>

እንደ እንግሊዙ ጠ/ሚ/ር፣ ዐቢይ አህመድም ስልጣን በፍቃዳቸው እንዲለቁ ...!!! (ባልደራሥ)

እንደ እንግሊዙ ጠ/ሚ/ር፣ ዐቢይ አህመድም ስልጣን በፍቃዳቸው እንዲለቁ …!!!

ባልደራሥ


በርካታ የካቢኔ አባላት ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው ከለቀቁ በኋላ፣ የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ሥልጣናቸውን እንደሚለቁ እገልጸዋል።

ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በከፍተኛ እና በዝቅተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊነት ላይ የነበሩ ወደ 60 የሚጠጉ ከመንግሥት ኃፊነት መልቀቃቸው፣ ቦሪስ ጆንሰን ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ያላቸውን አቅም መሰረት በማሳጣቱ፣ እሳቸውም ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ተገደዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ በኩል የሚተካቸው ሰው እስከሚገኝ እስከ መስከረም ድረስ በጠቅላይ ሚንስትርነት በሥልጣናቸው ላይ ለመቆየት አቅደዋል።ሆኖም፣ በርካታ ባልደረቦቻቸው እና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ከዚያ በፊት ሥልጣን እንዲለቁ ይፈልጋሉ። ለግዜው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ክፍት የነበሩትን የካቢኔ ቦታዎች በሌሎች ተክተዋል።

በኢትዮዽያም፣ ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ስልጣን እንዲለቁ የሚፈልጉ የገዢው ፓርቲ እና ሰፊ የማህበረሰብ ክፍል አለ። እነዚያ የገዢው ፓርቲ አባላት ስልጣን በመልቀቅ ታሪክ መስራት ይችላሉ። ጠ/ሚ/ሩ ለ 5 ዓመታት የተመረጡት ለተወካዮች ምክር ቤት አባልነት እንጂ፣ ለጠ/ሚ/ሩ ቦታ እንዳልሆነ ይታወቃል። ይህ ማለት፣ ገዢው ፓርቲ ስልጣን ሳይለቅ ጠ/ሚ/ሩ ሊቀየሩ ይችላሉ ማለት ነው። በቀድሞው ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ግዜም ይኸው በኢትዮዽያ ተደርጓል።ታሪክ ራሱን ይደግም ይሆን?

ጠ/ሚ/ሩ ሀገር መምራት እንደማይችሉ እንደሆነ በየግዜው ይበልጥ ፍንትው ብሎ እየታየ ነው።

Filed in: Amharic