትፈርሳለህ

ሜሞሪ ሾርት ካልሆንክ  በቁም የሞትክ ነህ!

ኢትዮጵያ ቀጣይ ነች አምሀራም ይኖራል

ያንተ መሰሎችም ቅዠቱ ያከትማል

ብዙ እንዳልነግርህ ቋንቋው ይመርሃል

ያለርሱ ደሞ አትኖር  ዋጠው ያሽርሃል

ኢትዮጵያ ሆይ ጠላትሽን ብችል በጦር ታልሆነም  በብዕሬ ወግቼ እጥለዋለሁ

እዎን አምሀራ ነኝ!

የኢትዮጵያ  ልጅ

ዘምሳሌ  ከቴምስ ማዶ

zemessale@gmail.com

Filed in: Amharic