>

በግፍ ዘሩ እንዲጠፋ የተደረገው አማራ ፍትህ ሲጠይቅ መንግስት የቁጥር ጨዋታ ውስጥ ገብቷል...!!! (ምንሊክ ሳልሳዊ) ፡

በግፍ ዘሩ እንዲጠፋ የተደረገው አማራ ፍትህ ሲጠይቅ መንግስት የቁጥር ጨዋታ ውስጥ ገብቷል…!!!

ምንሊክ ሳልሳዊ ፡


–  በምዕራብ ወለጋ በኦነግ ታጣቂዎች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሺሕ 600 በላይ ደርሷል –

የዐይን እማኞች

– መንግሥት በጊምቢው ጥቃት 338 ሰዎች መገደላቸውን ገለጸ

– ቢልለኔ ስዩም

መንግስት ሆይ ከአይን እማኝ በላይ ምስክር የለም። መንግስት ያወጣው የሟቾች ቁጥር አሃዝ ሆን ተብሎ ለማታለል የተደረገ ነው። ሕዝብ የመንግስትን መዋቅራዊ ውሸት ጠንቅቆ እንደሚያውቅ ባለስልጣናት ሊያውቁ ይገባል። መንግስት ጥያቄው የቁጥር ሳይሆን የመብት መሆኑን ዘግቶታትል። የተሳሳተ መረጃ ከመስጠት ወጥመድ መንግስት ራሱን ሊያላቅቅ ይገባል።

መንግስት እንደ ተቋም ባለስልጣናቱ እንደ ግለሰብ ውሸታሞችና አጭበርባሪዎች ናቸው። በወለጋው የጊምቢ ቶሌ ቀበሌ ጭፍጨፋ ከአከባቢው ነዋሪዎችና ቀባሪዎች በላይ ማንም ማስረጃ ሊሆን አይችልም። ወንጀል የፈጸመው በመንግስት መዋቅር የሚደገፈው ታጣቂ መሆኑ እየታወቅ መንግስት የሞቱትን ሰዎች ቁጥር በሚመቸው መልኩ ማቅረቡ ተቀባይነት የለውም። መንግስት የቁጥር ጨዋታ የብሄር ቆጠራ በገባ ሰዐት ሁሉ የዜጎችን መብት ይዘነጋዋል።

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር/ሠራዊት ብሎ በሚጠራው ሸኔ የተገደሉ ሰዎች ከ1 ሺሕ 600 መሻገሩን የዐይን እማኞች መግለፃቸው የታወቀ ሆኖ ሳለ የመንግስት መግለጫ በጊንቢው ጥቃት 338 ሰዎች መገደላቸውን መንግስት ምን ያህል መዋቅሩ በውሸት እንደተተበተመ ጠቋሚ ነው። በጥቃቱ የሞቱ ሰዎችን አስከሬን በመሰብሰብ ላይ የተሰማሩና ለደኅንነታቸው ሲባል ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ዐይን እማኞች ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ከ1 ሺሕ 600 በላይ ሰዎች እንደተገደሉ እና 900 የሚሆኑ ሰዎችን ሬሳ ቆጥረን ቀብረናል ብለዋል። የመብትና የቁጥር ጥያቄን መንግስት ከኝዛቤ ሊያስገባው ይገባል።

መንግስት ሆይ ከአይን እማኝ በላይ ምስክር የለም። የዐይን እማኞቹ አክለውም፣ እስከ አሁን ሬሳቸው ተገኝቶ ከተቀበሩት ሰዎች በተጨማሪ፣ በመኖሪያ ቤታቸው እንዳሉ ተቃጥለው የተገደሉ እና በተለያዩ ምክንያቶች በጫካ ውስጥ ሬሳቸው ጠፍቶ ያልተገኘበት ሁኔታ መኖሩን ተናግረዋል። ይህ ማለት ገና ወደፊት የሟቾች ቁጥር ይጨምራል ማለት ነው። ስለዚህ መንግስት ያወጣው የሟቾች ቁጥር አሃዝ ሆን ተብሎ ሕዝብን ለማታለል የተደረገ ነው። መንግስት ማውራት የነበረበት የተሳሳተውን ቁጥር ሳይሆን የዜጎችን መብት ነው።

Filed in: Amharic