>

" አፍነው ወሰዱኝ፤ አፍነው ጫካ ጣሉኝ...!!! (ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ)

” አፍነው ወሰዱኝ፤ አፍነው ጫካ ጣሉኝ…!!!

ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ


ቤቴን ሰብረው ገብተው፣አፍነው፣ ከአንገቴ በላይ ሸፍነው የወሰዱኝ ሰዎች ከ11 ቀናት በኋላ እንዳወሳሰዳቸው  ሸፍነው አምጥተው በካራ ጫካ ጥለውኝ ሄደዋል።

የት እንደነበርኩ በየት በኩል እንደወሰዱኝና በየት በኩል እንዳመጡኝም አላውቅም።

ብቻ የፈለጉትን ማድረግ የሚቾሉ ሰዎች በእግዚአብሔር አዳኝነትና በእነርሱ መሀሪነት በሕይወት ተመልሻለሁ።

ከአካሌ የጎደለም ሆነ የተጎዳ የለም።

የክራሞቴን ነገር ሆድ ይፍጀው!

ለተጨነቃችሁልኝ በሙሉ –

ለጭንቀታችሁና ለፀሎታችሁ ለምስጋና አማርኛዬ ጉልበት የለውም። አመሠግናለሁ!!!”

Filed in: Amharic