>

ክቡር ኢትዮጵያዊ ሆይ:- ለአብሉሱ ፈራይ ደም እየገበርክ መኖርህ ይብቃ...!!! (ኢያሱ ኤፍሬም ገ/ሃና) 

ክቡር ኢትዮጵያዊ ሆይ:- ለአብሉሱ ፈራይ ደም እየገበርክ መኖርህ ይብቃ…!!!

ኢያሱ ኤፍሬም ገ/ሃና 

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ቤተ ክርስቲያን ከ 100 በላይ መፅሓፍት በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጡ አሉ ከዚህ ውስጥ በይበልጥ የሚታወቁት ሰማኒያ አንድ ቅዱስመፅሐፍቶች ናቸው፡፡ በእዚህም ይዘቱ በዓለማችን ብቸኛው ትልቁ የእምነት መፅሐፍ ያደርገዋል፡፡ ከሰማኒያ አንዶቹ መፅሐፍት አንዱ መፅሐፈ ሔኖክ ነው፡

፡ ይህ መፅሐፍ ከብዙ የመፅሐፍ ቅዱስ መፅሐፍቶች እጅግ የከበደ ሚስጢር ያዘለ እንደሆነ የእምነት አባቶች ይናገራሉ ፡፡ ነገር ግን በጥንት የሮም ግዛትበነበረችው በናሲያ ከተማ ቀዳማዊ ኮንስታንቲን ዙፋን ላይ በነበረበት በ325 ኤዲ በተደረገው የመጀመሪያው የእምነት ጉባኤ ከታገዱ መፅሐፍት አንዱ ነው፡በእዚህ መጣጥፍ ውስጥ በመፅሐፈ ሔኖክ ያሉትን ሁሉ ታሪኮች ለመተረክ አይዳዳኝም ነገር ግን ከመፀሐፈ ሔኖክ የምንማረው እንዳንድ ቁም ነገሮችን ለዛሬመጣጥፌ ማጠንጠኛ አድርጌ ልጠቀምባቸው ፈቅጃለሁ፡፡ ታሪኩም እንዲህ ነው፡፡ መልአክቶች የሰው ልጆችን ባዩ ጊዜ በውበታቸው ተደነቁ በልባቸውም

ፈቀዷቸው ወደ ምድር ወርደው ከሰው ልጆች ጋራ ጋብቻን ፈፀሙ፡፡ ይህ ጋብቻ ግን መልካምን ነገር ይዞ አልመጣም፡፡

ለሰው ልጅ የተረፈው ነገር ቢኖር

ምድርን በደም ማጭቅየት እና የሰው ልጆችን መካራ ማብዛት ነበር ፡፡ ይህም በመሆኑ የሰው ልጆችም ወደ አምላካቸው ጮሁጩኸታቸውም በመልአክቶችተሰማ፡፡ መል አክቶችም ወደ ምድር ባዩ ጌዜ ምድር በደም ተጨማላቃ አዩ፡፡ መልክትም የሆነወን ነገር እና የሰው ልጆችን ጩኽት ለአምላክ አቀረቡ ፡አምላክም መልአክቶችን ልኮ የሰው ልጆችን ታደገ ፡፡ ከተላኩት መልአክት መካከል ሚካኤል ፡ ኡራኤል ገብራኤል እና እራፋኤል ይገኙበታል፡፡

ይህ ታሪክ የሚነግረን እና የሚያስተምረን ብዙ ሚስጥራቶች አሉ ፡፡ ሲጀመር መልአክ ሆኖ የቀረበህ ሁሉ ጠቃሚህ ነው ማለት አይደለም፡ ወሎ አድሮ አጥፊህመሆኑን ቃሉ ያስተምራል፡፡ ሲቀጥል በደል እና ሰቆቃ ሲበዛ መጮህ ያለብን ወደ ገዳዮቻችን ወደ በደሉህ አይደልም (ብዙ ሰው አብይ እየገደለው እና

እያስገደለው የህግ አምላክ መንግስት የለም ወይ ያላል)፡፡ ፀሎትህ እና ጩኽትህ ወደ አምላካችን መሆን ነው ያለበት፡፡ አምላካችንም የፍትህ መልእክትኞችንልኮ ሁሉን ነገር ያስተካክላል፡፡ ከመፀሐፈ ሔኖክ 3 እና 4 የምንማረው ይህንን ነው፡፡

በእርግጥ መፅሃፍት እንደሚነግሩን በጥንት ዘመን በሰው እና በአምላክ መካከል ያለው ግንኙነት ቀጥተኛ ነበር ለዚህም አምላክ ሙሴን አብርሃምን ሄኖክንያነጋገረበት መንገድ ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን በፀሎት ከበረታን አምላካችን ፅሎታችንን ለማግኘት ቅርብ ነው ፡፡

