>

"... ኢዜማ ለውጥ ያስፈልገዋል ያልን ሀይሎች ሁሉ በዶ/ር ብርሃኑ ነጋና ደጋፊዎቹ ከጀርባችን ተወግተናል...!!!" (ሀብታሙ ኪታባ ገመቹ)

“… ኢዜማ ለውጥ ያስፈልገዋል ያልን ሀይሎች ሁሉ በዶክትር ብርሃኑ ነጋና ደጋፊዎቹ ከጀርባችን ተወግተናል…!!!”

– ሀብታሙ ኪታባ ገመቹ

 

ብርሃኑ ነጋ እንዲመረጥ የሚፈልጉ ቡድኖች ቀደም ብለው የምርጫ መከታተያ ቅፅ አዘጋጅተው ጉባኤውን ለመጥለፍ ሲሰሩ ይዘናቸዋል። እነዚህን ሰዎች እንዲታገዱ ብናደርግም፣ የታገዱትን ጨምሮ ባዘጋጁት ቅፅ በዝርዝር የብርሃኑ ነጋ ቡድኖች ብለው በስምና በፎቶ የጠቀሷቸው ሰዎች በኢዜማ ጉባኤ ተመርጠዋል።

በኢዜማ ጉባኤ ከመንግስት ጋር በመስራታችን ያጣነው ተቀባይነት ዙሪያ ሪፖርት እንዲቀርብ ጠይቄ ነበር። ነገር ግን ብርሃኑ ነጋ በጉባኤው ስለ ትምህርት ሚንስቴር ሪፎርም እና ስለ ህወሃት ብቻ ዝርዝር ሪፖርት በማቅረብ ጊዜው እንዲሄድ አደረገ። በዚህም ስለ ኢዜማ ችግሮች ሳንመክር ጉባኤው ተዘጋ።

በርካታ የኢዜማ ሰዎች ከኢዜማ ስም በፍቅር የወደቁ ይመስለኛል። ኢዜማ በስሙ ሳይሆን፣ በተግባሩ ነው ልንመዝነው የሚገባ። በስም ብቻ ለውጥ ማምጣት ቢቻል ኑሮ እንደ ብልፅግና መልካም ስም የያዘ የለም ነበር።

ብልፅግና የብሄር ፖለቲካን በማከም ለውጥ አመጣለሁ የሚል የብሄር ፓርቲ ነው። ኦሮሚያ ክልል ሲሄድ ለኦሮሞ የሚመቸውን፣ አማራ ክልል ሲሄድ ለአማራ የሚመቸውን በመናገር እድሜ ለማስረዘም የሚጥር የብሄር ፓርቲ ነው። እንዴት እንደሆነ ባላውቅም አሁን ላይ አዲስ አበባ ኦሮሞ ትራፊክ ፖሊሶች በዝተዋል። ጥፋት አጥፍቸ ይዘውኝ፣ መንጃ ፈቃዴን ስሰጣቸው ስሜ ሀብታሙ ኪታባ ገመቹ ስለሚል ሳይቀጡ ያልፉኛል። ከባድ ጊዜ ላይ ደርሰናል።

ለአዲስ የፖለቲካ ባህል ብለን ትተነው እንጂ፣ የሰሜን ዕዝ ከጀርባው በህወሃት እንደተወጋው ሁሉ፤ ኢዜማ ለውጥ ያስፈልገዋል ያልን ሀይሎችም በዶክትር ብርሃኑ ነጋ ደጋፊዎች ከጀርባችን ተወግተናል።

(ሀብታሙ ኪታባ ገመቹ – የኢዜማ ስራ አስፈፃሚ)

Filed in: Amharic