>

ከአጣዬና የአቅራቢያው መንደሮች በኦሮሞ ወራሪ ሃይል እየተቃጠሉ ነው...!!! (ጌጥዬ ያለው)

 

–  ከአጣዬና የአቅራቢያው መንደሮች በኦሮሞ ወራሪ ሃይል እየተቃጠሉ ነው…!!!

ኤፍራታና ግድም -ሸዋ

 

ጌጥዬ ያለው

ከአጣዬ  በቅርብ ርቀት የሚገኙት መንደሮች ማለትም ዋዬና፣ አርሶ አምባ፣ ሞላሌ፣ ዘንቦ፣ በር ግቢ፣ ሺህ ሰማን በኦሮሞ ወራሪ ሃይል እየተቃጠሉ ነው። በቦታው ሰንደቅ አላማ የሚሉት የኦነግ ጨርቅ ተሰቅሏል። በርካቶች ተጨፍጭፈዋል፤ ቆስለዋልም። ወደ ከተማ የሚወስዱ መንገዶች ሁሉ ተዘግተዋል። ተሽከርካሪ ማለፍ አይችልም። ከጭፍጨፋው ያመለጡት ወደ ዳገታማው የመንዝ አካባቢ እየሸሹ ነው። በአሁኑ ሰዓት የአማራ ልዩ ሃይል በአካባቢው የለም።  እንደ ምንጮች ገለፃ የኦሮሞ ልዩ ሃይል ከጨፍጫፊዎች መካከል ተሰልፎ ይገኛል። ከጨፍጫፊዎች ውጭ ሌላ ታጣቂ ሃይል በስፍራው  የለም።

Filed in: Amharic