አሁን ያለው የኦትዮጵያ ሁኔታ እና በመፀሐፈ ሔኖክ የተገለፀው ታሪክ በብዙ መልኩ ተመሳሳይነት አለው ፡፡ ጠቢቡ ሰለሞን ከፀሐይ በታች ምንም አዲስነገር የለም ያለውን አስተወሉ፡፤ ለምን በሉኝ ፡ ትላንትና እናተን ከ27 አመታት የወያኔ መከራ እና ስቆቃ ነፃ ላወጣ የመጣሁ ነኝ ያለውን ግለስብን ሰይጣን

ይሁን መልአክ መሆኑን ሳናውቀው በሚሊዮኖች ሆነን በደስታ እና በእልልታ ተቀብለነው ነበር፡፡ በሔኖክ ዘመን የነበሩት ሰዎች መልአክትን የተቀበሉበት

መንገድ በእዚሁ መልኩ ይሆን? አስታውሱ ለ27 አመታት የተዘጋ ቤት ሲከፍቱት ይቀረናል ያለንን እሱ ነው፡፡ የሰውን ልጆች ማስቃያ የሆነውን ሶስተኛ እስርቤት ወደ ሙዜምነት እቀይራለሁ ብሎ በወያኔ የታሰሩትን ፋቶ ፡ የተሰደዱትን ወደ አገር ቤት ሲመለስ በተለይ ባለ ማህተሙ አማራው ወገኔ የዘመናችን

ሙሴ ብሎ በአዳባባይ አንግሶ ጋብቻውን በአደባባይ ፈፀመ፡፡ ይህ ልክ በሸሚያዛ እና በአዛዝኤል የተመራው የመልአክት ቡድን የሰው ልጆችን ፈቅዶ ጋብቻእንደ ፈፀመው ማለት ነው ፡፡ በእኛም ጉዳይ በአብይ ( አዛዝኤል ) ኦሮአማራ የሚለውን ጥምረት ፈጥረው ወደ ቤተ መንግስት ገቡ ወይም አነገስናቸው፡፡

ሔኖክ እንዳስተማረን በሰው ልጆች እና በተወረወሩ መልአክት መካከል በተፈጠረው ጋብቻ ምክንያት የተፈጠሩት ፍጡራን ( ጉዙፋን Nephilim) ምድርንበደም ሞሏት፡፡ ያገኙትን ነፍስ ሁሉ ይመገቡ ጀመር፡፡ ዋይታ እና እሪታም በዛ፡፡ የሄኖክን አስተምርሆ ከአብይ ስርአት ጋራ ስናነፃፅረው እጅግ ተመሳሳይ ሆኖ

እናገኘዋለን ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ አብይ በወላጋ መሳሪያ አስታጥቆ ያስማራቸው ኦነጎች የወለጋን ምድር ከቀን አንድ ጀምሮ እንስካሁን ድረስ አኬል ዳማአድርገዋታል ወድፊትም ያደርጓታል፡፡ ከእዚህ ቀደም የራሳቸው ሰው ጀነራል ከማል ገልቹ አሁን ደግሞ የፓርላማው አባል አንጋሳ እንደነገሩን በወለጋየሚፈፀመው ግድያ በአብይ ቀጥተኛ ትእዛዛ ሰጪነት ፡ በሽመልስ አብዲሳ አስተባባሪነት እንደሆነ አስረግጠው ነግረውናል ፡፡ እዚህ ላይ አብይ ግድያውንአላዘዘም ለሚሉ ዳናቁርት አንድ ምስክርነት ብቻ ላንሳ፡ እሱም አብይ በፓርላማ የተናገረው ንግግር ነው ፡ እንዲህም አለ ፡ በአዲስ አበባ ከፍተኛ ኦሮሞጠልነት አለ ፡ ኦሮሞን ጠልቶ በኢትዮጵያ መኖር የሚፈልጉ ሰዎች አሉ፡ ብሏል፡፡ ይህ ሲተረጎም ኦሮሞ ያልሆናችሁ ወይ ከኢትዮጵያ ውጡ ወይ ትገደላላችሁማለቱ ነው፡፡ ትላንት በአሩሲ በባሌ በሐረር እንዲሁም ዛሬ በወለጋ በሺዎች የሚታረዱት በአብይ በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ መንግድ ባስተላለፈው ተእዛዝመሰረት ነው፡፡

ይህ የማይገባው ሰው ካለ የአብይ የደም ድግስ ገበታ ተካፋይ የሆነ ሰው ብቻ ነው፡፡

ዛሬ በጣም ገኖ የአማራ መታረድ ሞት እና ስቆቃ ቢስማም አብሉሱፈራይ የደም ጥማቱን በአማራ ብቻ የሚያረካ ሳይሆን የተለያዩ የአገራችን ሕዝቦችን ማረዱእና ማሳረዱ አይቀርም ይህ የጊዜ ጉዳይ ነው፡፡ በእርግጥ አሁንም በትግራይ በደቡብ በጋምቤላ ወገኖቻችን የደም ግብር ለአብሉሱፈራይ እየገበሩ እንደሚገኙየአዳባባይ ሚስጢረ፡፡ በእርግጥ ለእዚህ እኩይ ተግባር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ተባባሪ የሆነው ሌላው ሉስፈር ትህነግ መሆኗ ሊሰመርበት ይገባል፡በነገራችን ላይ ስለምን አብሉሱፈራይ አንዳልኩት ጥቂት ላስረዳ፡፡ ሉስፈር የሰይጣን ሌላው ስም ነው ፡ ሉስፈርም ወይም ስይጣን ከመልአክት ሁሉ ከፍተኛውማእረግ የነበረው መልአካት ነበር፡፡ እረጅሙን ታሪክ ለማሳጠር ይህ መልአክ በሰራው ስሕተት ( አምላክ እሆናለሁ ብሎ በማሰቡ፡ ኢሳያስ 14፡ 12᎐15

