>

ኦነግ አማራን ይጨፈጭፋል ብአዴን ፋኖን ያሳድዳል...!!! (ወንጭፍ)

ኦነግ አማራን ይጨፈጭፋል ብአዴን ፋኖን ያሳድዳል…!!!

ወንጭፍ


የባሕር ዳር ፋኖን ማፈን እና ማሳደዱ ቀጥሏል…!!!

ባለፈው ሳምንት አፋኙና አሳዳጁ መንግሥት የአማራ ፋኖ በባሕር ዳር አመራሮችን እና አባላትን አስሯል፤ ሌሎችን ለማሰረም በማሳደድ ላይ ይገኛል።

ይህ አፋኝ የሆነ መንግሥት በጣም አሳዛኝ እና አስነዋሪ ተግባር በአንድ ጓዳችን ቤተሰብ ላይ ፈፅሟል። ነገሩ እንዲህ ነው፦

ያው እንደተለመደው አፍኖ ለማሰር ወደ አንድ የአማራ ፋኖ በባሕር ዳር ጓድ ቤት አፋኙ ግብረ -ሀይል ይሄዳል። ነገር ግን ጓዱ በቤቱ አልበረም። “የት ሄዶ ነው?”*በማለት ባለቤቱን ከልጆቹ ፊት እያንገራገሩና እያሰፈራሩ ያናግሯታል።

የባለቤቱም ምላሽ “እኔ አላወቅኩም። ለሥራ እንደ ወጣ ነው” የሚል ነበር። “በድጋሜ ስንመጣ ባይገኝ! ዋ!” በማለት ዝተውባት ይሄዳሉ።

በሚቀጥለው ቀን ወደ ቤቱ የሄዱት ከሌሊቱ 10:00 ሰዐት ነው፤ በውድቅት ሌሊት የአራት አመት ሕፃን ልጇን ጨምሮ ከሌሎች ልጆቿ ጋር በተኛችበት ቤቱን አስከፍተው “የት አለ ባለቤትሽ?” እያሉ ዛቱባት

ስልክ እንድትደውል አስገደዷት፥ ደወለች። ጓዳችንም ለሥራ በሄደበት ስልኩን አንስቶ “ምንድን ነው? ሰላም ነው?” እያለ በማናገር ላይ እያለ በመሃል ግን የሚሰማው የአፋኞችን የዛቻ ንግግር ነበር፤ ‘እንዲህ በዪው’ እያሉ በቁጣ ድምፅ ሲጮሁባት ይሰማ ነበር። “ልጅህ ታሟል በአስቸኳይ ና በዪው” ይሏታል።

Filed in: Amharic