>

ከጭፍጨፋ የተረፉት በተላላፊ በሽታ ተያዙ...!!! (ባልደራስ)

ከጭፍጨፋ የተረፉት በተላላፊ በሽታ ተያዙ…!!!

 በተላላፊ በሽታ የተያዙ 700 የጊምቢ ወረዳ ተፈናቃይ አማሮች ሕክምና  ተከለከሉ!!

ባልደራስ


በኦሮሚያ መስተዳድር ምዕራብ ወለጋ ዞን፤ ጊምቢ ወረዳ፤ ቶሌ ቀበሌ በአማራ ሕዝብ ላይ ከተፈፀመው ጅምላ ጭፍጨፋ የተረፉ አማሮች በተላላፊ በሸታዎች ተይዘዋል።

ወረርሽኙ “ብርድ ብርድ በማለት ለረጅም ሰዓት ሰውነትን ቁርምጥም ያደርጋል። ወደ ሐኪም ቤት ስንሄድ ለሌላው ሕዝብ አገልግሎት እየሰጡ፣ አማሮችን ለይተው መድኃኒት አልቋል ይሉናል፣  ያመናጭቁናል” ብለዋል ተፈናቃዮቹ።

ወረርሽኙ ፕላስቲክ ወጥረው በሚኖሩበት መጠለያ ውስጥ ልብስ ስለማይለብሱና ከክረምቱ ጋር ተደማምሮ ብርዱ ከፍተኛ ስለሆነ የመጣ እንደሆነም ይናገራሉ። የአካባቢው ባለስልጣናት አማሮችን ለይተው እንዳገለሏቸው ተናግረዋል። የታማሚዎች ቁጥር ከ700 በላይ መሆኑን መረጃዎች አመላክተዋል።

 

በጊምቢ በአንዳንድ የመንግሥት ባለሥልጣናት የሚደገፈው ኦነግ-ሸኔ ካደረሰው የጅምላ ጭፍጨፋ አምልጠው ከቀያቸው የተፈናቀሉ አማሮች ከሰባት ሺህ በላይ መሆናቸውን መረጃዎች ጨምረው አመላክተዋል።

ከሳምንት በፊት በወሊድ ላይ የነበሩ ሁለት እናቶች ህክምና ተከልክለው ከእነ ጨቅላ ልጆቻቸው መሞታቸው ይታወሳል።

ዘገባው—-ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ

Filed in: Amharic