ይመልከቱ) ከገነት ከክብሩ ተዋርዶ የተባረረ በምድር ላይ ፈላጭ ቆራጭ ሆነ ፡እና በምድር ላይ ከፍተኛው ስቆቃን ያመጣ ነው፡፡ አዎ እኛም ትላንትናከመልአክት ባላነሰ መልኩ ያመነው አብይ ፡ እሱም 7ኛው ንጉስ ነኝ ብሏል ( ፈጣሪ ነኝ ሊል የቀረው ትንሽ ነው) ፡፡

ከሉስፈር ጋራ ተመሳሳይ ነው፡ በእምነት

ትምህርት መሰረት በዓለም ላይ የሚደረጉ ጦርነቶች ሁሉ የሉስፈር የእጅ ስራ ውጤቶች ናቸው፡፡ ምክንያቱም ግብሩ ደም ነው እና ፡፡ በተመሳሳይ መልኩአብይም ግብሩ ደም ነው፡፡ በኦሮሚያ የሚፈሰው ደም የአብይ እና ግብረ አበሮቹ ግብር ነው ፡ ሌላ ትርጉም የለውም፡፡ ሉስፈር አዳም እና ሔዋንን አሳስቷል፡አብይም ሚሎዮኖችን አሳስቷል፡፡ የኖቤል ሽልማት አመራሮችንም ጨምሮ፡፡ ሉስፈር የሰውን ልጅ በጥቅም ( በገንዝብ) ይደልላል ይገዛል አብይም የሰውን. ልጅ በገንዝብ ይገዛል የደልላል ( ካላመኑ እርካብ እና መንበርን ያምብቡ)፡፡ ሉስፈር ለፈጣሪው ባሳየው ንቀት እና ተግደርዳሪነት ከክብሩ ወርዶ ተጥሏል፡አብይም ለፈጠርው ሕዝብ ከፍተኛ ንቀት አለው በአፃፋውም ሕዝቡም አንክ እንትፍ ብሎ ተፍቶታል፡፤ የቀረው ሉስፈር ከገነት እንደተባረረው ሁሉ አብይንእና ግብረ አበሮቹን ከአራት ኪሎ መባረር ነው፡፡ለእዚህም ነው አብሉስፈራይ ያልኩት፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለአብሉስፈራይ የደም ግብር እየገበረ መኖር የለበትም፡ ሰቆቃውም ሊቆም ይገባል ፡፡ የኢትዮጵያሕዝብ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንደ ሔኖክ ዘመን ለአምላኩ መጮህ አለበት ፡ ጩኽቱ ተሰምቶ መልእክቶቹም ለአምላክ እንዲያደርሱለት ተግቶ መፀለይአለበት፡፡

በርግጥ ነው አሁን ያለው ውጊያው ሰው ከሰው ሰለሆነ እንደ ጥንቱ መልአክት መጥተው ወጊያውን በአካል አያደርጉም ፡ ያኔ የተዋጉት ከተጣሉትመልአክት ጋራ መሆኑን አንዘንጋ፡ ዛሬ ውጊያው ስይጣን በውጣቸው ካደረ የሰው ደም ጠጥተው ከማይረኩ በአብይ ( አዛዛኤል) ከሚመሩ ከኦሮሙማየብልፅግና ሰዎች ( ስይጣናት ) ጋራ ነው ፡፡ ሰለሆነም በፅሎትህ አምላክህን በልብህ ነቅስህ ውጊያህን ከእዚህ የዘመናችን ስይጣንት ጋራ ማድረግ አልብህአምላክህ የፍትህ አምላክ ነው እና መላክቶቹን ሰይሞ በወጊያው ከናተ ጋራ ነው ፡፡ ከሴጣናት ጋራ የምታደርገው ውጊያ የተቀደሰ ነው፡፡ ለብ በል ያለመሰዋትነት ነፃነት የለም ደምህን ለስይጣን ከመገበር ለነፃነትህ ፡ለሚስትህ ከብር ለእናትህ ክብር ለልጅህ ነፃነት ለአገርህ ክብር ደግመህ ደግመህ አፍሳት፡፡

የደም ግብር አብሉስፈራይ እየቀለብን መኖር ይብቃ ይብቃ ይብቃ!!!

ምንጭ:- አሻራ ሚድያ

Filed in: Amharic