>

አፈናው ተጠናክሮ ቀጥሏል!! ጋዜጠኛ ወግደረስ  ጤናው በባህርዳር ታፍኗል!!

አፈናው ተጠናክሮ ቀጥሏል!!

ጋዜጠኛ ወግደረስ  ጤናው በባህርዳር ታፍኗል!!

*… ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው በአደራ እስረኝነት ተቀምጧል። “የፌዴራል ፖሊስ ‘አቆዩኝ’ ብሏል። የሚፈልግህ እርሱ ነው” ተብሏል…!

ጋዜጠኛ ወግደረስ  ጤናዉ፣ በደህንነቶች ታፍኖ ባህርዳር 2ኛ ፓሊስ ጣቢያ ታስሯል። ወግደረስ ጤናው በአዲስ አበባ ከአድዋ ክብረ በዓል ጋር በተያያዘ ታስሮ ከቆየ ቦኃላ በዋስትና መፈታቱ ይታወሳል።

ትንሽ ጋብ ብሎ የነበረው በፋኖዎች፣ በጋዜጠኞች፣ በአክቲሸስቶች እና በባልደራስ አባላት ላይ የሚፈፀመው አፈና ዳግም አገርሽቶ በአዲስ አበባ እና በባህር ዳር ሰዎች አየታሰሩ ይገኛሉ።

ዘገባው—-ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ

ምስል—- ወግደረስ በፖሊስ ጣቢያ

Filed in: Amharic