>
5:30 pm - Sunday November 1, 2544

ሽመልስ አብዲሳን ተጠያቂ ማድረግ ያልቻለ ሥርዓት የሽኔን የዘር ፍጅት ጥቃት ማስቆም አይችልም...!!! (ያሬድ ሀይለማርያም)


ሽመልስ አብዲሳን ተጠያቂ ማድረግ ያልቻለ ሥርዓት የሽኔን የዘር ፍጅት ጥቃት ማስቆም አይችልም…!!!

ያሬድ ሀይለማርያም

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ በዘር ላይ ያነጣጠረው ጥቃት በየሳምንቱ መቀጠሉ መንግስት ሽኔን አሳድጄ አካባቢውን ነጻ አድርጌያለሁ ባለ በቀናቶች ልዩነት መሆኑ እጅግ ያሳዝናል። መንግስት የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ፣ የጅምላ ጥቃቶችንም መከላከል አለመቻሉን ነው። ከሁሉ ከሁሉ ሀዘናችንን የሚያከብደውና የሚያሳዝነው በየእልቂቱ ማግስት የሁለቱ ክልል ሹሞች እየተዛዘሉ መግለጫ የሚሰጡት፣ የሚማማሉት፣ የሚወዳደሱት፣ አንዳንዴም የሚሸላለሙት እና ሽኔን እናጠፋለን እያሉ የሚፎክሩት ነገር ነው።

እኔ አሁንም ለእነዚህ እልቂቶች ተጠያቂ የማደርገው  ሽኔ የሚባለውን ቡድን ብቻ ሳይሆን ጠቅላይ ሚንስትሩን ጨምሮ የክልሉን ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና በየደረጃው ያሉ ባለስልጣናትን ነው። ያለ ተጠያቂነት ይህ ጥቃት ሊቆም አይችልም።

በግፍ የተገደሉትን ወገኖቻችንን ነፍስ ይማር

Filed in: Amharic