>

ዛሬም በወለጋ ከሁለት መቶ በላይ አማሮች በጅምላ ተጨፈጨፉ!! ዳጉ ጆርናል

ዛሬም በወለጋ ከሁለት መቶ በላይ አማሮች በጅምላ ተጨፈጨፉ!!

ዳጉ ጆርናል

*… በኦሮሚያ መስተዳድር ቄለም ወለጋ ዞን፤ ሮቢት ገበያ ወረዳ መቻራ ለምለም ቀበሌ ውስጥ በአማሮች ላይ አዲስ ጅምላ ጭፍጨፋ ተፈፅሟል።

በቄለም ወለጋ ዞን ሀዋ ገለን ወረዳ ፤ ለምለም ቀበሌ ዉስጥ መንደር 20 ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ በዛሬዉ እለት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት አሰቃቂ የጅምላ ጭፍጨፋ መካሄዱን  የአካባቢዉ ነዋሪዎች ለ ዳጉ ጆርናል ተናግረዋል።

ስማቸዉ እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ምንጭ እንደተናገሩት በዛሬዉ እለት የሽብር ቡድኑ በከፈተዉ ጥቃት ከሁለት መቶ በላይ ንጹሀን እንደተገደሉ ነግረዉናል። በጥቃቱ በርካታ ህጻናት እና እናቶች መገደላቸዉንም ገልጸዉልናል።

የሽብር ቡድኑ ሀይል ብዛት የነበረዉ  በመሆኑ በአካባቢዉ የሚገኙ የሚሊሻ የጸጥታ ሀይሎች ተጨማሪ ሀይል እስኪመጣ ወደ አካባቢዉ መግባት እንዳልቻሉም ነዋሪዎቹ አንስተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የአካል ጉዳት የደረሰባቸዉ በርካታ ዜጎች እንደሚገኙ እና ቁስለኞቹንም ከአካባቢዉ ለማስወጣት እንደተቸገሩም ነዋሪዎቹ ይናገራሉ።

በወለጋ ሰኔ 11/2014 ዓ.ም ተመሳሳይ የጅምላ ጭፍጨፋ  ቁጥራቸዉ ከፍተኛ የሆኑ ንጹሀን እንደተገደሉ ይታወቃል።

Filed in: Amharic