>

በአሶሳ  በኦነግ-ሸኔ እና የጉምዝ ታጣቂዎች ጥቃት በርካቶች ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል...!!! (ባልደራስ)

በአሶሳ  በኦነግ-ሸኔ እና የጉምዝ ታጣቂዎች ጥቃት በርካቶች ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል…!!!

ባልደራስ

*… የቆሰሉት እስካሁን ህክምና አላገኙም…!!!


በቤኝሻንጉል ጉምዝ፤ አሶሳ ዞን ሸርቆሌ ወረዳ ባፈው ሐሙስ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. አሸባሪው ኦነግ-ሸኔ እና የጉምዝ ታጣቂዎች ጥምረት በመፍጠር በአማራ ተወላጆች ላይ ጥቃት ፈፅመዋል።

በጥቃቱም እናትና ልጅን ጨምሮ በቁጥር ያልተጠቀሱ አማራዎች ተገድለዋል። ጥቃት ፈፃሚዎቹ በከፊል የኦሮሞ ብልፅግና አመራሮች የሚታገዙ እንደሆኑም የመረጃ ምንጮች ተናግረዋል።

በሰሞኑ ጥቃት ከተገደሉት አማራዎች መካከል ከአርባ ዓመት ጎልማሳ እስከ አምስት ዓመት ሕፃን ይገኙበታል።

የሟቾች የቀብር ስነ ስርዓት ትናንት አመሻሽ ተፈፅሟል። በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው ቁስለኞች ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የህክምና እርዳታ አላገኙም።

አሁንም ተጨማሪ ጥቃቶች በአካባቢው በሚኖሩ አማራዎች ላይ አንዣቧል።

Filed in: Amharic